TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በስልጤ ዞን ዛሬ ቢያንስ 2 ሰዎች የገደሉ‼️

በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን ገርቤ በር ወረዳ ባሎቀሪሶ በተባለ ቦታ በዛሬው ዕለት በአካባቢው ነዋሪዎች እና በጸጥታ አስከባሪዎች መካከል በተቀሰቀሰ #ግጭት ቢያንስ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን የዐይን ዕማኞች ተናገሩ። በግጭቱ የቆሰሉ ወደ ወራቤ ሆስፒታል ተወስደዋል። የጀርመን ራድዮ ያነጋገራቸው ሶስት የዐይን እማኞች እንደተናገሩት ሁለት ሰዎች የተገደሉት የጸጥታ አስከባሪዎች በተኮሱት ጥይት ነው። ግጭቱ ዛሬ ጠዋት አራት ሰዓት ገደማ መቀስቀሱን የተናገሩ የዐይን እማኝ "የሞተ ሁለት ነው። ግን በርካታ ቆስሏል። የቆሰለውን ይኸን ያህል አልለውም። በርካታ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

አንድ ሌላ የዐይን ዕማኝ የሟቾቹ ቁጥር ሁለት መሆኑን #አረጋግጠው የግጭቱ መነሾ ለኢንቨስትመንት የታጠረ ቦታ ሊሰጠን ይገባል የሚል ጥያቄ በወጣቶች በመቅረቡ እንደሆነ አስረድተዋል። የዐይን እማኙ የአካባቢው ወጣቶች ታጥሮ የተቀመጠን ቦታ ለማፅዳት ሲሞክሩ "ግብግብ ተፈጥሮ አንድ ሁለት ሰው ሞቷል" ብለዋል። "ከዚህ በፊት ለኢንቨስትመንት የተሰጠ መሬት ነበር። የተሰጠው ባለሐብት ሶስት አመት ሙሉ አጥሮት ነው ቁጭ ያለው። ምንም የሰራው ነገር የለም" የሚሉት የዐይን እማኝ የአካባቢው ወጣቶች በተደጋጋሚ ቦታው ሊሰጠን ይገባል የሚል ጥያቄ ከወረዳ እስከ ክልል አቅርበው ነበር ብለዋል።

"ጠዋት ሁለት ሰዎች ሞተዋል። ቤቶችም ተቃጥለዋል" ያሉ ሶስተኛ የዐይን እማኝ በበኩላቸው በግጭቱ የቆሰሉ ሰዎች ወደ #ወራቤ_ሆስፒታል መወሰዳቸውን ተናግረዋል። ከቆሰሉ መካከል የጸጥታ አስከባሪዎች ይገኙበታል ተብሏል። የዐይን ዕማኞቹ የጸጥታ ኃይሎች ወደ ከተማዋ ከገቡ በኋላ የመረጋጋት አዝማሚያ ይታያል ብለዋል።ወጣቱ ተጭኖ ተጭኖ እየሔደ ነው። ግጭት የተቀሰቀሰባት የገርቤ በር ወረዳ በስልጤ ዞን ከወራቤ ከተማ በ13 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ትገኛለች።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia