TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከጋምቤላ⬆️

"ፀግሽ ጋምቤላ ሰሞኑን የነበረው #ረብሻ ዛሬ #ተረጋግቶ የመስቀል በዓል እንዲህ #በደመቀ ሁኔታ ሁሉም የከተማው ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እና የክልሉ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በተገኙበት ያለምንም ችግር #በሰላም ተከብርዋል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ‼️

ማሳሰቢያ፦

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2011 ዓ.ም የመደበኛ ተማሪዎች ቅበላ ከጥቅምት 10 እስከ 14/2011 ዓ.ም ድረስ ማካሄዱ ይታወሳል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የምዝገባ ስርዓቱን አጠናቆ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ የገባ ሲሆን ለሠላማዊ የመማር ማስተማር መስፈን ከውጫዊና ውስጣዊ ባለድረሻ አካላት ጋር በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡

ነገር ግን ዩኒቨርሲቲው በሚገኝበት አካባቢ ምንም አይነት የፀጥታ እና የደህንነት ስጋት ሳይኖር ተማሪዎችን ሆን ብሎ ለማወክና በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ #ረብሻ እንደተከሰተ ተደርጎ በማህበራዊ ድረ ገፅ #እየተወራ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ይህ መሰረተ ቢስ #ወሬ እንደ ሆነ ታውቆ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች አንዳች #ስጋት እንዳይገባቸሁ ተቋሙ #ያሳስባል፡፡

መደበኛ የመማር ማስተማር ስራው ሳይስተጓጎል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ባለድርሻ አካላት የተለመደ ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እና አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው ያሳስባል፡፡

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
ጥቅምት 23/2011 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ‼️

አሶሳ ዩኒቨርሲቲን ወደ ቀድሞ ሰላሙ #ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ካለፈው እሑድ ጀምሮ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሰላማዊ መማር ማስተማሩ ተስተጓጉሏል፡፡ ተማሪዎች እና ተወካይ ፕሬዝዳንቱ እንደነገሩን የግጭቱ መነሻ የሁለት ተማሪዎች አለመግባባት ነው፡፡ ይህም እየተስፋፋ ሄዶ ወደ ቡድን ፀብ ተቀይሮ ነበር፡፡

ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ዶክተር #ሃይማኖት_ዲሳሳ ችግሩን ለመፍታት ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ከተማሪዎች ጋር ምክክር ተደርጎ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በውይይቱም መግባባት ላይ መደረሱ ተማሪዎች አረጋግጠዋል፡፡

ይሁን እንጂ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ትናንት ጠዋት ላይ ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሽ ሲገቡ እንደገና #ረብሻ ተጀምሮ ነበር፡፡

እንደ ተማሪዎቹ መረጃ የግጭቱ ዋነኛ ምክንያት የተማሪዎች መማክርት በወቅቱ አለመመረጥ ኢ-ፍትሐዊ አሠራር ፈጥሯል የሚል ነው፡፡

ተማሪዎቹ ምርጫው ‹‹ባለፈው ዓመት ሰኔ ላይ መካሄድ ነበረበት፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት አልተካሄደም፤ እስካሁን ግን መቆየት አልነበረበትም›› የሚል አቋም አላቸው፡፡

አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ችግሮችን ተወካዮቻቸው በወቅቱ አለመፍታታቸውም ለችግሩ መከሰት ምክንያት መሆኑን ነው ተማሪዎቹ የተናገሩት፡፡

ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ግን ‹‹በውይይቱ ለከፋ ግጭት የሚዳርግ ችግር አላገኘንም›› ነው ያሉት፡፡

በረብሻው ምክንያት ‹‹34 ተማሪዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸውም ይገኛል ብለዋል
ዶክተር ሃይማኖት፡፡

በተከሰተው ግጭት የሶስት ተማሪዎች ህይወት አልፏል፡፡ የጸጥታ ኃይሎች ግቢውን ወደ ቀድሞ ሰላሙ ለመመለስ እየሠሩ መሆናቸውን ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎችም ይህን መመልከታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ይሁን እንጂ ተረጋግተው ለመኖር እና ለመንቀሳቀስም ስጋት ውስጥ መሆናቸውንና ለሰላማቸው #ዋስትና እንደሚፈልጉ ነው የተናገሩት፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሳውላ ከተማ #ረብሻ ሁለት ሰዎች ተገደሉ አምስት ቆሰሉ‼️
.
.
በትናንትናው ዕለት በጋሞ ጎፋ ዞን #ሳውላ_ከተማ በተካሔደ ስብሰባ ላይ በተቀሰቀሰ ኹከት ሁለት ሰዎች #መገደላቸውን እና አምስት መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የሳውላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር #ብስራት_አንበርብር በከተማዋ ሊካሔደ በታቀደው ስብሰባ ላይ የተፈጠረውን ረብሻ ለመቆጣጠር የጸጥታ ኃይሎች በተኮሱት ጥይት ሁለት ሰዎች መገደላቸውን እና አምስት ሰዎች
መቁሰላቸውን ለ«DW» አረጋግጠዋል።

በስብሰው የተካፈሉ አንድ የአይን እማኝ በዞኑ ጉዳይ ላይ ለመመካከር የተጠራውን ስብሰባ "የሚቃወሙ ብዙ ወጣቶች ወጥተው ነበር። መጨረሻ ላይ እኛን ሊወክሉ የማይችሉ ሰዎች ወደ ስብሰባው መምጣት የለባቸውም በሚል ይመስለኛል" ሲሉ የኹከቱን ምንጭ ተናግረዋል። ስብሰባው እንደታቀደው ሳይካሔድ መቋረጡን የተናገሩት የአይን እማኙ የድንጋይ መወራወር ድርጊት መመልከታቸውም ገልጸዋል።

ኮማንደር ብስራት አንበርብር በበኩላቸው "እንግዶችም ወደ አዳራሹ ሊመጡ አልቻሉም። [ወጣቶቹ] ዙሪያውን ከበቡ። እኛ ስንከላከል በድንጋይ መስታወቶችን መስኮቶችን እየመቱ በአጥር ላይ ዘለው ለመግባት ጥረት ሲደረግ ነው የጸጥታው ኃይል በተኩስ አካባቢውን በተኩስ ለማስለቀቅ ጥረት ያደረገው። ሁለት ሰው እዚያ አካባቢ ሞቷል። አምስት የሚሆኑ ሰዎች ቆስለዋል" ሲሉ አስረድተዋል።

ፖሊስ ግጭቱን በማነሳሳት የተጠረጠሩ ያላቸውን 78 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ኮማንደሩ ጨምረው ተናግረዋል። በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የሚገኘው የሳውላ አካባቢ ባለፈው ጥቅምት ወር በዞን ደረጃ እንዲዋቀር ከተነሳ ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተነሳ ግጭት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን DW ዘግቧል።

የክልሉ ምክር ቤት በቅርቡ ባካሔደው መደበኛ ጉባኤ አካባቢው ቀደም ሲል ከነበረበት የጋሞ ጎፋ ዞን በመውጣት ራሱን ችሎ በዞን ደረጃ እንዲዋቀር ወስኗል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ(ሸዋንግዛው-ሀዋሳ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታ ወደ ነገ 09:00 ተላለፈ። ዛሬ ሊደረግ የነበረው ይህ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በሀዋሳ ከተማ ደጋፊዎች መካከል በተከሰተ #ረብሻ ሳይካሄድ ቀርቷል።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia