TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለሰራተኞቹ #ደሞዝ መክፈል አልቻለም‼️

(ተክለብርሀን አምባዬ ኮንስትራክሽን)

በሀገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ የግንባታ ተቋራጮች መካከል አውራየሆነው ተክለ ብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን በስሩ ከ1 ሺህ በላይ ጊዜያዊ እና ቋሚ ሰራተኞችን ይዞ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመውሰድ #ሲሰራ ቆየታል፡፡ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ የሚተመኑ ስራዎችን በመሠራት የዘለቀው የግንባታ ድርጀቱ ከኢትዮጵያ ውጪም በሶማሊላንድ አውሮፕላን ማረያፊ እስከ መገንባት የደረሰ ሲሆን በዩጋንዳም በሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ሃሳብ ነበረው፡፡

ነገር ግን የዚህ በጀት አመት ከጀመረበት ከሰኔ 2010 ጀምሮ ለኩባንያው ጥሩ ግዜ እንዳልሆነ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ቀዳሚው ነገር የአቢይ አህመድ አስተዳደር በዚህ አመት አዳዲስ ፕሮጀክትን ለመገንባት ስራዎች ከመጀመር ይልቅ #ሳይጠናቀቁ የተጓተቱትን መጨረስ ላይ ማተኮሩ መሆኑን ያስቀምጣሉ፡፡ ቀድሞም ቢሆን የመንግስትን አጠቃላይ በጀት ቀመር እና የአመቱን ትኩረት በመለየት የግንበታው ዘርፍ ላይ በየአመቱ ዝግጅት ለሚያደርጉት የግንባታ ተቋራጭ ድርጅቶች ይህ የመንግስት ውሳኔ ስራቸው በእጅጉ #እንዲቀዛቀዝ ያደረገ ሆኗል።

በአንድ የግንባታ ድርጅት ውስጥ በፕሮጀክት አዋጭነት ላይ የሚሰራ ባለሙያ ሀሳቡን ለዋዜማ ሲናገር የእሱን ድርጅት ጨምሮ አብዛኞቹ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ተቋራጮች የአመቱን የስራ ትኩረት የሚለዩት መንግስት ከፍተኛውን ወጪ የመደበበትን ዘርፍ ቀድሞ በመለየት መሆኑን ያስታውሳል፡፡ ዘንድሮ ግን አዲስ የግንባታ ፕሮጅክቶች ላይ መንግስት የተከተለው አቅጣጫ ለዘርፉ ተዋናዮች መልካም ዜና አይደለም።

በግንባታው ዘርፍ ቀዳሚ ስም ካላቸው ተቃራጮች መካከል ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን አውራ ነው፡፡ የድርጅቱ ሰራተኞች እንደነገሩን ደሞዝ ከተከፈላቸው 6 ወራት ተቆጥሯል። የዋዜማ ራድዮ ምንጮች እንደሚሉት ለቋሚ ሰራተኞቹ ያቀረበው “ለጥቂት ግዜ ታገሱኝ” ተማጽኖን በመቀበል አብዛኞቹ ሰራተኞች ቢቆዩም ጠዋት ገብተው ማታ ከመውጣት የዘለለ ስራ እየሰሩ አይደለም፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ ተክለ ብርሃን አምባይ ለረጅም ግዜ ሳይከፍል የቆየውን ግብር ከ68 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ በቅርቡ እንዲከፍል መደረጉም ድርጅቱን ለተጨማሪ የፋይናንስ ጫና እንደዳረገው የዋዜማ ምንጮች ይናገራሉ፡፡

በሀገሪቱ ውስጥ በኢንቨስትመንት በስፋት ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች መካከል የባንክ እዳ ጫና ካለባቸው ድርጅቶች ውስጥ ተክለብርሃን አምባዬ ከቀዳሚዎቹ ተርታ እንደሚሰለፍ ዋዜማ መረጃውን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምንጮቿ አረጋግጣለች፡፡ የሬድዮ ጣቢያው ምንጮች እንደሚሉት ድርጅቱ በእጁ የሚገኘው ሀብትና በባንክ ያለበት የእዳ ጫናም ተመጣጣኝ አይደለም፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ያለ ስራ #ደሞዝ እየወሰዱ ነውና፤ እኛ መንግስትም እንዲጠቀም ተገልጋዩ ህብረተሰብም ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ ለቅሬታችን ሰሚ ጆሮ እንፈልጋለን" ቅሬታ አቅራቢዎች
.
.
ከሐምሌ 1 ጀምሮ ስራ ላይ በዋለው አዲሱ የሰራተኞች ድልድል በጉለሌ ክፍለ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ቅሬታ አቅርበዋል ተብሏል፡፡ ሰራተኞቹ ድልድሉ ከመመሪያ ውጭ በትውውቅና በኔትወርክ ሆኗል ይላሉ፡፡ ከዚህ ቀደም #አለቆቻችን የሚሰሩትን #አድሏዊ አሰራር ስንቃወም ስለነበር ከቦታው ገለል ለማድረግ ተጠቅመውበታል ይላሉ፡፡ ክፍለ ከተማው በበኩሉ በጥንቃቄ የከወንኩት ስራ ነው፣ ችግሮች ካሉም ለማስተካከል በሬ ክፍት ነው ብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia