TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ⬇️

ከሰራዊቱ በተለያዩ ምክንያት የከዱ (የኮበለሉ) አባላት እና የፖሊስ አመራሮች መንግስት ባስቀመጠው የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን #ጥሪ አቀረበ።

ኮሚሽኑ መንግስት ባስቀመጠው የምህረት አዋጁ መሰረት እስከ ግንቦት 30/2010 ዓመተ ምህረት ድረስ ከሰራዊቱ የከዱ አባላትና አመራሮች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

የኮበለሉት የፌዴራል ፖሊስ ሰራዊት አባላት ከነሀሴ መጨረሻ ጀምሮ በመጪዎቹ ስድስት ወራት በምህረት አዋጁ መሰረት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በኮሚሽኑ የህግ ጉዳይ ምክር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር #ፋሲል_አሻግሬ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ በከተማ ፖሊስ ኮሚሽን፣ በፌደራል ፖሊስ ዋናው መስሪያ ቤት እንዲሁም በወንጀል መከላከል ዘርፍ ዳይሬክቶሬቶች በመገኘት ሪፖርት ማድረግ የሚችሉ ሲሆን፥ በክልል የሚገኙት ደግሞ ለክልላቸው ፍትህ ቢሮ ሪፖርት በማድረግ በምህረቱ ተጠቃሚ መሆኑን እንደሚችሉ ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ በዲሲፒሊን ምክንያት ከሰራዊቱ የተቀነሱ አባላት እና አመራሮች ከዚህ ቀደም የወሰዱትን ደብዳቤ ተመላሽ በማድረግ በምትኩ ሌላ የስንብት ደብዳቤና የስራ ልምድ ማግኘት እንደሚችሉ ታውቋል።

የምህረቱ ተጠቃሚ የሆኑ አባላት የወሰዱትን የመንግስት ንብረት ሪፖርት ለሚያደርጉበት ተቋም በመመለስ የነጻነት የምስክር ወረቀት መውሰድ እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል።

ሆኖም በዲሲፒሊን ምክንያት ከሰራዊቱ የተቀነሱ ፖሊሶች ወደ ስራ ቦታ እንደማይመለሱ የስራ አመራር ውሳኔ እንዳሳለፈ ኮማንደር ፋሲል አሻግሬ አስታውቀዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahehiopia
ባህር ዳር⬆️ላለፉት ስድስት ዓመታት ኑሮውን በአሜሪካ ያደረገውና የባህል ሙዚቃ አቀንቃኙ አርቲስት #ፋሲል_ደመወዝ ባሕር ዳር ገብቷል፡፡ በባሕር ዳር ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም አድናቂዎቹ አቀባበል አድርገውለታል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@segabwolde @tikvahethiopia
ትላንት በለገጣፎ ለገዳዲ ምን ሆነ

ሰሞኑን በለገጣፎ ለገዳዲ የከተማው አስተዳደር ህገ ወጥ ናቸው ባላቸው የመኖሪያ ቤቶች ላይ የማፍረስ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎም ሚዲያዎች ወደአካባቢው በመሄድ ሁኔታው ሲዘግቡት ነበር።

በትላንትናው ዕለት የmereja.com ጋዜጠኛ እና የካሜራ ባለሞያ ሁኔታውን ለመዘገብ ወደ ለገጣፎ ለገዳዲ አምርተው #አሳዛኝ ክስተት ገጥሟቸው ተመልሰዋል።

የተፈጠረውን ክስተት በዝርዝር ለማስረዳት፦

Mereja.com ባልደረባ የሆኑ አንድ ጋዜጠኛ(ጋዜጠኛ ፋሲል) እና አንድ የካሜራ ባለሞያ በለገጣፎ ለገዳዲ የተወሰደውን እርምጃ ለመዘገብ ወደ አካባቢው ይሄዳሉ። ስራቸውን እንዳጠናቀቁም ፖሊስ ይመጣና መታወቂያ ይጠይቃቸዋል፤ ጋዜጠኛው እንዲሁም የካሜራ ባለሞያ በፖሊስ በተጠየቁት መሰረት መታወቂያቸውን ይሰጣሉ። ፖሊስም መታወቂያቸውን ኮፒ አድርጎ ይመልስላቸዋል። ከዚህ በኃላ ፖሊስ ስራውን ያለፍቃድ መስራት እንደማችሉ ይነግራቸዋል፤ ፖሊስ ረዘም ያለንግግር ከጋዜጠኛ ፋሲል ጋር ያደርጋል በመጨረሻም መግባባት ላይ ይደረስና የተያዘባቸው እቃ ተመልሶ እንዲሄዱ ይፈቀድላቸዋል።

ጋዜጠኛ ፋሲል እና የካሜራ ባለሞያው ጉዞያቸውን ወደአዲስ አበባ ለማድረግ ታክሲ ውስጥ ሊገቡ ሲሉ ቁጥራቸው ከ10-15 የሚደርሱ #ገጀራ እና #ዱላ የያዙ ወጣቶች በጋዜጠኛ ፋሲል ላይ ደብደባ መፈፀም ይጀምራሉ። ይህ በሚሆንበት ሰዓት የካሜራ ባለሞያው ራሱ ለማዳን ከአካባቢው ለመሰወር ችሏል።

አስገራሚው ነገር ወጣቶቹ በጋዜጠኛ ፋሲል ላይ #ድብደባ የፈፀሙት #ከፖሊስ_ጣቢያ ፊት ለፊት መሆኑ ነው። ፖሊስ በመሃል ገብቶ ከመገላገል ውጭ፤ ወጣቶቹ ለምን ድብደባ እንደፈፁሙ እንኳን ይዞ #አልጠየቃቸውም። የተደራጁት ወጣቶች ከአካባቢው ከሄዱ በኃላ ጋዜጠኛ #ፋሲል በግለሰብ መኪና ወደጤና ተቋም እንዲሄድ ይደረጋል በወቅቱ ምንም አይነት የፀጥታ ሀይል አብሮት አልሄደም።

በጋዜጠኛ ፋሲል ላይ በደረሰው ድብደባ በጭንቅላቱ ላይ 2 ቦታ የመሰንጠቅ አደጋ ደርሷል እዲሁም ከፍተኛ ደም ፈሷል፤ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታልም ሪፈር ተብሎ የሄደ ሲሆን የደረሰበት አደጋ ከፍተኛ ቢሆንም በቤቱ ተኝቶ ህክምናውን መከታተል እንደሚችል ተነግሮ ወደቤቱ ተመልሷል።

ምንጭ፦ ወ/ሮ ፍሬዘር ነጋሽ(የmerej.com ስራ አስኪያጅ) - ለTIKVAH-ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ተከትሎ ከፌዴሬሽኑ ፕሬዘዳንት ከአቶ ኢሳያስ ጅራ እጅ የተቀበሉትን የንሃስ ሜዳሊያ ለደጋፊዎቻቸው ሰጠዋል። የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በሽሬ ስታዲየም እስከ አሁን 1:35 መውጣት አልቻሉም ብሏል ክለቡ። ደጋፊዎቹ በመከላከያ ተከበው እየተጠበቁ ሲሆን ከተማው እስኪረጋጋ እንደሚቆዩና ከሽሬ ወጠው መንገድ እንደሚጀምሩ የደጋፊዎች ማህበር ሊቀመንበር ገልፀዋል።

Via #ፋሲል_ከነማ_የስፖርት_ክለብ
🗞ቀን ሰኔ 30/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፋሲል_ከነማ

በ2019/20 ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣርያ ድልድል ዛሬ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ የሆነው ፋሲል ከነማ ከ ታንዛኒያው አዛም ጋር ተደልድሏል።

Via #SoccerEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ70_እንደርታ #ፋሲል_ከነማ

የመቐለ 70 እንደርታ ቡድን በካኖ ስፖርትስ አካዳሚ በፓብሎ ቦያስ ደሳምፓካ ስታዲየም የመጨረሻ ልምምዱን ትላንት አድርጓል ። የቡድኑ ተጨዋቾች #በጥሩ_ጤንነት መሆናቸውን ተሰምቷል።

በሌላ ዜና...

የአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ማጣሪያ እግር ኳስ ውድድር ፋሲል ከነማን ከታንዛንያው አዛም ክለብ ጋር ያገናኛል፡፡ ጨዋታው ነገ እሁድ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስቴዲየም ይደረጋል፡፡ የፋሲል ከነማ ምክትል አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ እንደተናገሩት አፄዎቹ ለማሸነፍ የሚያስችል መልካም የስነ ልቦና ዝግጅት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ እንደ ምክትል አሰልጣኝ ሀይሉ ነጋሽ ገለጻ ተጫዋቾቹ ለማሸነፍ የሚያስችል ልምምድ በባሕር ዳር ከተማ ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ አፄዎቹ የመጨረሻውን ልምምድ ትናንት አድርገው ዛሬ ዕረፍት ላይ ናቸው፡፡ ጉዳት የደረሰበት ምንም ተጫዋች እንደሌለ እና የተሻለ የስነ ልቦና መነቃቃት እንደሚታይባቸውም ነው የተናገሩት፡፡

Via #AMMA & #ethiokickOff

የስፖርት ጉዳዮችን ብቻ ትከታተሉ ዘንድ👇
@tikvahethsport

⛹‍♀🏋‍♀🏂🏄‍♂🚴‍♀🥊🥋🏇🤼‍♂https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
#ፋሲል_ከነማ

ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ የ2013 የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ይረከባል።

ቡድኑ ዋንጫውን የሚረከበው በአሁን ሰዓት ከሃዋሳ ጋር እያካሄደ ያለውን ጨዋታ እንዳጠናቀቀ ነው።

ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች የቀሩት ሲሆን ፋሲል ሀዋሳን 1 ለ 0 እየመራ ነው።

2 ሺህ የፋሲል ደጋፊዎች በስታዲየሙ ተገኝነዋል::

@tikvahethsport