TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቤንሻንጉል⬇️

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በአጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች #የጸጥታ ችግር መከሰቱ ተገለጸ።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሺ ዞንና በአጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች በተከሰተው የጸጥታ ችግር በሰዎች ሕይወትና በንብረት ላይ #ጉዳት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ገልጿል፡፡

አሁን ለተከሰተው የጸጥታ ችግር መስከረም 16 ቀን 2011 ዓ.ም በኦነግ ስም የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች በምዕራብ ወለጋ ዞን ቢላ አሙማ አገሎ በተባለው ስፍራ በቤንሻንጉል ጉሙዝ የከማሺ ዞን አመራሮች ላይ ባደረሱት ጥቃት 4 የከማሺ ዞን አመራሮች #መገደላቸውን ተከትሎ መሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡

በእነዚህ ታጣቂዎች ግድያ የተፈጸመባቸው የከማሺ ዞን አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል ከተላኩ አመራሮች ጋር ከዚህ ቀደም ከክልሉ #ተፈናቅለው የነበሩ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ወደነበሩበት #በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ በአሶሳ ከተማ ተወያይተው ወደ ከማሺ ዞን በመመለስ ላይ እያሉ ነበር ተብሏል፡፡

በከማሺ ዞንና እንዲሁም በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ዞን ስር በሚገኙት የሳስጋ፣ ድጋ፣ ሐሮ ሊሙ፣ ሊሙ፣ ቦጂ ብርመጂ ወረዳዎችና በሌሎች አከባቢዎች በተከሰተው በዚህ ግጭት ከነቀምቴ ሆስፒታል በተገኘው መረጃ መሰረት እስከ አሁን የ5 ሰዎች ሕይወት አልፏል፣ በርካቶች ቆስለዋል፣ በንብረት ላይም ውድመት ደርሷል፡፡

በተከሰተው ችግር ሳቢያ በቤንሻንጉል ክልል ሲኖሩ የነበሩ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ተፈናቅለው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ወሰን አካባቢ ወደሚገኙት የኦሮሚያ ወረዳዎችና ወደ ነቀምቴ ከተማ መሰደዳቸውንም ቢሮው ገልጿል፡፡

በአከባቢው የተከሰተውን ችግር #ለማረጋጋት የጸጥታ ኃይሎችና የአስተዳደር አካላት፣ የፌዴራል መንግስትና ሁለቱ ክልሎች በቅንጅት እየሰሩ መሆኑንም የኮሙኒኬሽን ቢሮው ገልጿል፡፡

በዜጎች ላይ ለደረሰው ጉዳት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ #ሀዘን ገልጿል፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላላም ጃለታ በበኩላቸው፣ በአከባቢው የጸጥታ ችግር መከሰቱን አምነው፣ በከማሺ ዞን የሚገኙት ነዋሪዎች ጥቃት ይደርስብናል በሚል ፍርሃት የጉሙዝ ተወላጆች ቤታቸውንና ንብረታቸውን ትተው ወደ ጫካ #እየተሰደዱ ሲሆን፤ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ደግሞ ወደ አጎራባች የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች እየተሰደዱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በተፈጠረው ችግር በርካታ የኦሮሞ ማህበረሰብና የጉሙዝ ተወላጆች ቤቶች ላይ ቃጠሎ ደርሷል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia