በ2 ቀን ውስጥ በጎሳ ግጭት 400 ሰዎች ሞቱ‼️
በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ በታህሳስ ወር ላይ ተከስቶ በነበረ #የጎሳ_ግጭት የ400 ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተገለፀ።
በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቅ አካባቢ ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ ተከስቶ በነበረው የጎሳ ግጭት በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ 400 የሚሆኑ ዜጎች ህይዎት አልፏል።
ግጭቱ የተፈጠረውም በዩምቢ ከተማና አካባቢው በሚገኙት #ባቴንድ እና #ባኑን በተሰኙ ጎሳዎች መካከል መሆኑ ነው የተገለፀው።
የግጭቱ ምክንያትም በአካባቢው ለመካሄድ ዝግጅት ላይ በነበረው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ነው ተብሏል።
የባቴንድ ጎሳዎች የገዢውን መንግስት መመረጥ #የሚደግፉ ሲሆን ፥ባኑኖች ደግሞ በአካባቢው እነሱን ወክሎ የሚወዳደረውን #የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች ነበሩ።
በተፈጠረው ግጭትም ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም በርካቶች ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
እንዲሁም በግጭቱ ብዛት ያላቸው ሰዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።
ግጭቱን ተከትሎ የሀገሪቱ መንግስት ታህሳስ 30 ላይ በአካባቢው ሊካሄድ የነበረውን ምርጫ መሰረዙ ይታወሳል።
ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia