TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLaiTadesse

ኅብረተሰቡ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር #እየጨመረ መምጣቱን ከግምት በማስገባት አሁንም የሚያደርገውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ዶክተር ሊያ ታደሰ አሳሰቡ።

ባለፉት 24 ሠዓታት ብቻ 17 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ያሳዘናቸው የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ፤ ''በዚህም ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር አስመዝግባለች'' ብለዋል።

እስከሁን የተመዘገቡትና የተገለጹት ቁጥሮች ትክክለኛ አሃዝ እንደማያሳይ ገልጸው ፤ "የምናውቀው የመረመርነውን ብቻ ነው፣ የመረመርነው ደግሞ ትንሽ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ስለዚህ ወረርሽኙን መርሳትና መዘናጋት እንደማይገባ እና ኅብረተሰቡም ቁጥሩ "ያነሰው በሽታው እኛ ጋር ስላልመጣ ወይንም ስለማይመጣ" እንዳልሆነ ሊገነዘብ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በኬንያ እና በሱዳን በመጀመሪያዎቹ ቀናት ትንሽ ቁጥር ማስመዝገባቸውን ተከትሎ መዘነጋት መታየቱን አስታውሰው ፤ ''ዋጋ አስከፍሏቸዋል'' ብለዋል።

ሕዝቡም ከጎረቤት አገሮች መዘናጋት ትልቅ ችግር ሊያመጣ እንደሚችል በመማር የሚደረጉትን ጥንቃቄዎች ማጠናከር እንደሚገባም አሳስበዋል።

"ትክክልኛ ትምህርትና እርምጃ ለመውሰድ ፣ በብዙ ቁጥር መያዝ ፣ በብዙ ቁጥር መሞት የለብንም" ያሉት ሚኒስትሯ ፤ ያለው #ብቸኛ አማራጭ #መጠንቀቅ በመሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot