TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ጎርጎራ ፕሮጀክት"

የ ‹‹ገበታ ለሀገር›› ፕሮጀክትን ተከትሎ ' 120 ባለሀብቶች ' በጎርጎራ ከተማ በተለያየ የልማት ዘርፍ ለመሰማራት የፕሮጀክት ንድፈ ሀሳብ ማስገባታቸውን የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ መግለፁን #ኢፕድ በድረገፁ አስነብቧል።

የፕሮጀክቱን መጀመር ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ባለሀብት በአካባቢው የልማት ቦታ እየጠየቀ መሆኑን እና ወረዳው ለዚህ የሚሆኑ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑንም አሳውቋል።

ባለሀብቶቹ በሎጅ፣ በሆቴል እንዲሁም በሪዞርት ልማት ላይ ለመሳተፍ ጥያቄ ማቅረባቸውን የተገለፀ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማትና ማቀነባበሪያ፣ በዓሣ እርባታ፣ በእንስሳት በተለይ በዶሮ እርባታ፣ በአኩሪ አተር ልማት፣ በከሰል ድንጋይ ልማት ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸውን ተሰምቷል።

በተጨማሪ በእንስሳት መኖ ማልማትና ማቀነባበርን እንዲሁም በንብ ማነብ ለመሳተፍ ፍላጎቶች ከባለሀብቶች በኩል መምጣቱን የምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Update

"...ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ድጋሜ አይካሄድም" - ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ

ዛሬ ዕለታዊ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ፥ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ ድጋሜ አይካሄድም ብለዋል።

ለህዝበ ውሳኔው መራጮች በያዙት ካርድ እንደሚመርጡ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ሰኞ ከሚደረገው ምርጫ ጋር በተያያዘ የፖለቲካ ፓርቲዎች እስከ ነገ ታዛቢዎቻቸውን ማስመዝገብ እንደሚችሉ አሳውቀዋል።

የቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተም ፥ ከማዕከል የሚከናወነው የቁሳቁስ ስርጭት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

አዲስ አበባ ላይ ከዛሬ 9 ሰዓት ጀምሮ ስርጭት ተጀምሯል፡፡ ማምሻውንም ይከናወናል ተብሏል። በሌሎች አከባቢዎች ከማዕከል ወደ ክልል የሚደረገው ስርጭት ተጠናቅቋል ብለዋል።

ከምርጫ ታዛቢዎች ጋር በተገናኘም እስካሁን ከ120 በላይ ለሆኑ ዓለምአቀፍ ታዛቢዎች ባጅ እንደተሰጣቸው እና አሁንም ለመታዘብ እየገቡ ያሉ መኖራቸውን ወ/ሪት ሶሊያና ገልፀዋል።

#ኢፕድ

@tikvahethiopia
"..ህዝቡን እያሽበርኩ በዚህ እቀጥላለሁ የሚል ከሆነ ዳግም በተጠናከረ መልኩ የሀይል እርምጃ ይወሰድበታል" - ሀገር መከላከያ ሰራዊት

ከሰሞኑን ትግራይ ክልል የነበረው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለምርጫው ሰላማዊነት ሲባል ወደሌላ የአገሪቱ አካባቢዎች መንቀሳቀሱን ተከትሎ በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህውሓት ሚሊሻዎች ከተደበቁበት በመውጣት ሰላማዊውን የትግራይ ህዝብ ሲያሸብሩ ነበር አለ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ በሰጠው መግለጫ።

የሰራዊቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮ/ል ጌትነት አዳነ ፥ ሀገራዊ ምርጫውን ተከትሎ ከውጭም ከውስጥም ስጋት ስለነበር ሰራዊቱ በመንግስት ትዕዛዝ መሰረት ከትግራይ ወደ ማዕከል፣ ምስራቅ፣ ምእራብና የደቡብ የሀገራችን ክፍል እንዲንቀሳቀስ ተደርጎ ነበር ብለዋል።

"ይህን ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ በየጢሻው ተደብቆ የነበረው የህወሓት ሚሊሻ ህዝቡን ሲያስገድድና ሰላማዊ እንቅስቃሴውን ሲያስተጓጉል ነበር" ሲሉ ተናግረዋል።

መከላከያ ሰራዊቱ በወሰደው እርምጃ ህዝብን ወደ ሰላማዊ ኑሮው መመለስ ተችሏል ሲሉም ተደምጠዋል።

ዳይሬክተሩ ፥ በክልሉ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን በፍጥነት በመስራት ገበሬው እንዲያርስ፣ ነጋዴው እንዲነግድ፣ ተማሪዎች እንዲማሩ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ ገልጸዋል።

ይህ መልሶ የማቋቋም ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተደረገ ባለበት ወቅት የህወሓት ሀይል ህዝቡ ተጠቃሚ እንዳይሆን ፋይዳ ቢሲ ትንኮሳዎችን ከተደበቀበት እየወጣ እየተነኮሰ ይገኛል ብለዋል።

በሽብርተኝነት የተፈረጀው ቡድን ህዝቡን እያሽበርኩኝ በዚህ እቀጥላለሁ የሚል ከሆነ ዳግም በተጠናከረ መልኩ የሀይል እርምጃ እንደሚወሰድበት አስጠንቅቀዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-06-24

#ኢፕድ
@tikvahethiopia
እየከፋ የመጣው የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ስርቆት :

በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ በሁምቦ ላሬና ቀበሌ ከፍተኛ ኤሌክትሪክ የኃይል ማስተላለፍያ ታወርና ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ላይ የስርቆት ወንጀል በመፈፀሙ በአካባቢው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ተቋርጦ መሰንበቱን የኢትይጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

የስርቆት ወንጀሉ የተፈፀመው ከወላይታ ሰብስቴሽን ተነስቶ ለሦስት የደቡብ ዞኖች አገልግሎት በሚሰጥ የኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ መስመር ላይ ሲሆን በዚህም ሁለት ታወሮች ወድቀዋል፣ 20 ታወሮች ደግሞ ብረታቸው ተገንጥሎ ተወስዷል፡፡

የኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ መስመሩን ጠግኖ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎችን ሳይጨምር 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጭ ይጠይቃል ተብሏል፡፡

የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ስርቆቱ በተቋሙና በኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የሚያደርስ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ችግሩ የተከሰተባቸውን የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች በእንጨት ምሶሶ በመስራት ለተቋረጠባቸው ለ3ቱ ዞኖች አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ብሏል፡፡

የወላይታ ዞን ዓቃቤ ህግ በከፍተኛና በዝቅተኛ ኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ የሚፈፀማን የስርቆት ወንጀል ለመከላከል በርካታ ጥረቶችን እያደረገ ሲሆን በእዚህም ደርጊቱን የፈፀሙ 5 ግለሰቦች ከ3 ዓመት እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ማድረጉን አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ በስርቆት ወንጀል የተጠረጠሩ 32 ግለሰቦችን በ11 መዝገቦች ላይ ክስ መመስረቱ ተገልጿል፡፡ #ኢፕድ

@tikvahethiopia
የሰኔ ወር የዋጋ ግሽበት ...

የ2013 የሰኔ ወር የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ24.5 ከመቶ ጭማሬ አሳይቷል፡፡

የምግብ ዋጋ ግሽበት የሰኔ ወር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ28.7 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በዳቦና እህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በያዝነው ወርም የቀጠለ ሲሆን ፥ በተለይ የበቆሎና የገብስ ዋጋ በፍጥነት #ጨምሯል፡፡ በተጨማሪ ፦
- ሥጋ፣
- የምግብ ዘይት፣
- ቅቤ፣
- ቅመማ ቅመም፣
- በርበሬና ቡና የዋጋ ጭማሪ በዚህም ወር በመቀጠላቸው ለዋጋ ግሽበት ምጣኔ በፍጥነት መጨመር አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

ያለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ዋጋ ከአሁኑ ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በንጽጽር ዝቅተኛ ስለነበር የዋጋ ግሽበቱ በያዝነው ወርም ከፍ ብሎ ታይቷል፡፡

በሌላ በኩል " ምግብ ነክ " ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት የሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ19 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ከምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ምክንያቶች ውስጥ በተለይም
- በአልኮል፣
- ልብስና ጫማ፣
- የቤት እንክብካቤና ኢነርጂ (ማገዶና ከሰል)፣
- የቤት መስሪያ እቃዎች (የቤት ኪራይ፣ ሲሚንቶና የቤት ኪዳን ቆርቆሮ) ፣
- ህክምና እና ጌጣጌጥ (ወርቅ) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ነው፡፡

አጠቃላይ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር 7 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጄንሲ አመልክቷል፡፡

#ኢፕድ

@tikvahethiopia
#GERD🇪🇹

"...የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምትገነባው ሙሌት አካሂዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ነው" - ፕ/ር ያዕቆብ አርሳኖ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር እና የዓባይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ፥ ኢትዮጵያ ታላቁን የህዳሴ ግድብ የምትገነባው ሙሌት አካሂዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት በመሆኑ የሙሌት ጉዳይ ብዙ የሚያነጋግር እንዳልሆነ ገለፁ።

ፕሮፌሰር ያዕቆብ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት ቃል፤ ሁለተኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ጉዳይ ኢትዮጵያውያን እና የዓለምን ፖለቲከኞች ቀልብ በእጅጉ የሳበ ክስተት ነው ብለዋል።

በተለይ ግብጽና ወደግብጽ ተለጥፋ ያልተገባ ጭቅጭቅ ውስጥ የምትገኘው #ሱዳን በተነዙ የሐሰት ፕሮፓጋንዳዎችና እና አሳሳች መግለጫዎች የተነሳ የህዳሴው ግድብ ሁለተኛው እርከን ሙሌት በተጋነነ ወሬ ውስጥ ነበር ሲሉ ገልፀዋል።

መታወቅ የነበረበትም ሆነ አሁንም መታወቅ ያለበት ጉዳይ #ኢትዮጵያ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምትገነባው ሙሌት አካሂዳ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት መሆኑ ነው ሲሉ አስገንዝበዌ።

ይህ እንደሚሆን ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት ጥናት እና ዲዛይን ፣ በድርድሩ ሂደት ፣ በግድቡ ግንባታ ስራና በየጊዜው በሚወጡ በኢትዮጵያ መንግስት መግለጫዎች መገለጹን አስታውሰዋል።

#ኢፕድ

@tikvahethiopia
የትምህርት ቤት የመመዝገቢያ ዋጋ ፦

የትምህርት ቤት የመመዝገቢያ ዋጋ ከወርሀዊ ክፍያ ከ25 በመቶ በላይ እንዳይበልጥ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን አስታውቋል።

የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ በሰጡት መግለጫ ትምህርት ቤቶችን ለምዝገባ ከወርሀዊ ክፍያቸው በላይ እንዳያስከፍሉ የሚያስገድድ አሰራር መዘርጋቱን ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቶች ለምዝገባ ብቻ ከክፍያቸው በላይ እያስከፈሉ በማስቸገራቸው ምክንያት አሰራሩን መፈተሽ እንዳስፈለገ የጠቆሙት ዋና ስራ አስኪያጇ አዲሱ አሰራር ግን ለዚህ መፍትሄ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

እንደ ወይዘሮ ሸዊት ገለፃ፤ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሬን በሚመለከት ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በሚደረግ ስምምነት መሠረት እንደሚሆን ገልፀዋል። #ኢፕድ

@tikvahethiopia
ከባህር ዳር ተነስቶ አዲስ አበባ ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ።

ከባህር ዳር ተነስቶ አዲስ አበባ ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ሱሉልታ ከተማ በቁጥጥር ስር የዋለው መሳሪያ 83 ትንሿ ሽጉጥ፣ 199 ኤም ፎርቲን ጥይት እና 10 ሺህ 865 የሽጉጥ ጥይት መሆኑ ታውቋል።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና አዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ ባደረጉት የተቀናጀ ክትትል ተጠርጣሪ የሆኑት ሹፌሩና ረዳቱ ተይዘዋል።

#ኢፕድ

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

የጤና ሚኒስቴር ካለፉት ስምንት ሳምንታት ወዲህ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሶስተኛ ማእበል በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑን አስታወቀ።

በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምላሽ አስተባባሪ አቶ መብራቱ ማሴቦ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናግሩት ፤ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ሶስተኛ ማእበል ላለፉት ስምንት ሳምንታት በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መጥቷል።

የወረርሽኙ ማዕበል በተለይ ደግሞ ከሀምሌ ወር የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ጀምሮ መጠነኛ መቀነስ አሳይቶ የነበረ ቢሆንም በነሐሴ ወር እንደ አዲስ ማገርሸቱንና በዚህም ከ600 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

በቀን ውስጥ ተመርምረው ቫይረሱ እንዳለባቸው የሚረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ሃያ በመቶ መድረሱን ያመለከቱት አቶ መብራቱ ፣ በአንድ ቀን ምርመራ ብቻ እስከ 2 ሺ የሚጠጉ ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው እየታወቀ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በቫይረሱ የተያዙ፣ ምልክቱን ያላሳዩ፣ ያልተመረመሩ በርካታ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉና የምርመራ አቅም ውስንነትን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችልም አስታውቀዋል። #ኢፕድ

@tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቋል::

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳውቋል፡፡

ኤጀንሲው ከባለድርሻ አካላት ጋር በዋናነት የ2013 ፈተና ዝግጅት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል።

ከ617 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተናው ዝግጁ እንደሆኑ የገለጹት የኤጀንሲው የቀድሞ ዋ/ዳይሬክተር ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)፤ ለፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት በእጥፍ መጨምሩን ገልጸዋል።

ፈተናው የጸጥታ ችግር ባለባቸው የአማራ እና የአፋር ክልል አካባቢዎችም እንደ ወላጆችና ተማሪዎች ፈቃድ እንዲሁም እንደ አካባቢው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ሊከናወን እንደሚችልም ተናግረዋል።

ፈተናው በ10 የትምህርት አይነቶች መዘጋጅቱንና የኢኮኖሚክስ ፈተና በዘንድሮው መርሃ ግብር አለመካተቱን ገልጸዋል፡፡

አስፈላጊ ቁሳቁሶች ባለመድረሳቸው ምክንያት የዘንድሮው ፈተና ቀደም ሲል እንደነበረው በወረቀት እንደሚከናወን ተገልጿል። #ኢፕድ

@tikvahuniversity @Tikvahethiopia