TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጅግጅጋ⬇️

በጅጅጋ መሀል ከተማ እንቅስቃሴ የቆመ ሲሆን፣ በመኖሪያ መንደሮች ዘረፋዎች አሁንም ቀጥለዋል። ፖሊሶች የማይታዩ ሲሆን፣ የመከላከያ ሰራዊት አባለት የከተማውን ቁልፍ ቦታዎች ከመቆጣጠር ውጭ ስርአት አልበኝነትን ዝርፊያውን ለማስቆም ጥረት እያደረጉ አይደለም ተብሏል።

#አብዲ ኢሌ የሰጡት መግለጫ ከከተማው ሁኔታ ጋር ፍፁም ተቃራኒ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ አህመድ ሽዴ የኢሶህዴፓ አዲሱ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። #አብዲ_ኢሌ ከክልል ፕሬዘዳንትነት ከተነሱ በኋላ የኢሶህዴፓ ሊቀመንበር ሆነው መቆየታቸው ይታወቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በነፍስ ግድያ፣ ከቀዬ በማፈናቀል፣ በአስገድዶ ማስደፈር፣ የሃይማኖትና የንግድ ተቋማትን በማቃጠል፣ በዝርፊያና በሌሎች በርካታ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው የታሰሩት የቀድሞ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ #አብዲ_ኢሌ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስቀመጡት ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ታገደ፡፡

#REPORTER
#update የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት አቶ አብዲ መሀመድ ዑመርን( #አብዲ_ኢሌ) ጨምሮ የክልሉ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት፥ በተጠረጠሩበት የማፈናቀል፣ የአካል ጉዳትና ህይዎት ማለፍ ወንጀል ለፖሊስ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀን ፈቅዷል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አብዲ_ኢሌ

የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጉዳያቸውን የሚመረምረውን ፍ/ቤት ነፃም #ገለልተኛም አይደለም ሲሉ ተናገሩ፡፡ የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከዚህ በኋላ ጠበቆቻቸውን እንዳሰናበቱና እንደማይከራከሩ ቢገልፁም ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ቆርጧል፡፡

Via #VOAአማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia