TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update⬆️የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሀይሎች የመጨረሻውን #የሰላም ስምምነት አዲስ አበባ ላይ ተፈራርመዋል። ተቀናቃኝ ሀይሎቹ በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ በተካሄደው 33ኛው የኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ነው የሰላም ስምምነቱን የተፈራረሙት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Tigray , #Mekelle

የፕሪቶሪያውን #የሰላም_ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ በምግብ እና ሸቀጦች ላይ ቅናሽ እየታየ መሆኑን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል።

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ስለታየው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ቅናሽ በ " ቀዳማይ ወያነ ገበያ " ያሉ ነጋዴዎች እና ሸማቾች ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥተዋል።

አለቃ አረጋዊ ጨርቆስ የተባሉ ነጋዴ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፦

- ሰርገኛ ጤፍ 11 , 000 ብር ይሸጥ የነበረው አሁን ከ6000 እስከ 6500 እየተሸጠ ነው።

- ነጭ ጤፍ 14,000 እስከ 13,500 ይሸጥ የነበረው አሁን 10,000 ብር እየተሸጠ ነው።

" ይህ የሚመጣው ከመኸኒና ከአካባቢው ብቻ ሲሆን አላማጣ ዝግ ነው፣ ጨርጨር ዝግ ነው። መንገድ በምዕራብ አቅጣጫ በሽረ በኩል ዝግ ነው ፤ ወቅቱ ጥቅምት እና ህዳር ቢሆንም በሁሉም አቅጣጫ መስመር ቢከፈት ይቀንሳል።

ሰላሙን ተከትሎ ከመሃል ሀገር ቢመጣ ደግሞ በደንብ ይቀንስ ነበር።

በተለይ ነዳጅ ቢገባ አሁን ውድ የሆነው ትራንስፖርት ይቀንስ ነበር። አንድ ሊትር ነዳጅ በጥቁር ገበያ 350 ብር እየተገዛ ሲሆን ከነዳጅ ማደያ የሚገዛ ነዳጅ ቢኖር ኖሮ በደንብ ይቀንስ ነበር " ብለዋል።

በመቐለ የስንዴ ዋጋ በኩንታል ከ10 ሺህ ብር ወደ 7 ሺህ ብር ቀንሷል።

ሰመሃል ኪዳኔ የተባለች የበርበሬ ነጋዴ ደግሞ ለአንድ ኪሎ ግራም 700 ብር የነበረው በርበሬ አሁን 500 ብር ገብቷል ይህ የሆነው በሰላሙ ስምምነት ተስፋ በማድረግ ነጋዴው ይቀንሳል ብሎ ስላመነ የያዘውን በቅናሽ እየሸጠ በመሆኑ ነው ብላለች።

" ህዝባችን ተጨቁኗል፣ በጣምም ተርቧል፣ አጥቷል #ሰላም በመሆኑ ተጠቃሚ ነን ፤ በጦርነት ኪሳራ እንጂ ልማት የለም ፤ ድርድርን ተከትሎ ባንክ ቢከፈት የቴሌኮም አገልግሎት ቢጀመር እንዲሁም ነዳጅ እንዲገባ ነው #ተስፋችን " ብላለች።

ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው የሰጡ ሩፋኤል የተባሉ ሸማች ፤ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የሸቀጦች ዋጋ በጣም ወርዶ ማግኘታቸውን ገልፀዋል። ሙሉ በሙሉ ቀንሷል ባይባልም ለውጦች እየታዩ መሆኑን አመልክተዋል።

ዘይት 1,700 እና 1,800 የነበረው ወደ 1,400 ዝቅ ማለቱን ገልፀዋል። ፉርኖ ዱቄት በኩንታል እስከ 13,000 ብር የነበረው ወደ 9,000 ብር ወርዷል (እንደየጥራቱ)።

ነጭ ጤፍ ከአንድ ወር በፊት 13,000 ብር እንደገዙ አሁን ግን 3,000 ብር ቀንሶ በ10,000 ብር እንደገዙ ገልፀዋል፤ ከዚህም ይቀንሳል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ሰርገኛ ጤፍ ፣ ቀይ ጤፍ ላይም መቀነስ እንዳሳየ አስረድተዋል።

በሩዝ ፣ በመኮሮኒ ዋጋዎች ላይም ከፍተኛ የሆነ ቅናሽ መመዝገቡን እኚሁ ሸማች ለሬድዮው ተናግረዋል።

#በአስቸኳይ መሰረታዊ አገልግሎቶችን በመክፈት ህዝቡ የመግዛት አቅም እንዲኖረው ቢደረግ ጥሩ መሆኑን የገለፁት ሸማቹ የመሰረታዊ አገልግሎት መከፈት ፣ የንግድ ቀጠናዎች ትራንስፖርት ቢከፈት አሁን ካለው ዋጋም እንዲቀንስና ገበያው  እንደሚረጋጋ ገልፀዋል።

መሀመድ ካህሳይ የተባሉ ነጋዴ ለሬድዮው በሰጡት ቃል ፥ " ሰላምን ምንም የሚወዳደረው ነገር የለም ፤ ጥፋት ጥፋት ነው ሁልጊዜ ሰላም ግን ሰላም ነው ፤ አሁን ሰላም ከተጀመረ ጀምሮ 5 ሊትር ዘይት 2,100 የነበረው በአንድ ጊዜ ወደ 1,500 እና 1,450 ብር ገብቷል።

የበለጠ መኪና/ትራንስፖርት ሲከፈት ባንኩ ሲከፈት በጣም ቆንጆ ነገር ይሆናል ።

ባንክ ሳይከፈት ዋጋው እንደዚህ የሆነ ባንክን ጨምሮ መሰረታዊ ነገር ሲከፈት ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል በጣም ደስ ይላል። ስኳርም አንድ ኪሎ 270 የነበረ 160 ገብቷል በጣም ደስ ይላል።

መድሃኒትም ይሁን ጥራጥሬ ከመጣ ሁሉም ነገር ወደቦታው እየተስተካከለ ይመጣል ሱቁም ይሞላል ፣ ትራንስፖርትም 24 ሰዓት የሚሰራ ከሆነ በጣም ቆንጆ ነው።

መንግሥት ቶሎ ብሎ አስተካክሎ ካደረገው በጣም ደስ ይለናል። "

በመቐለ ገበያ ፤ ከሳምንት በፊት 2,700 ብር ሲሸጥ የነበረ የ25 ኪሎግራም መኮሮኒ አሁን 1800 ብር እየተሸጠ ነው። አንድ ፓስታ ከ130 ብር ወደ 60 ብር ቀንሷል። 1 ኪሎ ኦቾሎኒ ከ370 ብር ወደ 160 ብር ቀንሷል። ሽኩርት ፣ ቲማቲም ፣ ድንች ዋጋ ላይ ለውጥ የለም።

Credit : ጋዜጠኛ ሙልጌታ አፅብሃ (ቪኦኤ ፌድዮ)
የፅሁፍ ዝግጅት ፦ Tikvah Family

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray , #Mekelle የፕሪቶሪያውን #የሰላም_ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ በምግብ እና ሸቀጦች ላይ ቅናሽ እየታየ መሆኑን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል። የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ስለታየው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ቅናሽ በ " ቀዳማይ ወያነ ገበያ " ያሉ ነጋዴዎች እና ሸማቾች ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥተዋል። አለቃ አረጋዊ ጨርቆስ የተባሉ ነጋዴ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፦ - ሰርገኛ…
#Tigray , #Mekelle

የፕሪቶሪያውን #የሰላም_ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ በምግብ እና ሸቀጦች ላይ የታየው ቅናሽ (በቀዳማይ ወያነ ገበያ) ፦

- ሰርገኛ ጤፍ 11,000 ብር ይሸጥ የነበረው አሁን ከ6,000 እስከ 6,500 እየተሸጠ ነው።

- ነጭ ጤፍ 14,000 እስከ 13,500 ይሸጥ የነበረው አሁን 10,000 ብር እየተሸጠ ነው።

- የስንዴ ዋጋ በኩንታል ከ10 ሺህ ብር ወደ 7 ሺህ ብር ቀንሷል።

- ለአንድ ኪሎ ግራም 700 ብር የነበረው በርበሬ አሁን 500 ብር ገብቷል።

- ዘይት 1,700 እና 1,800 የነበረው ወደ 1,400 ቀንሷል። 5 ሊትር ዘይት 2,100 የነበረው በአንድ ጊዜ ወደ 1,500 እና 1,450 ብር ገብቷል።

- ፉርኖ ዱቄት በኩንታል እስከ 13,000 ብር የነበረው ወደ 9,000 ብር ወርዷል (እንደ የጥራቱ)።

- ስኳር አንድ ኪሎ 270 የነበረ 160 ገብቷል።

- 25 ኪሎግራም መኮሮኒ 2,700 ብር ሲሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን 1,800 ብር እየተሸጠ ነው።

- አንድ ፓስታ ከ130 ብር ወደ 60 ብር ቀንሷል።

- አንድ ኪሎ ኦቾሎኒ ከ370 ብር ወደ 160 ብር ቀንሷል።

(ሽኩርት ፣ ቲማቲም ፣ ድንች ዋጋ ላይ ለውጥ የለም።)

@tikvahethiopia
#Tigray

ህወሓት ፤ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ባወጣው መግለጫ " አምባገነን " ሲል የጠራቸው የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይ ዘግናኝ ግፍ እየፈፀሙ ነው ብሏል።

በአጠቃላይ የኤርትራ ጦር በደቡብ አፍሪካ የጦርነት ማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም በትግራይ እና በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን #ሁሉን_አቀፍ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ከሷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት #ኃላፊነቱን_እንዲወጣ ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይና በህዝቡ ላይ እየፈጸመው ያለውን ግፍ እና በደል በአስቸኳይ እንዲያስቆም እንዲያደርግ ፤ ከትግራይ እንዲወጣ እንዲያስገድዱ ፤ ሲፈጽመው ለነበረው ወንጀል #ተጠያቂ እንዲሆን እንዲያደርጉ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

" ህወሓት " በዛሬው መግለጫው ያነሳቸው ነጥቦች ምንድናቸው ?

- በተፈረመው #የሰላም_ስምምነት መሰረት ጦርነት እንዲቆም ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት እንዲከበር፣ የኤርትራና ሌሎችም ሃይሎች ከትግራይ እንዲወጡ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብሏል።

- ህወሓት ፤ " አምባገነን " ሲል የጠራቸው የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፤ በሰላም ስምምነቱ #እንዳልተደሰቱ ገልጾ ፤ " ወታደሮቹን ያስወጣል ተብሎ ቢጠበቅም ተጨማሪ ክፍሎችን (ኃይሎቹ) ወደ ትግራይ እያመጣ ነው " ብሏል። ይኸው ጦር በህዝባችን ላይ አሰቃቂ ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል ሲል ገልጿል።

- የኤርትራ ጦር በሴቶቻችን ላይ ጾታን መሰረት ያደረገ እጅግ አረመኔያዊ ጥቃት እየፈፀመ ፤ ንፁሀን ዜጎችን እየጨፈጨፈ ፣ የህዝብና የግል ንብረት እየዘረፈ ወደ ኤርትራ እያጓጓዘ ፤ የተረፈውን ደግሞ #እያጠፋ እና እያቃጠለ ነው ፤ የትግራይ ቅርሶችም በከፍተኛ ደረጃ እየወደሙና እየተዘረፉ ነው ፤ በአጠቃላይ የኤርትራ ጦር በደቡብ አፍሪካ (ፕሪቶሪያ) የጦርነት ማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላም በትግራይ እና በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ሁሉን አቀፍ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል።

- ህወሓት የኢትዮጵያ መንግሥት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ፤ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ኢሳያስ አፈወርቂ በትግራይ እና በሕዝቡ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ እና በደል #በአስቸኳይ_እንዲያስቆም ፤ ከትግራይ እንዲወጣም እንዲያስገድደው እንዲሁም በትግራይ ሲፈጽመው ለነበረው ወንጀል ሁሉ ተጠያቂ እንዲሆን ማደረግ አለበት ብሏል።

- ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም አፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ፣ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት በኢሳያስ አፈወርቂ " አምባገነን " ስርዓት ላይ ትክክለኛ ማዕቀብ እንዲጥልና ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል።

ይህንን የህወሓት ክስ በተመለከተ ከ "ኤርትራ" በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ጦርነት እንዲያበቃ ፤ ያሉት ችግሮችም #በሰላም እንዲፈቱ ፤ የሰብዓዊ ድጋፍ ያለገደብ ለተቸገሩት ዜጎች ሁሉ እንዲደርስ ፤ መሰረታዊ አገልግሎቶች ስራ እንዲጀምሩ ለማድረግ በደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ (የስምምነቱ ማስፈፀሚያ ላይ) ስምምነት መፈረማቸው አይዘነጋም።

በናይሮቢ ስምምነት በትግራይ ክልል ያሉ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት የውጭ ኃይሎችን እና ከኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ኃይሎችን ሁሉ ከክልሉ (ከትግራይ ክልል) ከማስወጣት ጋር #አብሮ እንደሚከናወን መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

በፕሪቶሪያ የተፈረመው #የሰላም_ስምምነት ለዘላቂ ሰላም አስተዋፅኦ ያደርጋል ? ወይስ አያደርግም ? በሚሉት ነጥቦች ክርክር እና ውይይት እንዲደረግ ከ #USAID በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ " ሀበጋር " (የደበበ ኃ/ገብርኤል የህግ ክርክር ፕሮግራም) ባለፈው ቅዳሜ አንድ የውይይት እና ክርክር መድረክ ተዘጋጅቶ ነበር።

በመድረኩ ላይ የተጋበዙ ምሁራን ፣ የሕግና የፖለቲካ ባለሙያዎች ፣ የፖለቲካ ፖርቲዎች በየፊናቸው ሀሳብ ሲሰጡ ፤ የተለያዩ ጥያቄዎችንም ሲሰነዝሩ ተስተውለዋል።

የታሪክ ምሁር እና የቀድም #የአብን ብሔራዊ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም (ዶ/ር) የፕሪቶሪያው ስምምነት " #ዘላቂ ሰላምን አያመጣም " በማለት፣ እንዲሁም የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አበበ ገ/ህይወት " ስምምነቱ ዘላቂ ሰላም ያመጣል " በማለት ክርክር አድርገዋል።

በአንድ ወገን ያሉት ተሳታፊዎች ስምምነቱ ከነችግሩም ቢሆን ዘላቂ ሰላም ያመጣል፣ በሌላ ወገን ደግሞ ስምምነቱ አሳታፊና ግልፅኝት፣ ተጠያቂነት መርሆችን ካላሟላ ዘላቂ የሆነ ሰላም ሊመያመጣ አይችልም ፣ ቀድሞውንም አሳታፊነት እና ግልጸኝነት የጎደለው ነው በማለት ሀሳባቸውን አቅርበዋል።

በመድረኩ ፦

- የፕሪቶሪያው ስምምነት ዘላቂ ሰላም ያመጣል ? አያመጣም ?
- የተፈናቃዮች ጉዳይ
- የራያ እና ወልቃይት ጉዳይ ተነስተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ክርክርና ውይይት መድረኩ የተሳተፉ አካላትም አነጋግሯል።

ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-19