TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰላም፣ አንድነት፣ እኩልነት፣ መተባበር፣ ተስፋ፣ ፍትህ፣ ብልፅግና፣ መዋደድ፣ መቻቻል እና ይቅር ባይነት በእናት ሀገሬ ኢትዮጵያ ሰፍኖ ማየት የሁል ጊዜ ምኞቴ ነው።

ኢትዮጵያዊነት ይለምልም! ደም የፈሰሰበት አጥንት የተከሰከሰበት አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራችን ለዘላለም ከፍ ብሎ ይውለብለብ!

ቲክቫህ ማለት ተስፋ ማለት ነው! በእናታችን ተስፋ አንቆርጥም!

#ቲክቫህ #ተስፋ #አንድነት #ሰላም #ኢትዮጵያዊነት #ፍትህ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍትህ ለብላቴናው መሀመድ!

የዛኔው ለጋ ህፃን የአሁኑ ታዳጊ መሀመድ ከዛሬ 12 አመት በፊት የ4 አመት ጨቅላ ህፃን ሳለ ነበር አፍንጫው ላይ የወጣችን አነስተኛ ስጋ ለማስነሳት ቤተሰቡ ጋር በሳኡዲ አረቢያ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል የገባው በወቅቱም እናቱ በገባበት የህክምና ክፍል አጠገብ ሁና የልጇን መውጣት ብትጠብቅም ሳይመጣ ቀረባት ከሰአታት ቡሃላም ፈፅሞ ያልጠበቀችው ያልገመተችው ዱብ እዳ ተነገራት ።

ልጇ መሀመድ በጣም ደክሞ ህይወቱ አደጋ ላይ መሆኑን ሰማች እንዴ በምን ምክንያት? ልጄ እኮ ጤነኛ ነበር ምን አደረጋችሁብኝ… እያለች ጠየቀች አለቀሰች ግን ሰሚ አላገኘችም… …

እነሆ ላለፉት 12 አመታት ወይዘሮ ሀሊማ በሞትና በህይወት መካከል የሚገኘውን ልጇን አይን አይኑን እያየች አጠገቡ ኩርምት ብላ እያለቀሰች ትገኛለች ለመሆኑ ህፃን መሀመድን ምን ቢያደርጉባት ይሆን 12 አመት ሙሉ ከገባበት ሰመመን ሳይነቃ የአልጋ ቁራኛ ያደረጉባት ይሄን ወንጀል የፈፀሙትስ አካላቶች ተጠይቀው ይሆን???

የኢትዮጲያ ኤምባሲ በሳኡዲ ለመሆኑ የመሀመድን ጉዳይ ምነው ዝም አለው??

ቢቢኤን ከወላጅ እናቱ ከወይዘሮ ሀሊማ ባደረገው አጠር ያለ ቆይታ የህፃን መሀመድ እናት ወይዘሮ ሀሊማ ይህን ብላለች...

"ወገኖቼ ሆይ ፍረዱኝ ልጄን ተቀማሁ ሀዘን ጠበሰኝ"

ሀሊማ ሁላችንም ከጎኗ ሁነን ለፍትህ እንጮህላት ዘንድ በየእምነታችን በዱአ እና ፆለት እናግዛት ዘንድ ትማፀናለች።

#ፍትህ ለብላቴናው መሀመድ

©BBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፍትህ_ለጫልቱ!!
#JUSTICE_FOR_CHALTU!

ሴት ሰው ናት!
ሴት ሀገር ናት!
ሴትን #መድፈር ሀገርን መድፈር ነውና በሞት ይቀጡልን!

"እኛም ሴቶች ዜጋ ነን!"

መንግስት የአሲድ መድፋት ወንጀልን ያስቁምልን!

📌 #የአሲድ ጥቃት አስመልክቶ ህግ ይውጣ።
📌 #አሲድ በቀላሉ እንዳይገኝ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረግ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፍትህ_ለጫልቱ!!
#JUSTICE_FOR_CHALTU!!

ሴት ሰው ናት!
ሴት ሀገር ናት!
ሴትን #መድፈር ሀገርን መድፈር ነው!

መንግስት የአሲድ መድፋት ወንጀልን ያስቁምልን!

📌የአሲድ ጥቃትን አስመልክቶ ህግ ይውጣ።
📌አሲድ በቀላሉ እንዳይገኝ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረግ።

#ETHIOPIA
#ፍትህ_ለጫልቱ!!
#JUSTICE_FOR_CHALTU!!

ሴት ሰው ናት!
ሴት ሀገር ናት!
ሴትን #መድፈር ሀገርን መድፈር ነው!

#ፍትህ_ለጫልቱ!!
#JUSTICE_FOR_CHALTU!!

📌በእህታች #ጫልቱ ላይ የደረሰው በደል ልባችንን የሰበረው እንዲሁም ለዚህች ምስኪን ኢትዮጵያዊት ፍትህ ይገባታል የምትሉ ይህንምልክት በመጫን በአንድ ላይ ድምፃችንን እናሰማ።

በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ በደሎችን አንታገስም!
#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፍትህ ለእህቶቻችን⬆️

ከሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ #ቡልጋሪያ አካባቢ ስለደረሰ የመኪና አደጋ መረጃ ሰጥቻችሁ ነበር። አደጋው በሁለት ሴቶች ላይ የደረሰና አደጋውን ያደረሰው የፖሊስ መኪና እንደነበር አይዘነጋም። በነገራችን ላይ አደጋው የደረሰባቸው እህትማማቾች ነበሩ። በዚህ አደጋ የወጣት #ሳራ_ተወልደ ህይወት ወዲያው ሲያልፍ እህቷ #እየሩስ በወቅቱ ለህክምና እርዳታ ሆስፒታል ብትገባም ህይወቷን ማትረፍ አልተቻለም። እንግዴ ከአንድ ቤት ሁለት ሰው ማጣት ቤተሰቡን ምንኛ በሀዘን እንደሚጎዳ መገመት ቀላል ነው።

ዛሬ ደግሞ የሰማሁት እጅግ በጣም አሳዛኝ መረጃ ነው። የመኪና አደጋውን ያደረሰው ግለሰብ እስከዛሬ ለፍርድ አልቀረበም፤ በህግም አልተጠየቀም። ቤተሰቦች #ፍትህ እየጠየቁ ናቸው። አደጋውን ያደረሰው ግለሰብ ለፍርድ እንዲቀርብ እና እንዲጠየቅም ቤተሰቦች ጠይቀዋል።

የሚመለከተው አካል ይህን ጉዳይ ተከታትሎ አጥፊውን ለፍርድ ሊያቀርብ ይገባል‼️

የህግ የበላይነት ይረጋገጥ!
ፍትህ ለእህቶቻችን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አክሱም🔝የአክሱም ሙስሊሞች ዛሬ ጁምዓ ሶላት እንደወትሮው በተለመደው ሰዓትና ቦታ በሰላም ሰግደዋል። በሌላ በኩል በዛሬው እለት አዲስ አበባ የሚገኘው ኑር መስጅድ የሰገዱ ምእምናን #ፍትህ_ለአክሱም_ሙስሊምች በማለት ድምፃቸውን አሰምተዋል።

🔹ከአክሱም ሙስሊሞች ጋር በተያያዘ አንዳንድ ሀላፊነት የጎደላቸው ግለሰቦች በፌስቡክ ሀሰተኛ ፎቶዎች(የቆዩ) በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገር ሲጥሩ ተመልክተናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያን እንፈልጋታለን‼️

ምስኪኑ ዜጋ ሲፈናቀል፣ ሲሰቃይ፣ ሲቸገር፣ ተበደልኩ ሲል፣ ፍትህ ተነፍጊያለሁ ብሎ ሲጮህ፣ መንግስት በድሎኛል ብሎ ሮሮውን ሲያሰማ ለርካሽ #የፖለቲካ_ትርፍ እና #ሀገር_ለማትራመስ የምትሯሯጡ ጨካኝ አረመኔ ሰዎች ኢትዮጵያን ስለምንፈልጋት እጃችሁን ሰብስቡልን።

ሰዎች ሰውነታቸውን ክደው #ሀዘናቸውን እንኳን #ብሄር ለይተው እንዲገልፁ የምትገፋፉ ሰውነታችሁን የከዳችሁ ሁሉ #ኢትዮጵያን ስለምንፈልጋት እጃችሁን ከሀገራችን ላይ አንሱ።

በደንብ ስሙኝ...🔥

ህዝቡን በብሄር ከፋፍላችሁ #ወደጦርነት ለመክተት ፌስቡክ ላይ #ተዘፍዝፋችሁ የምትውሉ ሰዎች--የምትወዱትን ማጣት ስትጀምሩ፣ ምስኪን ህፃናት እንደቅጠል ሲረግፉ ማየት ስትጀምሩ፣ ሚሊዮኖች ሰላም ፍለጋ መሰደድ ሲጀምሩ ስታዩ ደም እምባ እያለቀሳችሁ እያንዳንዷን ፌስቡክ ላይ የዋላችሁበትን ቀን #ትረግሟታላችሁ
.
.
መንግስት በአስቸኳይ #ፍትህ እንፈልጋለን ብለው የሚጮሁ ዜጎች ካሉ ያዳምጥ፤ ምላሽ ይስጥ፤ በምስኪን ዜጎች ህይወት ላይ #ቁማር የሚጫወቱ የፖለቲካ ነጋዴዎችንም አደብ ያስገዛ!

#FACEBOOK ከብዶናል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፍትህ_ለመአዛ

በተስፋ ነዳ

እናቴ….እናቴ…ሰውየው ይታሰር! ሰውየው ይታሰር!

እንዲህ አይነት ሰቆቃ የሰማሁበት ቀን በህይወቴ ትዝ አይለኝም፡፡ በጆሮዬ የሰማሁትን ይህንኑ መዓት ለራሴ እንከዋን ደግሜ ላስበው ባልፈልግም ይህ ህመም ነገ በኔ፣ በአንተ፣ በአንቺ ጓዳ ሊፈጠር እንደማይችል ማረጋገጫ የለኝምና እያመመኝም ቢሆን ልዝለቀው፡፡

መአዛ ካሳ በመንግስት መስርያ ቤት ውስጥ በፋይናንስ ኦፊሰርነት ተቀጥራ ስትሰራ የነበረች በስነምግባሯ የተመሰገነች ሴት ነበረች፡፡ ከባለቤቷ ጋር መፋታቷ ሳያግዳት ሁለት ልጆቿን እያሳደገች የ75 ዓመት አዛውንት የሆኑት እናቷንም የምትረዳ ታታሪም ነበረች፡፡ እህቷ እንዲህ አለችኝ ‹ እኛ እኮ ለራሳችንም መሆን አቅቶናል…እሷ ግን የመንግስት ስራ እየሰራች በትርፍ ጊዜዋ ደግሞ በስልክ ድለለላ እየሰራች እየተሯሯጠች እናታችንንም የምትረዳ ነበረች፡፡›

ታድያ በዚህች ሴት ላይ አንድ ክፉ አይን አረፈ፡፡ መኩሪያ (ለጊዜው ስሙ የተቀየረ) በቅርቡ በተቀጠረችበት መስርያ ቤት ውስጥ በካሸሪነት ሲሰራ 90000 ብር ጎድሎበት ታግዶ… በኋላም ወደ ሌላ መደብ ተቀይሮ ነበረ፡፡ የመአዛን ቅጥር ተከትሎ ይህ ሰው አይኑን አሳረፈባት፡፡ ሁለት ልጆች እያሏት የ3 ወር ፅንስ እንዳላት እያወቀ አፈቀርኩሽ ይል ጀመር፡፡ ጥርጣሬ አደረብኝ! ምነነቱ ለጊዜው ሊገለፅ የማይፈልግ በስራዋ አካባቢ የሚያውቃት ሰውም ጉዳዩ የፍቅር ሳይሆን መኩሪያ እሷን ሊጠቀምባት ፈልጎ እንደነበረ…የተወሳሰቡ የፋይናንስ ኬዞችም እንደነበሩ ገለፀልኝ፡፡ ለእህቷም ይሄንነኑ አነሳሁባት ‹አዎ እሱኮ አፈቀርኩሽ ያላት ገና በገባች የመጀመርያው ቀን ነው፡፡ ልጆቿን ይዛ ስትሄድ ብስኩት ጋባዥ ይሆናል.. እኔ ራሱ ሄጄ በአንድ ቀን ነው የተግባባኝ እነደውም ግብዣ ሲያበዛብኝ ገርሞኝ ነበረ› ትላለች፡፡ እንግዲህ ይህ ያልታወቀ ተልዕኮ ያነገበ የሚመስለው የፍቅር ጥያቄ በሷም ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በተደጋጋሚም እንደማትፈልገው ነግራዋለች፡፡

ጥር 1 ለእህትየው ደውሎ ነገ ነይ እስቲ እንጨዋወት ቢላትም እህትየው ግን መደወሉ እየገረማት እንደማይመቻት ትነግረዋለች፡፡ ጥር 2 መአዛ ቤቷ እንግዶች ጠርታ ስለነበረ ለመውጣት እየተቻኮለች እያለ ቢሮዋ ሆኖ አስር ጊዜ እግሩን እየዘረጋ ሊያደናቅፋት ይሞክራል፡፡ ጉዳዩ ያልገባት መአዛም ከቀልድ ቆጥራው ትቆጣዋለች፡፡ ሎከሯን ከዘጋች በኋላ ውሃዋን ልትጠጣ ስታነሳ ከለሩን ቀይሯል፡፡ ይሄ የኔ ውሃ አይደለም ተቀይሮብኛል ስትል ‹ ምን ይቀየርብሻል ከጠረጵዛ ላይ ያነሳሁልሽ የራስሽ ነው › ይላታል፡፡ መልሶ ሌላ ውሃም ያመጣላታል.. ይሄም የኔ አይደለም! ስትለው ማበድ ይጀምራል፡፡ ‹ውሃዬን ቀየርክብኝ ብላ ስሜን አጠፋች › ብሎ ይጮሃል፡፡ እንደምንም ጉዳዩ በርዶ ልትወጣ ስትል ከኋላዋ ይነካታል፡፡ ‹መአዚ እንኪ › ይላታል፡፡ ዘውር ስትል የያዘውን ጩቤ ሆዷ ውስጥ ይሰካዋል፡፡ መሰካቱም ሳያንስ ከጨጓራዋ ወደታች 15 ሲንቲሜትር ይሸነትረዋል..‹ ውስጡን አማሰለው፡፡› ትላለች እህቷ፡፡ ይሄኔ መአዛ በደመነፍስ ጩቤውን ከሆዷ አውጥታ ትይዘዋለች፡፡ እህቷ እነደነገረችኝ መአዛ በጊዜው ‹ ልሰካበት እችል እኮ ነበረ..ግን የልጆች አባት ነው…እንዴት እሱ ተሳሳተ ብዬ ልሳሳት › ብላለች፡፡ ከዚህ በኋላ ጩቤውን ወንበር ስር ወርውራ አምልጣ ብትወጣም ሰዎች ዕያዩ ..በቪድዮ እየተቀረፀ.. ሴቶች በመሆናቸው ማስጣል እቅቷቸው… በተደጋጋሚ ጀርባዋን በጩቤው ወጋት፡፡ በመጨረሻም ሰው መጥቶ አስጣላት፡፡

ከዚህ በኋላ ወደ ሆስፒታል ሄደች.. በተዐምር ተረፈች… የደሟ አይነት ጠፍቶ ለሰአታት ቆየች… ውስብስብ ህክመናን ቀዶ ህክምናን ጨምሮ አካሄደች (ብዙ ዝርዝር ጉዳዮች ስላሉት እዚ መፃፍ አስፈላጊ አይደለም፡፡) ጨጓራዋ በመቀደዱ አሲዱ ወጥቶ ሰውነቷን ጨረሰው..በፊስቱላ ተይዛ በአፏ የገባው ሁሉ በአንጀቷ ይወጣል፡፡ ይቺ ምስኪን ሴት ላይ ይሄን ጨምሮ ብ ሰቆቃ ደረሰ.. ሃኪሞች የቻሉትን ሁሉ ጥረት አደረጉ…
በዚህ ሁሉ ጊዜ የተጠርጣሪው እህት ፣ አክስት ና ሁለት ጎረምሶች ሆስፒታሉ ውስጥ ያንዣብባሉ፡፡ ከዛ አልፎም ለእህቷ የእናሳክምልሽ ጥያቄ አቀረቡ እህቷም ማንነታቸውን ባለማወቅ የመስርያ ቤት ሰው ነን ስለለዋት ‹እስካሁን የት ነበራችሁ › የሚል ወቀሳ ከማቅረብ ውጪ ጥያቄያቸውን አልገፋችም ነበር፡፡ መአዛ ግን ‹ ሊገሉኝ ውሃዬን ሊቀይሩብኝ መጡ › ብላ አበደች፡፡ በሌላኛው ቀን ተጠርጣሪው ከየት እነደሆነ ባይታወቅም በእህቱ ስልክ ደውሎ ‹ ደህና ነች በሉልኝና በዋስ ልውጣ ..ከዛ አሳክማታለሁ› አለ፡፡ እህተዋ ጥያቄውን አልተቀበለችውም፡፡

ብዙ ታሪክ ሆነ… እህትየው ትላለች.. ‹ለአንድ ለአምስት ቀን አንድ ጉዳይ ስለነበረኝ..እስራሁለት ቀን ያለ እንቅልፍ ካስታመምኳት በኋላ..ሰው ተክቼ ወጣሁ ..ደህና ነበረች..ትበላ ነበረ…ታወራ ነበረ… በሁለተኛው ቀን ነይ ተባልኩ.. ያለኔ ስለማይሆንላቸው ነው ብዬ ነበረ ያሰብኩት ግን ሲርየስ ኬዝ ነው ሲሉኝ በላዳ ስበር ሄድኩ…› እነዲህም ሆነ ያቺ ምስኪን ሴት በምን እነደሆነ ባለታወቀ ምልኩ በድንገት አብዳለች…ማንንም አታቅም..ጥቁር ሆናለች.. ትጮሃለች …ከአማኑዔል ሆስፒታል መድሃኒት መጣ..መዋጥ ስለማትችል በመርፌ ተሰጣት.. በቀጣይ ቀናትም ይኸው ህይወት ቀጠለ፡፡

ከሶስት ቀን በፊት እነቷ እጅ ላይ እነደተኛች አሸለበች፡፡ እነትየው ተከራከሩ ‹ ልጄን አትነኳት ከተነሳች ትጮሃለች.. ማነሽ አንቺ አላቅሽም ትለኛለች ካለችኝ ቀድምያት ሞታለሁ!› ግን አልፋ ነበረ፡፡

‹ገደሉኝ ..መጡ..በር ዝጉ..ውሃዬን ይቀይሩታል.. ብላ እነደጮኸች በር በሩን እነዳየች መአዛ አለፈች፡፡ ሁለት ልጆቿን ቻው እንኳን ሳትል አለፈች፡፡

የሰባት አመት የመጀመርያ ልጇ ልቅሶ ቤት ውስጥ እየዞረች ‹እናቴ የት ሄደች..የትኛው አፈር ውስጥ ነው ያለችው ትላለች፡፡› ጡት ያልጣለው ሁለተኛ ልጇ ነገር አለሙ ሳይገባው ጣቱን ይጠባል፡፡
እስከአሁን ቤተሰቦቿ ፍርድቤት ቀርበው አያቁም.. ሄደው ተከልክለው ተመልሰዋል…በስሚ ስሚ ከሚሰሙት ውጪ የክሱ ሂደት ምን ደረጃ ላይ እነዳለ አያቁም.. እበካችሁን የህግ ባለሙያዎች ድረሱ!

ሁለቱ ልጆች በቃጣይ ሊያድጉ የሚችሉት እያታቸው ዘንድ ቢሆንም አያትየውም የመኣዛን እጅ ጠብቀው አዳሪ ነበሩና ምንም ማድረግ የማይችሉ ናቸው፡፡ እባካችሁን እንድረስላቸው!
የእናቷ የባንክ አካውንት በፎቶ እስካሳውቃችሁ ድረስ ይሄን ፖስት ለወገኖቻችን በሙሉ በማድረስ ተባበሩኝ!

ለመረጃ፦
ሜሽ 0979491370
ተስፋ 0924410897 መሄድ ለምትፈልጉ አድራሻቸው ..ሳሪስ ወርቁ ሰፈር!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update #ፍትህ_ለመአዛ

"...ተጠርጣሪው አምልጧል!.."
የተበዳይዋ የመአዛ እህት ደወለችልኝ።

''ተስፋ እባክህን የምትችለውን አርግልን... ተጠርጣሪው አምልጧል። የቤቷን የልጆቿን አድራሻ ያውቃል። 'የህግ ያለህ' ብለህ ጩህልን። "

ከዚ በላይ መቀጠል አልቻለችም።

መአዛ በህክምና ላይ ሆና ስትሰቃይ ቤተሰቦቿ የህጉን ሂደት መከታተል አልቻሉም። ፖሊስም 'እየተጣራ ነው' ከማለት ውጭ ምንም መረጃ አልሰጣቸውም።

በመሀል የት ሆኖ እንደደወለ ባይታወቅም ደውሎ ' መአዛ ደህና ናት ብላችሁ አስፈቱኝ' ብሏል።

እህትየው ዛሬ ለመርማሪው ስትደውልለት ስልክ አያነሣም። በሌላ ሰው ሲደወልለት ደግሞ 'ሀኪም ቤት ስንወስደው አምልጦናል' ብሏል።

ምን አቅም አለኝ? ምን ላርግላት?
ማድረግ የምችለው ጩኸታቸውን መጮህ ነው።

እባካችሁን አጋሩልኝ
ለመረጃ 0924410897

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአፋር ውሎ...🔝

በአፋር ክልል አንድ ታዳጊ በመከላከያ ሰራዊት አባላት #መገደሉን ተከትሎ #ፍትህ የጠየቁ ወጣቶች በገዋኔ፣ በረሃሌና አዋሽ አካባቢዎች መንገዶችን ዘግተው ውለዋል። በዚህም አዲስ አበባን ከጅቡቲና የትግራይ ክልልን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘው መንገድ ለሰዐታት ተዘግቶ ነበር።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ያስተዛዝባል...ቅን ልብ ቢኖረንስ??
(ውስጣችን ንፁህ ስላልሆነ ይሆን የምንፈራው?)

ይህን ፅሁፍ ያገኘሁት ከአንድ ከ200,000 በላይ ተከታዮች ካሉት የፌስቡክ ገፅ ነው። መልዕክቱ ብዙዎች ጋር ደርሶ ሰዎችን #መቀየር ይችላል ግን አይተን እንዳላየን ያለፍነው ብዙዎች ነን!! ሼር ያደረጉት እንኳን 13 ሰዎች ናቸው። ይሄኔ ግጭት፣ ረብሻ፣ የጦርነት ቅስቀሳ፣ የሀሰት ዜና...ቢሆን #በሺዎች የምንቆጠር ሰዎች ነበርን #ላይክ እና #ሼር የምናደርገው። ያሳዝናል! እውነት ሰላም እና ፍቅርን የምንፈልግ፤ እውነት #ፍትህ እና #እኩልነት የምንፈልግ ሰዎች ከሆንን ውስጣችን #ቅን ሊሆን ይገባዋል፤ ለሀገር እና ለህዝብ የሚጠቅሙ ነገሮችንም ማጋራት አለብን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የወላይታ_ሶዶ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍ ማጠቃለያውን በሶዶ ስታዲየም እያደረገ ይገኛል፦

√ጋሞ፣ ጎፋ፣ ሲዳማ፣ ዳውሮ የወላይታ #ወንድም ሕዝቦች ናቸው!

√ኢትዮጵያዊነት #ፀጋ እንጂ ኩነኔ ሊሆን አይገባም!

√የኢንዱስትሪ ፓርኮች #ለወላይታ!

√ወላይታ #የብሔር ጠላት የለውም!

√ልማት ለወላይታ፣ #ፍትህ ለወላይታ

√ለሕገመንግስታዊ ጥያቄ ሕገመንግስታዊ መልስ ይሰጠን!

√ወላይታ #ፍቅር ነው ሁሉን #ያቅፋል!

Via ናትናኤል መኮንን & TIKVAH-ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፍርድ

በጉራ ፈርዳ የእርስ በርስ ግጭት በማስነሳት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አንዲደርስ ያደረጉ 45 ተከሳሾች እንደ ወንጀል ተሳትፏቸው እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አንዲቀጡ መወሰኑን የፍትህ ሚኒስቴር አሳውቋል።

በደቡብ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን በጉራ ፈርዳ የእርስ በርስ ግጭት በማስነሳት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አንዲደርስ ያደረጉ 45 ተከሳሾች እንደ ወንጀል ተሳትፏቸው እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አንዲቀጡ ተወሰኖባቸዋል ።

የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሚዛን -ቦንጋ-ጋምቤላ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት ነው ።

ተከሳሾች ከ2011 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ባሉ ጊዚያት የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም በወረዳው የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች ምንም መሬት የላቸውም፤ መሬታችንን ለቀው መሄድ አለባቸው በማለት በደቡብ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን በጉራ ፈርዳ ወረዳ የሚኖሩ የሸኮና የመዠንገር ብሔረሰቦች በአማራ ብሔር ላይ የጦር መሳሪያ አንስተው የእርስ በርስ ጦርነት እንዲነሳ ለማድረግ በማሰብ ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም በጉራ ፈረዳ ወረዳ ጌኒቃ ቀበሌ ሌንጣ መንደር አንድ የሸኮ ብሔረሰብ ተወላጅ ተገድሎ በመገኘቱ ይህን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ገዳዩ ማን እንደሆነ ባልታወቀበት ሁኔታ ልጃችንን የገደሉት አማራዎች ናቸው፤ የእኛ ሰው ሞቶ አማራ እዚህ ሀገር ቆሞ አይሄድም በማለት ሌሎች የጦር መሳሪያ እንዲያነሱ በማድረግ ፦

- የ30 (ሰላሳ) ሰዎች ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ አንዲጠፋ፤

- 14 (አስራ አራት) ሰዎች የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ፤

- 3,930,850. (ሶስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ሺህ ስምንት መቶ ሀምሳ ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም

- 5,273 (አምሰት ሺ ሁለት መቶ ሰባ ሶስት ) የሚሆኑ የአከባቢው ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉ ያደረጉ በመሆኑ ተከሳሾች በህብረትና በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የእርስ በርስ ጦርነት ማስነሳት ወንጀል በጠቅላይ አቃቤ ህግ ዘርፍ የተደራጁና ደንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶ ነበር።

ዐቃቤ ህግ ወንጀሉ በተፈፀመበት ቦታ በመገኘት ከፖሊስ ጋር በመሆን ከወንጀል ምርመራው አንስቶ ክስ መስርቶ ሲከራከር እንዲሁም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሚዛን -ቦንጋ-ጋምቤላ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን ሲመለከተው ከቆየ በኋላ በ45 ተከሳሾች ላይ እንደ ወንጀል ተሳትፏቸው የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

በዚህም መሰረት የፌዳ,ደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሚዛን -ቦንጋ-ጋምቤላ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት በ45 ተከሳሾች ላይ የሚከተለውን የቅጣት ወሳኔ አስተላልፏል።

➡️ ኮ/ብል ኢሳቅ ጃፍሮ የተባለ #ፖሊስን ጨምሮ ስምንት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ23 ዓመት ፅኑ እስራት፤

➡️ ሶስት ተከሳሾች በ18 ዓመት፣

➡️ አራት ተከሳሾች በ16 ዓመት ፣

➡️ አራት ተከሳሾች በ15 ዓመት ፣

➡️ ሰባት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ10 ዓመት

➡️ አስራ ዘጠኝ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው ከ8 ዓመት ከ5 ወር እስከ 3 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል።

#ፍትህ_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2005 የ20/80 ባለ3 መኝታ ተመዝቢዎች ፦ " ... በ14ኛው ዙር የዕጣ አወጣጥ የከተማ አስተዳደሩ ቤቶች በቴክኖሎጂ ሆነ በማኑዋል ዕጣ የማውጣት ሂደቶች በሚፈጠሩ ችግሮች ሊወጣለት ከሚገባው ባለእድለኛ ወጪ ለሌላ ለማይመለከተው አካል እንዳይተላለፉ የሄደበትን ርቀት እናደንቃለን፡፡ ነገር ግን ይህ ቁርጠኝነት በባለ3 መኝታ 2005 ዓ.ም የ20/80 ተመዝቢዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲገለጽ እንፈልጋለን፡፡…
#መልስ_ያላገኘው_ጥያቄ

የ2005 የ20/80 የባለ 3 መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤት ቆጣቢዎች ባለፈው ሙሉ በሙሉ የተሰረዘው ዕጣ ሳይወጣ የእነሱ ጉዳይ ላይ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ግልፅ የሆነ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው በድጋሚ አሳሰቡ።

የጋራ መኖሪያ ቤት ይደርሰናል ብለው እየቆጠቡ ያሉ ወገኖች አለን ስላሏቸው ጥያቄዎች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ማሳወቃችን አይዘነጋም።

" ዛሬም ድረስ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ የሚሰጠን አጥተናል " ያሉት ነዋሪዎቹ " ከልጆቻችን ምግብ ቀንሰን፣ በቤት ክራይ እየተሰቃየንና እየተማረርን ላለፉት 9 ዓመታት ቆጥበን ስለምን በዕጣው ልንካተት እንዳልቻልን በግልፅ ሊነገረን ይገባል " ብለዋል።

የቀጣዩ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ከመውጣቱ በፊትም መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጠይቀዋል።

የ2005 ዓ/ም 20/80 ለባለ 3 መኝታ ቆጣቢዎቹ ፤ " #ቤቶቹ_የትገቡ ? ፣ #ተስፋ_አድርገን_ነበር#13ኛው_ዙር_ላይ_97_አልቋል_ብላችሁን_አልነበር?! ፤ #ባለ3_መኝታ_ኦዲት_ይደረግ#ፍትህ_እንሻለን! "በሚሉ እና በሌሎች ሀሽታጎች በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ በመሰባሰብ ጥያቄያቸው መልስ እንዲያገኝ ዘመቻ እያካሄዱ መሆኑን ገልፀዋል።

https://t.iss.one/tikvahethiopia/72439?single
https://t.iss.one/tikvahethiopia/72244?single
https://t.iss.one/tikvahethiopia/72384?single
https://t.iss.one/tikvahethiopia/72271

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይፈለጋል #Wanted ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው መሀመድ ሽኩር አበባው በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትሉን አጠናክሮ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል። አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠርጠሪው እንደተያዘ በማስመሰል የሚያሰራጩት መረጃ #ሀሰተኛ መሆኑን አስታውቋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጠርጣሪው ሳይያዝ እንደ ተያዘ አድርጎ መረጃ ማሰራጨት ተገቢ እንዳልሆነ የገለፀው የአዲስ አበባ…
" እስካሁን ፍትሕ አልተሰጠም "

በአዲስ አበባ ፣ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ' አስኮ አዲስ ሰፈር ' በጥይት ተመተው የተገደሉት የበድር መስጂድ ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም በመስጂዱ የተለያዩ ኪታቦችን በማቅራት የሚታወቁት አቅሪ ሸይኽ አብዱ ያሲን ከተገደሉ ዛሬ 20 ቀን ሆኗል። 

ሸይኽ አብዱ የተገደሉት ከዒሻ ሰላት በኃላ ወደ ቤታቸው ሲሄዱ በጥይት ተመተው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

ምንም እንኳን ሼይኽ አብዱ ከተገደሉ በርካታ ቀናት ቢያልፍም እስካሁን #ፍትህ እንዳልተሰጠ ፤ ይህም በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ሃዘን እንደፈጠረ " ሃሩን ሚዲያ " ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ በሼይኽ አብዱ ያሲን ግድያ ይጠረጠራል ያለው " መሀመድ ሽኩር አበባው " የተባለ ግለሰብ እንደነበር ይታወሳል።

ግለሰቡን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ መሆኑን ከመግለፅ ባለፈ በማህበራዊ ሚዲያ ፎቶውን በማሰራጨት ህብረተሰቡ ያለበትን ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርቦም ነበር።

ከዛ በኃላ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ስለመዋሉ / ስለመገኘቱ ምንም የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia