TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የታማኝ በየነ አቀባበል #በሰላም እንዲጠናቀቅ በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ #ጥበቃ እየተደረገ ይገኛል። በተለያዩ ቦታዎችም ፍተሻ እየተደረገ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

ሰሞኑን ወደ መሬት ባንክ እንዲመለሱ ውሳኔ የተላለፈባቸው የአዲስ አበባ ሰፋፊ ቦታዎች ዳግም በሕገ-ወጥ መንገድ እንዳይወረሩ #ጥበቃ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽህፈት ቤት ለቦታዎች ጥበቃ እንዲያደርግ ለደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት በደብዳቤ ትዕዛዝ አስተላልፏል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል...

በሕገ-ወጥ መንገድ #የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የያዙ አካላትን #በማጋለጥ ጥቆማ እንዲሰጥ የከተማው ነዋሪ ጥሪ ቀርቦለታል፡፡ ጥሪውን ያቀረበው የአዲስ አበባ አስተዳደር ቤት ኖሯቸውም የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የወሰዱ ካሉ፣ ነዋሪው እንዲጠቁመው ይፈልጋል፡፡ የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት በፌስቡክ ገጹ እንዳስረዳው፣ ታጥረው የቆዩ የከተማዋን መሬት ወደ መንግስት እንደመለሰው ሁሉ በጋራ መኖሪያ ቤቶችም ላይ ምርመራውን ቀጥሏል፡፡ የቤት ችግር ላለባቸው ነዋሪዎች ታስቦ የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በህገ-ወጥ መንገድ በያዙት ላይ፣ በተደረገው #ፍተሻ የተገኘውን ውጤት እንደሚገለፅም ተጠቁሟል፡፡
እስከዚያው ነዋሪዎች፣ ሰው ሳይገባባቸው የቆዩ፣ በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶችን እንዲጠቁሙ አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬደዋ‼️

በድሬዳዋ የተከሰተውን የጸጥታ መደፍረስ ለመቆጣጠር የመከላከያ ሰራዊት የጸጥታ ማስከበር ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ እንዲረከብ መደረጉን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። በሰሞኑ ሁከት የተጠረጠሩ 200 ሰዎች #በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልጿል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ የመከላከያ ሰራዊት ወደ ድሬዳዋ እንዲገባ የተደረገው ባለፉት ቀናት በከተማይቱ የነበረው ሁኔታ ከአስተዳደሩ እና ከፌደራል ፖሊስ አቅም በላይ ስለነበር ነው።

የመከላከያ ሰራዊት ከተማይቱን ለመቆጣጠር የሚያስችሉትን ኮማንድ ፖስቶች በተለያዩ አካባቢዎች ማቋቁሙንም ጽህፈት ቤቱ ይፋ አድርጓል።

የጀርመን ራድዮ የድሬዳዋ ዘጋቢ #መሳይ_ተክሉ እንደገለጸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከትላንት ምሽት ጀምሮ በከተማይቱ ተሰማርተዋል። በመኪና ላይ ሆነው ከሚዘዋወሩት በተጨማሪ በየአካባቢው በተጠንቀቅ ቆመው የሚታዩ እንዳሉ ዘጋቢው ተናግሯል። የሰራዊቱ አባላት ለአደጋ ይጋለጣሉ ለተባሉ የመንግስት ተቋማት እና ድርጅቶችም #ጥበቃ እያደረጉ ነው ብሏል።

በከተማይቱ ያለው ዘጋቢያችን የመንግስት ወታደሮቹ ህገወጥ እንቅስቃሴዎች በሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ በድምጽ ማጉያ ሲያስጠንቅቁ ተመልክቷል። በድሬዳዋ ሰሞኑን ሲደረጉ የነበሩ የህዝቡን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ከሚያውኩ ድርጊቶች እንዲታቀቡም ተቃዋሚዎችን ሲያስቡም ታዝቧል።

በድሬዳዋ ላለፉት ሶስት ቀናት ተቃውሟቸውን ለማሰማት አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች ጎማዎች በማቃጠል እና ድንጋይ በመደርደር መንገዶችን ዘግተው ነበር። በዛሬው ዕለት በከተማይቱ እንቅስቃሴዎች እንደሚታዩ የገለጸው ዘጋቢያችን መንገዶች መከፈታቸውን እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ ስራ መመለሳቸውን ተናግሯል።

በድሬዳዋ ከሰሞኑ በተከሰተው ሁከት ምክንያት በሰው እና በንብረት ላይ ስለደረሰው ጉዳት የተጠየቁት የከተማይቱ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እና ፖሊስ “የተደራጀ መረጃ የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ምንጭ:- DW AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአ/አ የሁለት ሰው ህይወት አለፈ!

አዲስ አበባ በፌደራል ፖሊስ አባላት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ። የፌደራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጀይላን አብዲ እንደነገሩን ከሆነ ዛሬ ረፋድ ላይ በፌደራል ፖሊስ ከሚጠበቁ ተቋማት መካከል አንዱ በሆነው የፌደራል ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ግቢ ውስጥ በተፈጠረ አለመግባባት የ2 ሰው ህይወት አልፏል።

ክስተቱ የተፈጠረው ኤጀንሲውን ከሚጠብቁ የፖሊስ አባላት መካከል አንዱ ለተመሳሳይ #ጥበቃ ስራ ወደ ሌላ ተቋም መቀየሩ የተነገረው የፌደራል ፖሊስ አባል እና በሃላፊው የተሰጠውን ትዕዛዝ ባለመቀበል ምክንያት የተጀመረ ውይይት ወደ አለመግባባት አምርቶ ፖሊሱ የስራ ሃላፊውንና በስራ ላይ በነበረ አንድ አባል ላይ ግድያ መፈጸሙ ተገልጿል። ድርጊቱን የፈጸመው የፌደራል ፖሊስ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን አቶ ጄይላን ተናግረዋል።

Via #ኢትዮኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
" ... አሽከርካሪ እየተንገላታ ነው። እንደድሮው 24 ሰዓት ተንቀሳቅሶ ሥራ መሥራት አልቻለም " - አቶ ዳመነ ተሾመ

ከጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ. ም ጀምሮ እስካሁን ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከአዳማ እስከ መተሃራ ባለው አውራ ጎዳና የሚንቀሳቀሱ 5 የአገር አቋራጭ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ታግተው ተወስደው 3ቱ #በሕይወት_እንዳልተገኙ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማሕበር አመራር አባል አቶ ዳመነ ተሾመ ለዶቼ ቬለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ " ታግተው ጫካ ከተወሰዱት 5 ሹፌሮች መካከል ገንዘብ ከፍለው የወጡ አሉ " ብለዋል።

አቶ ዳመነ ፤ ይህንን እገታ የፈፀሙትን አካላት ማንነት እንዳላወቁትና መንግሥትም የደረሰበት እንደማይመስላቸው ተናግረዋል።

" በኮሪደሩ ላይ ከፍተኛ ችግር እየተፈጠረ ነው። አሽከርካሪ እየተንገላታ ነው። እንደድሮው 24 ሰዓት ተንቀሳቅሶ ሥራ መሥራት አልቻለም " ብለዋል።

ማሕበራቸው ከኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ኤጀንሲ እና ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌደሬሽን ጋር ትናንት በችግሩ እና መፍትሔዎች ዙሪያ መወያየቱን ገልፀው ፤ " የሾፌሮች መታገት እና መንገላታት ይቁም። እኛ የአበል፣ የደሞዝ ጥያቄ ሳይሆን መንግሥት #ከለላ እና #ጥበቃ ያድርግልን የሚለውን ሀሳብ አንሸራሽረናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በዋናነት ከአዳማ እስከ መተሃራ በምእራብ ወለጋ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ችግር ውስጥ እንደሆኑ የጠቆሙት አቶ ዳመነ አሽከርካሪዎቻችን ወደ ቤታቸው ለመግባት በየመንገዱ ችግር እየተፈጠረባቸው ወደ 21 ቀናቶችን ፈጅቶባቸዋል " በማለት የሚገጥማቸው ችግር ምን ያህል አሳሳቢ እየሆነ እንደመጣ አስገንዝበዋል።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ ሬድዮ

@tikvahethiopia