TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
20,000 ሰው

"በቃና ቴሌቪዥን 20 ሺ ሰው የሚፈልግ የስራ ማስታወቂያ ወጥቶ ነበር፤ ስራውን #ለመመዝገብ 2480 ብር አካባቢ ያስከፍላሉ እናም ዛሬ ለመመዝገብ "ልደታ መርካቶ" ህንፃ ሄደን ቢሮው #ታሽጓል፤ እነሱም #ታስረዋል ብለው መለሱን። እነዚህ አካላት እውነተኛ ናቸው? አይደሉም? ደግሞስ በሚዲያ እንዴት ይለቀቃል ታማኝ ካልሆነ?? እባክህ አጣራልን። አመሰግናለሁ!"

B ከተባለች የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የደረሰኝን ይህን ጥቆማ ይዤ "አብዛን ንግድ" ወደተባለው ድርጅት ጋር በተደጋጋሚ ስልክ ብደውልም ስልኮቹ በመዘጋታቸው ምክንያት ስለጉዳዩ መጠየቅ አልቻልኩም። ከድርጅቱ ምላሽ ሊሰጥ የሚችል አካል ካለ @tsegabwolde መልዕክት ያኑርልኝ።

/0930787232/
/0902087777/

ጉዳዩን አጣርቼ የምደርስበትን አሳውቃችኃለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia