TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሀዋሳ-ዶ/ር ዐብይ⬇️

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2011 የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ፍጹም #ሰላማዊና ውጤታማ እንዲሆን በሚቻልበት ሁኔታ ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንቶች እና ከክልል አመራሮች ጋር #መወያየታቸው ተገለፀ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃዋሳ ከተማ እየተካሄደ ከሚገኘው የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ጎን ለጎን በትናት ምሽት ከአመራሮቹ ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በዚህ ወቅት የትምህርት ዘመኑ ሰላማዊና ውጤታማ እንዲሆን የተማሪዎች፣ ወላጆች፣ መምህራን፣ የትምህርት ማህበረሰብ አባላት፣ የክልል አመራሮችና #የጸጥታ አካላት ኃላፊነት እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት #ከጥቅምት የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ ተማሪዎችን በመቀበል የመማር ማስተማር ሥራ እንደሚጀምሩ የትምህርት ሚኒስትር ማስታወቁ #የሚታወስ ነው።

በዘንድሮ አመት ከ149 ሺህ በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎች #ዩኒቨርስቲዎች በሚያወጡት መርሃግብር መሠረት ጥሪ እንደሚደረግላቸው ተነግሯል።

ምንጭ፦ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ከፍተኛ ጫና እያሳደረብን ነው "

የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው ምደባ የሚጠባበቁ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ምደባው እንዲፋጠንለቸው በድጋሚ ጠይቀዋል።

የመጀመሪያውን ዙር ፈተና ተፈትነው እና ውጤታቸውን አውቀው ቤታቸው የተቀመጡ ተማሪዎች 6ኛ ወራቸውን ሊደፍኑ እየተቃረቡ ይገኛሉ።

እስካሁን ምደባ ይፋ የሚሆንበት ቀን ይፋ ያልተደረገ ሲሆን ይህ ሁኔታ ተማሪዎችና ወላጆችን ጫና ውስጥ እየከተተ ነው።

መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የሆኑ አንድ ወላጅ ልጃቸው ብሄራዊ ፈተና ወስዳ ወራት ቢቆጠሩም እስካሁን የምትማርበትን ተቋም ባለማወቋ ጫና እየደረሰባት፤ በግል እንኳን ለማስተማር ውሳኔ ላይ ለመድረስ እንደተቸገሩ፤ አመቱም እየተጠናቀቀ በመሆኑ ከእሷም አልፎ ቤተሰብ ላይ ጫናው እየበረታ መምጣቱን ገልፀዋል።

ከትምህርት እንዳትርቅ ጥረት እያደረጉ መሆኑ የገለፁት ወላጅ ፤ ነገር ግን ከመደበኛው ትምህርት ስርዓት ተማሪ መነጠሉ የሚያሳድረው ጫና ከባድ ነው ብለዋል።

መንግስት የሚስተካከሉ እና የቀረቡ ቅሬታዎች ካሉ በፍጥነት አስተካክሎ እና መፍትሄ ሰጥቶ ተማሪዎችን በፍጥነት ምደባቸውን እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል።

ሌሎች መልዕክታቸውን የላኩ የቤተሰቡ አባላት ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ውጭ ሆነው የሚያሳልፉት ጊዜ ከፍተኛ የስነልቦና ጫና ውስጥ እየጣላቸው በመሆን መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከጥቂት ቀናት በፊት ምደባን በተመለከተ ለቲክቫህ በላከው መልዕክት ትንሽ እንዲታገሱ መልዕክት ማስተላለፉ ይታወሳል።

የ2013 ዓ/ም ፈተና የመጀመሪያ ዙር #ከጥቅምት 28/2014 ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ቀናት የ2ኛው ዙር ፈተና #ከጥር 24 ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀን መሰጠቱትና ውጤትን ጨምሮ መቁረጫ ነጥብ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

@tikvahethiopia