TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Free_Nazrawit_Abera
(ከቴዲ አፍሮ)

ኢትዮጵያዊቷ እህታችን ወ/ሪ ናዝራዊት አበራ በየዋህነቷ ምክንያት በአሁኑ ሰዓት በሃገረ ቻይና ወህኒ ቤት ትገኛለች።

ወጣቷ መሃንዲስ ናዝራዊት አበራ ለእስር የበቃችበትና የተከሰሰችበት ወንጀል እስከ ሞት ቅጣት ሊያስፈርድባት እንደሚችልም ቤተሰቦቿ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በመቅረብ እየተናገሩ ነው። የናዝራዊት ቤተሰቦች ቻይና የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሚችለው መንገድ ሁሉ እየተባበራቸው እንደሚገኝ እየተናገሩ ቢሆንም ከጉዳዩ መክበድ ጋር በተያያዘ የመንግሥት፣ የሁሉም ኢትዮጵያውያን፣ የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማትና የመገናኛ ብዙኃንን ርዳታና ድጋፍ የሚያስፈልግበት አስጨናቂ ጊዜ ላይ መድረሳቸውን አሳውቀዋል። በናዝራዊት ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወላጅ እናቷ ግማሽ አካላቸው የማይታዘዝ (Paralyze) መሆኑንም በሚያሳዝን ሁኔታ ተረድተናል።

በዚህም መሰረት የሞት አደጋ የተደገነባትን እህታችንን ለመታደግ በሚያስፈልገው ሁሉ ለመተባበር፣ በኢትዮጵያዊነታችን ብቻ ሳይሆን ሰው በመሆናችንም ጭምር አቅማችን የሚፈቅደውን ሁሉ ለማድረግ ከናዝራዊትና ከቤተሰቦቿ ጎን መቆማችንን እናሳውቃለን።

በናዝራዊት ቤተሰቦችና ጓደኞች በኩል የተጀመረውን የኦንላይን ፊርማ የማሰባሰብ ሂደት በኩልም ጉዳዩ የበለጠ አለም አቀፍ ትኩረት እንዲኖረው ሁላችንም ወደ ድረገፁ በመግባት እንድንፈርምም ጥሪያችንን ለመላው ኢትዮጵያውያን እናቀርባለን።

https://www.change.org/p/the-prime-minister-office-of-ethiopia-free-nazrawit-abera-from-guangzhou-prison
ከሁሉም በላይ ሁሉን ማድረግ የሚቻለው ፈጣሪያችን እግዚአብሔር እህታችን ላይ ከተደገሰባት የሞት አደጋ ይታደጋት ዘንድ በፀሎት እንለምነው።

ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)
#Free_Nazrawit_Abera!!

መንግስት በቻይና መንግስት እፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ እስር ላይ የምትገኘውን ናዝራዊት አበራን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ከfbc ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ መንግስት #ጓንዡ_ግዛት በሚገኘው ማረሚያ ቤት የምትገኘውን የናዝራዊት አበራን ጉዳይ #በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ተናግረዋል።

በስፍራው በሚገኘው የኢፌዴሪ ቆንስላ ፅህፈት ቤት ሰራተኞችም ናዝራዊት በምትገኝበት ማረሚያ ቤት ሶስት ጊዜ በመሄድ ያለችበትን ሁኔታ ተመልክተዋል ነው ያሉት።

መንግስትም ዜጋውን የመከታተል መብቱን ተጠቅሞ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ጠቅሰው፥ ተጠርጣሪዋን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ እየተናፈሱ ያሉ ወሬዎች #ሃሰት መሆናቸውንም ነው የተናገሩት።

በተለይም ከተጠረጠረችበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ #የሞት_ፍርድ_ተፈርዶባታል በሚል እየተናፈሰ ያለው ወሬ ሃሰት መሆኑንም ገልጸዋል።

ተጠርጣሪዋ አሁን ላይ በማረሚያ ቤት የምትገኝ ሲሆን አቃቤ ህግም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ክሱን ካቀረበ በኋላ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት አምርቶ #እንደሚወሰንም አስረድተዋል።

መንግስት አሁን ላይ እንደ ዜጋ መጠየቅ የሚችለውን እያደረገ ሲሆን፥ ትክክለኛ ፍርድ እንድታገኝ ክትትል ይደረጋልም ነው ያሉት።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tijvahethiopia
#Free_Nazrawit_Abera‼️

በቻይና ዕፅ ይዛ ተገኝታለች በሚል ወንጀል ተጠርጥራ በእስር የምትገኘው የናዝራዊት አበራን ጉዳይ የሚከታተል ቡድን ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገለፀ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የሁለትዮሽ የህግ ማዕቀፍ፣ አለም አቀፍ የህግ ስምምነቶችና ከሀገሪቱ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት በመጠቀም ጉዳዩን የሚከታተል ቡድን ማዋቀሩን ገልጿል፡፡

በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ አለምአንተ አግደው ጠቅላይ አቃቤ ህግ ያደራጀው የባለሞያዎች ቡድን በቻይና በናዝራዊት ላይ አየተካሄደ የሚገኘውን ምርመራና እዚህ አገር ቤት ከድርጊቱ አፈፃፀም ጋር ያለውን ሂደት የሚከታተል ይሆናል ነው ያሉት፡፡

በቻይና ዕፅ ይዛ ተገኝታለች በሚል ወንጀል ተጠርጥራ በቁጥጥር ስር የዋለችው ናዝራዊት በሲቪል ምህንድስና ተመርቃ በኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ዘርፍ ተሠማርታ ኢትዮጵያ ውስጥ ትሰራ እንደነበር ከቤተሰቦቿ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የሁለትዮሽ የህግ ማዕቀፍ፣ አለም አቀፍ የህግ ስምምነቶችና ከሀገሪቱ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት በመጠቀም ጉዳዩን የሚከታተል ቡድን አዋቅሮ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን አመልክቷል፡፡

ቡድኑም በቻይና በናዝራዊት ላይ አየተካሄደ የሚገኘውን ምርመራና ኢትዮጵያ ላይ ከድርጊቱ አፈፃፀም ጋር ያለውን ሂደት አቆራኝቶ የቅርብ ክትትል ያደርጋልም ተብሏል።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FREE_NAZRAWIT_ABERA🔝

#የጎንደር_ወጣቶች ጋርድ ማህበር ጎንደር ላይ ፍትህ ለናዝራዊት ይላል!! #ናዝራዊት

@tsegabwolde @tikvahethiopia