TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLiaTadesse

የውጭ አገራት የጉዞ ታሪክ ሳይኖራቸው የኮሮና ቫይረስ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር #እየጨመረ መሆኑ ተጠቆመ!

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ #ለኢዜአ እንደተናገሩት ፤ ኅብረተሰቡ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር "አነስተኛ ነው" በማለት እየተዘናጋ ነው።

የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸውና ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ሳይኖራቸው በቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ መዘናጋት አይገባም ብለዋል።

በጎረቤት አገራት በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ሆኑንም ገልጸው ይህም ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል።

ሳይንሳዊ ምርምሮችም የቫይረሱ ስርጭት ሊጨምር እንደሚችል እያሳዩ መሆኑን ጠቁመው ኅብረተሰቡ ሳይዘናጋ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ምክራቸውን ለግሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrDerejeDuguma

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ኪት ከአንድ ወር በኋላ ማምረት እንደሚጀመር #ለኢዜአ አስታውቀዋል።

ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ከአንድ ወር በኋላ ከቻይና መንግሥት ጋር በመተባበር የመመርመሪያ ኪት ለማምረት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለእዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ድጋፉን ከምታደርገው የቻይና መንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ እየመከሩ መሆኑን ገልጸዋል።

'የመመርመሪያ ኪቱን ሀገር ውስጥ ማምረት ሲጀመር ከውጭ የሚገባውን ኪት ሙሉ በሙሉ ያስቀራል' ያሉት ዶክተር ደረጀ ፣ ምርቱ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንደሚዳረስ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት እጅግ ዘመናዊ የኤርባስ ኤ 350 አውሮፕላኖችን መረከቡን አሳውቋል። ይህንን በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ያስተላለፉት መልዕክት ከላይ ተያይዟል። በነገራች ላይ አየር መንገዱ ከኤር ባስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር አዳዲሶቹ አውሮፕላኖች ጭኖ ያመጣውን የእርዳታ እቃዎች ለጤና ጥበቃ…
#EthiopianAirlines

አቶ ተወልደ ገብረማርያም አየር መንገዱ ያስገባቸው ኤርባስ ኤ-350 አውሮፕላኖች የገበያ ተወዳዳሪነቱን ይጨምራል ሲሉ ተናገረዋል።

አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ፥ አዲስ የገቡት አውሮፕላኖች አየር መንገዱ ከዚህ በፊት ከነበረው ተመሳሳይ አውሮፕላኖች ጋር ሲነጻጸሩ ዘመናዊና የተሻሉ ናቸው ብለዋል።

"አውሮፕላኖቹ አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ዘርፍ የተሻለ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስችሉታል" ሲሉም ገልፀዋል።

አዳዲሶቹ አውሮፕላኖች ኮቪድ-19 ወረርሽኝን በመከላከል የተሻለ ሥራ ለመስራት እንደሚያግዙ አቶ ተወልደ #ለኢዜአ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትላንት ለሊት 8 ሰዓት የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 6 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ የተሽከርካሪ አደጋ በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ደርሷል።

በአደጋው በሁለት የቤተሰብ አባላት ላይም ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በመርጦ ለማርያም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።

የዞኑ ፖሊስ የሟቾች አስከሬን ለየቤተሰባቸው ለመላክ ዝግጅት ላይ እንደሆነ #ለኢዜአ አሳውቋል።

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአዲስ አበባ የሚኖሩ እንደሆኑ ተገልጿል።

ከደቡብ ወሎ ዞን መከነ ሰላም ከተማ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2-78171 አዲስ አበባ የሆነ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከመንገድ ወጥቶ በመገልበጡ ነው አደጋው የደረሰው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሀዋሳ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ ፦ በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር በመሀል ከተማ ክፍለከተማ በአዲስ አበባ ቀበሌ በተለምዶ ቤተሰብ መምሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። የሐዋሳ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ደረሰ ቡሳሮ የአደጋው መንስኤና የደረሰው የንብረት ውድመት በምርመራ ሂደት ላይ መሆኑን ገልፀዋል። ኮማንደር ደረሰ በአካባቢው ህብረተሰብ…
ትላንት ለሊት በሀዋሳ የደረሰው የእሳት አደጋ ፦

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ደረሰ ቡሳሮ #ለኢዜአ በሰጡት ተጨማሪ መረጃ ቃጠሎው የደረሰው ትላንት ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ ነው።

ኮማንደር ደርሰ የነበረው ቃጠሎው መጠነ ሰፊ ስለነበር በፍጥነት መቆጣጠር አልተቻለም ብለዋል። እሳቱን ለመቆጣጠር ከሶስት (3) ሰዓት በላይ ፈጅቷል።

በእሳት አደጋው በሰው ላይ ጉዳት አልደረሰም።

አጠቃላይ የወደመው ንብረት ለጊዜው ባይታወቅም እስካሁን ባለው መረጃ ፦

- አራት ባጃጅ፣
- አንድ ዶልፊን ተሽከርካሪ፣
- አምስት የንግድ ሱቆች፣
- ሜሪ ጆይ የአረጋዊያን ማዕከል ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትናንት ሌሊት በአዲስ አበባ በ4 የተለያዩ አካባቢዎች የእሳት አደጋ ደርሷል።

በደረሰው የእሳት አደጋ ከ7 ሚሊየን 550 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን #ለኢዜአ አስታውቋል።

በተደረገው መከላከል 67 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ንብረት ማትረፍ መቻሉ ተገልጿል።

የእሳት አደጋው የተከሰተው በአቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተሞች እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ በሁለት የተለያዩ አካባቢዎች ነው።

አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 "መልካ ሸኔ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከምሽቱ 12 ሰዓት ከ50 ገደማ በከብቶች በረትና በ7 አባወራ ቤቶች ላይ ቃጠሎ ደርሶ ውድመት አስከትሏል።

በአደጋው 9 ላሞችና ሁለት ጥጆች ሞተዋል።

ምክንያት ?

አባወራዎቹ የወይራ ጭስ ለማጠን በተያያዘ እሳት መሆኑ ታውቋል።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 7 ሰዓት ላይ ጀመስጂድ ቅጥር ግቢ በሚገኝ መጋዘን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

ምክንያት ?

ገና ፖሊስ እያጣራው ነው።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው "ስኩል ኦፍ ቱሞሮው" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 6 ሰዓት ገደማ የመኖሪያ ቤት ላይ ቃጠሎ ተከስቷል።

ምክንያት ?

የኤሌክትሪክ ኮንታክት ነው ተብሏል።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት "መለስ ፋውንዴሽን" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሌሊቱ 4 ሰዓት ገደማ በአንድ ማተሚያ ቤት በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ደርሷል።

ምክንያት ?

እስካሁን አልታወቀም።

#ENA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ጥያቄ ምንድነው ? ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ምላሽስ ? • " እንደዚህ ዓይት ውሳኔ ላይ የተደረሰው አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ኃላፊዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው " - የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ፍቅረስላሴ አካሉ (ለአዲስ ስታንዳርድ) • " ማህበራችን የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አላቀረበም " - ዶ/ር በፍቃዱ ዘለቀ (ለዶቼ…
" የተሰራጨውን የአቋም መግለጫ አላውቀውም " - የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፤ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች ስም የተሰራጨውን አቋም አላውቀውም ብሏል።

ማህበሩ ይህን ያለው #ለኢዜአ በላከው መግለጫ ነው።

ማህበሩ ፤ ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምሀርት ድረስ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎችን በማደራጀት በአምስት ዓላማዎች እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጿል።

ከአምስቱ ዓላማዎች መካከል አንዱ የመምህራን መብትና ጥቅም ማስከበር ነው ያለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲ መምራን ያነሱትን ጥያቄዎች ለትምህርት ሚኒስቴርና ለሚመለክታቸው የፌዴራል መንግስት አካላት እያቀረበ ለመፍትሄው እየሰራ መሆኑን አመልክቷል።

" አንዳንድ ጥያቄዎች በፍጥነት ምላሽ ማግኘት የሚገባቸው መሆኑን " እናምናለን ያለው ማህበሩ " አንዳንዶቹ ደግሞ ጊዜ የሚፈልጉ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል " ብሏል።

ማህበሩ ከሰሞኑን " የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች የአቋም መግለጫ "  በሚል ርዕስ  " ከህዳር 26/2015 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሥራ ማቆም አድማ እናደርጋለን " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ አላውቀውም ብሏል።

እውቅና ያለው የማህበሩ መዋቅር ስም  " የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር "  መሆኑን የገለፀው ማህበሩ ፤ መምህራን ማህበራቸው ጉዳዩን በጥብቅ ይዞ እየሰራ መሆኑን አውቀው የተለመደውን የማስተማር የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት በሙያዊ ኃላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ጥሪውን አቅርቧል።

#ኢዜአ

ማስታወሻ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/74911

@tikvahethiopia