#AddisAbaba #የተማሪዎችምገባ
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፤ የውሃና የመሰረተ ልማት አቅርቦቶች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚከናወነው የምገባ ሥርዓት ፈተና መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።
ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው የነበረው በአ/አ ት/ት ቢሮ የተማሪዎች ምገባ ባለሙያ አቶ አለሙ ሀይሉ ፥ የምገባ ሥርዓቱ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ትልቁ አጋዥ ነገር እንደሆነ አስረድተዋል።
የሥርዓቱ በት/ቤቶች መኖር ዘርፈ ብዙ ውጤቶች እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል።
ነገር ግን በዚህ ሂደት አንዳንድ ተግዳሮቶች እንዳሉ አንስተዋል።
ምንም እንኳን ካሁን በፊት ከነበረው አንፃር ሲታይ በርካታ ለውጦች ቢኖሩም #የውሃ_አቅርቦት ችግር ተግዳሮት መሆኑን አመልክተዋል።
በተለይ ምገባ ላይ ብዙ ውሃ እንደሚያስፈልግ የገለፁት አቶ አለሙ ፤ " 5 የምገባ ቀናቶች አሉ (ከሰኞ እስከ ዓርብ) በእነዚህ ቀናት መካከል የውሃ አቅርቦቱ እንደተፈለገ የማይሆንበት ጊዜ አለ " ብለዋል።
ችግሩን ለመቅረፍም አማራጮች እየተወሰዱ መሆኑና ተጨማሪ የውሃ ታንከር ጥቅም ላይ እንደሚውል አስረድተዋል።
አንዳንድ ት/ቤቶችን በተባለው ቀንም አድሬስ ከማድረግ አኳያ ችግሮች እንዳሉ ገልጸው " ከዚያ አኳያ ውሃ ነው መታገዝ ያለበት " ሲሉ አሳስበዋል።
ሌላው በመንግሥት እንዲሁም በዓለም ባንክ የተሰሩ የምገባ አዳራሾች የመብራት አቅርቦት እንዲኖራቸው ከማድረግ ጋር ተያይዞ በተወሰነ ደረጃ ተግዳሮት እንዳለ አመልክተዋል።
ምንም እንኳን የምገባ አዳራሾች ቢኖሩም ምግብ ለማብሰያ የሚሆን #የመብራት_ኃይል አቅርቦት ላይ የተወሰኑ ተግዳሮቶች እንዳሉ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በት/ቤቶች ምገባ ሥራ ተሰማርተው ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ሰዎች በተለይ #ከኑሮ_ውድነቱ አኳያ ሲታይ የሚከፈላቸው ክፍያ " በጣም አነስተኛ ነው " በማለት ሲያማርሩ ይደመጣሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህንኑ ምሬታቸውን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው ? ሲል ጥያቄ አቅርቧል።
አቶ አለሙ ፤ " ከምገባ ክፍያ ጋር ተያይዞ እየቀረበ ያለው በየጊዜው እንደዬ ኑሮ ሁኔታው እየታዬ ይሻሻላል። " ብለዋል።
" ለምሳሌ ያለውን የኑሮ ሁኔታ ማዕከል ያደረገ ጥናት በማድረግ ወደ #23 ብር በተማሪ (በነፍስ ወከፍ) እንዲያድግ ተደርጓል " ሲሉ ገልጸዋል።
" በዚህ ዓመት ለምገባ ፕሮግራሙ መጠቀም ያለባቸው ተብሎ የተመደበው ወደ 3.2 ቢሊዮን ብር ነው " ሲሉ አክለዋል።
" በዚያ ደረጃ የተወሰኑ ማሻሻያዎች እየተደረጉ ይኬዳል ማለት ነው። ሲጀመር (የምገባው ፕሮግራሙ) በ14 ብር ነበር አሁን #23 ብር የደረሰበት ሁኔታ አለ። ለቀጣይ ደግሞ ወቅቱን ባገናዘበ ሁኔታ እየተጠና የሚሻሻልበት አሰራሮች አሉ " ሲሉ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ ያገኘው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከሳምንት በፊት ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን የምግብና ሥርዓተ ምግባ ቅንጅታዊ አሰራርን አስመልክቶ የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ሲያደርግ በነበረበት ወቅት ጥያቄ አቅርቦ ነው።
መረጃው የተዘጋጀው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia