TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

ከባድ #የውንብድና ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ። ተከሳሽ #እስጢፋኖስ_መለሰ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01/02/03 ክልል ልዩ ቦታው መርካቶ ለይላ ህንፃ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ግንቦት 21 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሲሆን በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 671/1/ለ/ ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ተከሳሽ የማይገባውን ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ ካልተያዘው ግብራበሩ ጋር በመሆን የግል ተበዳይ
ፋሲል ማሞ የተባለውን ግለሰብ ጋላክሲ ኖት 3 የዋጋ ግምቱ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ብር የሆነውን ሞባይል ቀምቶ ሲሮጥ የግል ተበዳይ ለመያዝ በሚከተልበት ጊዜ ያልተያዘው ግብረአበሩ ለማስቆም #በገጀራ የቀኝ እጅ አውራ እጣቱን የመታውና ጉዳት ያደረሰበት በመሆኑ ተከሳሽ በፈፀመው ከባድ የውንብድና ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል።

ዐቃቤ ህግ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ለፍርድ ቤቱ ያስረዳልኛል ያላቸውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች በማቅረቡ እንዲሁም ተከሳሽ የተመሰረተበትን ክስ ማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን #ጥፋተኛ ነህ ብሎታል። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 7ኛ ወንጀል ችሎትም ህዳር 05 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በ6 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋምቤላ ክልል‼️

በጋምቤላ ክልል በማጅንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ እና አካባቢው በ126 ሰዎች ግድያ፣ 36 ከባድ የአካል ጉዳት፣ ከ 7 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን በማፈናቀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ፍርድ ቤት #ጥፋተኛ ብሏል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት በዛሬ ውሎው በጋምቤላ ክልል #በማጅንግ_ዞን ጉደሬ ወረዳ እና አካባቢው ከ2006 እስከ 2007 ዓ.ም ከሌላ ቦታ የመጡ ነዋሪዎች ላይ ከላይ የተጠቀሱትን ድርጊት በመፈጸም ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው ክስ ተመስርቶባቸው ከ4 አመት በላይ በፍርድ ቤት ክርክር ላይ የነበሩ ከ15 በላይ ተከሳሾች ላይ ነው የጥፋተኝነት ውሳኔውን ያሳለፈው።

ተጠርጣሪዎቹ ከሌላ አካባቢ መጡ ያሏቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችን ሚዚያ 29 በተባለው የመሰብሰቢያ አደራሽ በመሰብሰብ የቡናም ሆነ የሌሎች ምርት ውጤቶችን ለማጅንግ ብሄረሰብ ማከፈል አለባችሁ በማለት ሲዝቱባቸው የነበረ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም የዞን እና የወረዳ ሚሊሻዎችን በማነሳሳት ያልታጠቁትን በማስታጠቅ በአካባቢው ግጭት በመፍጠር የ126 ዜጎች ህይወት እንዲጠፋ፣ 36 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እንዲደረስ እና 7 ሺህ 422 ነዋሪዎች ማፈናቀላቸውን አቃቤ ህግ በክሱ አስረድቷል።

በ2007 ዓ.ም በቁጥጥር ስር በዋሉት ተጠርጣሪዎቹ ላይ አቃቤ ህግ ያስረዳልኛል ያላቸውን የሰነድ እና የሰው ማስረጃ አሰባብሰቦ አሰምቷል።

ተካሳሾቹ የአቃቤ ህግን የሰነድ እና የሰው ማስረጃዎች መከላከል ባለመቻላቸው ጉዳዩን የተከታተለው ፍረድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሏቸዋል።

በዚህ መዝገብ በ39ኛ ላይ ክስ ቀርቦበት የነበረው አቶ ጸጋየ ገሊቶ የቀረበበትን የአቃቤ ህግ የሰነድ እና የሰው ማስረጃ በአግባቡ መካከሉን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በነጻ አሰናብቶታል።

በሌሎቹ ተከሳሾች ላይ ግን የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ ሀሳቦች ለማቀበል ፍርድ ቤቱ ለታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጥንቃቄ አድርጉ‼️ #ከኢትዮጵያ ወደ #ቻይና የምትሄዱ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ሰዎች ይህን እቃ እዛ ላለ ሰው አድርስልኝ/አድርሺልኝ ሲሏችሁ በደንብ የሚላከውን ነገር ፈትሹ። ቻይና ከሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ለመረዳት እንደቻልነው አንዳንዶች በሚላከው እቃ ውስጥ አደንዛዥ እፆችን በመጨመር እንደሚልኩ ጠቁመዋል። በተለይ ምግብ ነክ ነገሮች ውስጥ የአደንዛዥ እፆችን በመክተት ይልካሉ።…
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር‼️

በህገ ወጥ ደላሎች #ነፃ የትምህርት አግኝታችኋል ተብለው ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ #ነብያት_ጌታቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሁለቱ ሀገራት በሚገኙ ህገ ወጥ ደላሎች ነጻ የትምህርት እድል አግኝታችኋል ተብለው ወደ ቻይና የሚጓዙ ዜጎች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ወጣቶቹ አግኝታችሁታል የተባለው ነፃ የትምህርት እድል #ሀሰተኛ በመሆኑ ቻይና ሲደርሱ ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጡ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ከዚህ ባለፈም በቻይና አደገኛ እፅ #በማዘዋወር እና #ጫትን ከኢትዮጵያ ወደ ቻይና በማስገባት በህገ ወጥ ስራ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ቃል አቀባዩ አብራርተዋል፡፡

ቃል አቀባዩ በቻይና በዚህ አይነት ወንጀል መሳተፍ ከእድሜ ልክ እስራት እስከ #ሞት ቅጣት በሚደረስ ፍርድ የሚያስቀጣ መሆኑንም ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም በዚህ ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ 47 ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑት በፍርድ ቤት #ጥፋተኛ ተብለው የእርምት ጊዜያቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ሲሆን የቀሪዎቹ ደግሞ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዜጎች ከተመሳሳይ ችግር ለመውጣት የትምህርት እድል አግኝታችኋል ሲባሉ ከተቋማቱ በቂ መረጃ መሰብሰብ እንደሚገባቸውም ቃል አቀባዩ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል ወደ ቻይና ለተለያዩ ጉዳዮች የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን የታሸጉ ነገሮችን ወደ ቻይና አድርሱልን ተብለው ሲጠየቁ ስለእቃዎቹ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት ይገባቸዋልም ነው ያሉት።

እነዚህ ወንጀሎች የሁለቱን ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት እንዳያበላሹም መንግስታቱ እርስ በርስ የተሳሰሩ ደላሎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሌሎች ሀገራት የሄዱ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ቃለ አቀባዩ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም በተያዘው ሳምንት 1 ሺህ 40 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ እና 1 ሺህ 15 ኢትዮጵያውያን ከፑንትላንድ መመለሳቸውን ጠቅሰው፥ በቀጣይ ሳምንት ደግሞ 500 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ እንዲሁም ከፑንትላንድ 517 ዜጎች እንደሚመለሱ አውስተዋል።

እነዚህን ዜጎች ከሀገራት ለማስመለስ ከአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የግብረ ሰዶም ጥቃት ያደረሰዉ ታዳጊ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ!
.
.
ተከሳሽ የ16 ዓመቴ ታዳጊ ወጣት #ናሆም_መሀሪ የተመሳሳይ ጸታ ግንኙነት ወንጀል በመፈጸሙ በዓቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 631/1/ለ/ ሥር የተደነገገዉን በመተላለፍ ተከሳሽ ከእርሱ ጋር ተመሳሳይ ጾታ ካለዉ ወንድ ልጅ ጋር የግብረሰዶም ጥቃት ለመፈጸም በማሰብ ጥር 16 ቀን 2011ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታዉ ካራ ስጋ መሸጫ አካባቢ በ8ዓመቱ ህፃን ላይ የፈጸመዉን የግብረሰዶም ጥቃት በማስረጃ በማረጋገጡ ነዉ ዓቃቤ ህግ ክሱን የመሰረተዉ፡፡

ተከሳሽ ህጻኑን አባብሎና አታሎ ድርጊቱን ፈጽሞል በግል ተበዳይ ላይም የአካል እና የስነልቦና ጉዳት እንዲደርስበት ምክንያት ሆኗል ሲል ዓቃቤ ህግ በክሱ አስረድቷል፡፡የግል ተበዳይም በጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል የህክምና ምርመራ ተደርጎለት ወሲባዊ ጥቃት እንደተፈጸመበት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየዉ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ ችሎትም የወንጀሉን መፈጸም በሰዉና ከጋንዲ ሆስፒታል በተገኘ የህክምና ማስረጃ አረጋግጦ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት ተከሳሹ #ጥፋተኛ የተባለበት የህግ ድንጋጌ ደረጃና እርከን ስላልወጣለት መነሻዉ ከ16 ዓመት ጀምሮ የሚያስቀጣ ቢሆንም የጥፋተኛዉን እድሜ ከግምት በማስገባት ሰኔ 25 ቀን 2011ዓ.ም በዋለዉ 5ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሹ በ13 ኣመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

Via የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተማሪ ሊዲያ አበራ ጉዳይ ...

በደቡብ ክልል ሀላባ ቁሊቶ ከተማ በሚገኘው የሀለባ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪዋ #ሊዲያ_አበራ የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ/ም ከትምህርት ቤቷ ተወስዳ ከታሰረች በኋላ ጉዳዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኗል።

ሊዲያ ከታሰራች በኋላ ለ5 ቀናት ፍርድ ቤት ሳትቀርብ መቆየቷን እና በእስር ቤት ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደተፈጸመባት አባቷ አቶ አበራ ሻሞሮ እንዲሁም ጠበቃዋ አቶ አበባየሁ ጌታ እንዳገለፁለት ቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት በድረገፁ አስነብቧል።

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሕግ እና ፖሊስ ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ወ/ሮ ታሪኳ ጌታቸው የ14 ዓመቷ ተማሪን ጉዳይ ኮሚሽኑ እየተከታተለ መሆኑን ገልፀዋል።

የሊዲያ እስር ምክንያት ምንድን ነው ?

በሀላባ ቁሊቶ 30 ዓመታት የኖሩት አቶ አበራ ሻሞሮ፣ ሁለት ሴት ልጆች የሃላባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ10ኛ እና 11ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው።

ሊዲያ የካቲት 22/2015 ዓ.ም. በመደበኛ ትምህርቷ ላይ ተገኝታ ነበር።

በዚያን ዕለት ሊዲያ በምትማርበት ክፍል ውስጥ አንዲት ተማሪ መውደቋ የነገሮች ሁሉ መነሻ ነው።

👉 ጉዳዩን በተመለከት ሰሜ አይጠቀስ ያሉ የሀላባ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የሰጡት ቃል ፦

" ተማሪዋ የወደቀችው ሊዲያ መተት አሰርታባት ነው በሚል በተፈጠረ ግርግር የትምህርት ቤቱ ሥራ በጊዜያዊነት ተስተጓግሎ ነበር።

ከጥቂት ጊዜ በኋላም ፖሊሶች ወደ ትምህርት ቤቱ መጡ።

ያለምንም መጥሪያ...ፖሊሶች መጥተው ከነዩኒፎርሟ፣ ከነደብተሯ እያለቀሰች” ከትምህርት ቤት ወሰዷል።

ይህ በጣም አሳሳቢ እና የሚያሳዝን ነው። "

👉 የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ወንድሙ መርጋም የሰጡት ቃል ፦

" በዚያን ዕለት ሌላም ተማሪ መውደቋ ለሊዲያ እስር ምክንያት ሆኗል። ሆኖም ታዳጊዋ ላይ ቀደም ብሎ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው አቤቱታ ያቀርቡባት ነበር።

ከእሷ ጋር አብረን ምግብ በልተናል የሚሉ 8 ተማሪዎች ወላጆች ቅሬታ አቅርበዋል፤ ትምህርት ቤቱ እርምጃ ይውሰድ የሚል ጫናም እየበረታ መጥቶ ነበር።

በዚህ ሳቢያ ትምህርት ቤቱ የቅሬታ አቅራቢ ተማሪዎች ወላጆች ጉዳዩን ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲወስዱ አድርጓል።

በትምህርት ቤት ውስጥ ከእሷ [ሊዲያ] ጋራ ግንኙነት ነበረን፣ ምግብ በልተናል ያሉ 8 ተማሪዎች ወድቀዋል ፤ ይሄ ነገር ከእሷ ጋር ግንኙነት አለው? ወይስ የለውም ? የሚለውን ለማጣራት ነው ክስ ተመስርቶ በዚያው እየታየ ያለው።

በዕለቱ ተማሪዎች ስለተረበሹ እና እርምጃ መውሰድ ስላለብን...ለፖሊስ ልጅቷን በአፋጣኝ ይዛችሁ ብትሄዱ የተሻለ ይሆናል ያልነው። "

ሆኖም ይህ በሊዲያ ላይ የቀረበው ቅሬታ በእህቷ ላይ አልተሰማም ተብሏል።

👉 የሊዲያ ጠበቃ አቶ አበባየሁ ጌታ ፦

" ሊዲያ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰደች በኋላ ከሕግ ውጪ ለ5 ቀናት ፍርድ ቤት ሳትቀርብ ታስራ ቆይታለች።

ከአምስት (5) ቀናት በኋላ ሃላባ መጀመሪያ ፍርድ ቤት ካለ ጠበቃ ጋር ቀርባ የ14 ቀናት ቀጥሮ ለምርመራ ከተሰጠ በኋላ ወደ ሃላባ ቁሊቶ ማረሚያ ቤት ተወስዳለች።

ይህ ድርጊት ከሕግ ጋር የሚጻረር ነው። ለአካለ መጠን ያልደረሰ ሰው በወንጀል ሲጠረጠር ከቤተሰቦቹ ጋር ቆይቶ ለምርመራ ሲፈልግ እንደሚጠራ በሕግ ተደንግጓል።

በተጠረጠረችበት ወንጀል #ጥፋተኛ ሆና ብትገኝ እንኳን የማረሚያ ቤት እስር እንደማይፈረድባት የወንጀል ሕጉ ያስቀምጣል።

በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ላይ ለሃላባ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ተጠይቋል። ይግባኙም የታዳጊዋ አያያዝ እንዲሁም ለቀናት በእስር ላይ እንድትቆይ መደረጉ ተገቢ አይደለም የሚል ነው።

የሊዲያ ከሳሾች ጉዳት ደርሶብናል ያሉት ተማሪዎች ወላጆች ሲሆኑ ልጆቻችንን ላይ ባደረገችባቸው መተት/ድግምት አፍዝዛ ጉዳት አድርሳባቸዋለች የሚል ማመልከቻ አቅርበው ነው የተከሰሰችው።

ክሱ ተሰራ በተባለው መተት / ድግምት ተጎድተው ሕክምና ላይ የሚገኙ ተማሪዎች አሉ ይላል።

ሊዲያም ባለፈው አርብ አግኝተናት አናግረናት ነበር። በወቅቱም ንቅሳት ካለብሽ እናይሻለን በሚል እርቃኗን እንደፈተሿት ተናግራለች።

ሊዲያ እስሩ በተፈጸመባቸው የመጀመሪያዎቹ ቀናት ታለቅስ ነበር። አሁን መምህራን፣ የትምህርት ቤት ጓደኞቿ እና ሌሎች ሰዎች እየጠየቋት በመሆኑ በጥሩ ሞራል ላይ ትገኛለች።

በኢትዮጵያ ሕግ ድግምት ፣ ጥንቆላ፣ እኔ አውቅልሃለሁ ባይነት፣ መንፈስ መጥራት እና መሰል ወንጀሎች የሚዳኙበት ድንጋጌ አለ።

ሆኖም እነዚህ ወንጀሎች ጥቅምን ለማግኘት በማሰብ እና የሌላን ሰው ገንዘብ ለማግኘት የሚፈጸም እንጂ የግል ጥቅም ምን እንደሆነ በማታውቅ ታዳጊ ልጅ፣ ገንዘብ ያለበትን እጠቁማቸኋለሁ ባላለችበት ሁኔታ. . . [ሕጉ] ይህንን ሁኔታ ሊቀበለው አይችለም።

ሰዎችን ለማፍዘዝ የተለያዩ ዱቄት መሰል ምርቶችን ማምረት፣ መሸጥ እና ማሰተላለፍ ወንጀል ነው ሊዲያ ግን ይህንን ሁሉ አላደረገችም።

በማኅበራዊ ሚዲያዎች ለሕይወቷ የሚያሰጉ ዛቻዎች እና ማስፈራሪያዎች እየተዘዋወሩ ነው። በደረሰባት የሥነ ልቦና ጫና ምክንያት ከሥነ ልቦና ጫናው ተላቃ ትምህርቷን ትቀጥላለች ማለት ይከብዳል። "

👉 የሊዲያ አባት አቶ አበራ ሻሞሮ ፦

" ... የልጄ እስር የተወረወረ ዱብ ዕዳ ነው። ልጆቼ በትምህርታቸው ከአጠቃላይ ተማሪ ተሸላሚ ናቸው። እያጠኑ የሚያድሩ ናቸው።

የተቀረውን የትምህርት ጊዜ ሌላ አካባቢ እንዲጨርሱ እየሞከርኩ ነው።

ልጄም በማረሚያ ቤት ባነጋገርኩበት ወቅት መቼ ነው ከዚህ የምወጣው? ብላ ጠይዋኛለች። "

👉 ጉዳዩን በተመለከተ የሀላባ ዞን የቁሊቶ ከተማ አሰተዳደር ሰላም እና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ከቀናት በፊት በፌስቡክ ገጹ ይህን ብሏል ፦

" ... በከተማችን በሙሰሊም ሴት ተማሪዎች ላይ ድግምት አሲራለች ተብላ በታሰረች ተማሪ ሊዲያ አበራ በተያያዥ ጉዳይ በአቶ ናስር በሀላባ በዚህም ጉዳይ መሰል ተያያዥነት ያላቸው ግለሰቦችም ጭምር ተይዘው በምርመራ ሂደት በማረሚያ መኖራቸው ይታወቃል።

በታሰሩበት ኬዝ እንዳንድ አክቲቪስቶች ጉዳዩን ወደ ሓይማኖታዊ ለማስመሰል በማጦዝ የሚሞክሩ እንዳላችሁ በማሕበራዊ ሚዲያ እየታየ ያለው ሁኔታ በፖሊስ እና በምርመራ ባለሙያዎች ሂደቱ እየተጣራና ማንም በተጠረጠረበት ወንጀል ታሰሮ አንደሚጣራ የሚታወቅ  ስለሆነ ሁሉም ማህበረሰብ በትዕግስት እንዲጠብቅ ስንል እናሳስባችኋለን።

#ይህንን_ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውንም  አካል በህግ የምንጠይቅ መሆኑን እናውቃለን። "

የመረጃ ምንጭ ፦ ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት / የሀላባ ዞን የቁሊቶ ከተማ አሰተዳደር ሰላም እና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ናቸው።

@tikvahethiopia