TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለጥያቄዎቻችሁ መልስ‼️

ዛሬን ጨምሮ ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ጥያቄዎች ቀርበውልኛል፦

"ምንድነው የምትንዘባዘበው መረጃ ከሌለህ ትርኪ ምርኪ ነገር ለምን ትፖስታለህ?"

"ትንንሽ ጉዳዮችን ለምን ትፅፋለህ?"

"አንተ የመንግስት አጨብጫቢ ነህ?"

"አንተ ከዚህ ብሄር ነህ #መሰለኝ ለዚህኛው ታደላለህ..." እና ሌሎችም።

እንዲሁም አስተያየት መሰል ብዙ ስድቦች ይደርሱኛል።
.
.
በመሰረቱ ይህን ቻናል ለህዝብ ጥቅም እና ለመረጃ ልውውጥ የከፈትኩት ነው። ከየትኛውም ወገን ንፁህ ነው። እኔም ከየትኛውም ወገንተኝነት 1000000% ንፁህ ነኝ። እኔ ራሴን የሁሉም ሰው አድርጌ ነው የምቆጥረው። ለሁሉም የሰው ፍጡር እጅግ በጣም ትልቅ ክብር ነው ያለኝ! የኔ መስፈርት ሰው መሆን ላይ ነው። በመሆኑም መረጃዎች ሲላኩልኝ መጀመሪያም መጨረሻም የማየው ከየትኛው ወገን፣ ከየትኛው ብሄር፣ ከየትኛው ሀይማኖት ተከታይ ሰዎች ተላከልኝ ሳይሆን ይህን መረጃ ባሰራጨው ለተከበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ይጠቅመዋል? የሚል ጥያቄ ነው የማነሳው።

በፍፁም ያለአንዳች ግብ እዚህ ገፅ ላይ የሚለጠፈው ፅሁፍ የለም። በተለይ ቻናሉ ለሰላም የሚሰራ ነው። ይህ ማለት ችግር ሲፈጠር ይደብቃል ማለት አይደለም። መረጃዎቹ ሁሉ እንዲመቱልኝ የምፈልገው ግብ አለ። የአያንዳንዱን ከተማ እንቅስቃሴ ሰላም መሆኑን ሰው በሰላም እየተንቀሳቀሰ እለታዊ ተግባሩን መፈፀሙን የሚገልፁ ፅሁፎችን የምለጥፈው መቀለ ሆኖ ስለ ወለጋ፤ ባህር ዳር ሆኖ ስለ ሀዋሳ፤ ሞያሌ ሆኖ ስለ ቤንሻንጉል ጉዳይ መሰማት ስላለበት ነው። ለኛ ስናነባቸው ትንሽ እና ተራ የሚመስሉን ነገሮች ብዙ ሺዎችን በእንቅስቃሴያቸው እንዳገዛቸው በቂ ማረጋገጫ አለኝ።

ይሆነ ቦታ ወጣቶች የሚሰሩትን ጥሩ ስራ ሳቀርብ ሌላውም በነጋታው አስቦት ያድራል። እዚህ ከተማ እንዲህ አይነት ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተከናወነ፣ ተከበረ የምለውም በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ስላለው ነው።

ከዚህ ቀደም የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚያከብሩትን በዓል እንዲሁም የክርስትና እምነት ተከታዮች የሚያከብሩትን በዓላት በየከተማው በየቀበሌው #በሰላም ስለመከበሩ የማበስረው የዚህን ቻናል ግብ ለማሳካት ነው። 😁ብችል የእያንዳንዱን ሰው ሰላማዊ ውሎ ብዘግብ ደስ ይለኛል።

እና ወዳጆቼ በሰላም ተከበረ በሰላም አለቀ የሚሉ ቃላቶች ማደጋገማቸውን እንደትንሽነት እና እንዳላዋቂነት አትቁጠሩት ትልቅ ትልቅ ጥቅም አላቸው።

ሌላው ከናተ የሚመጡት መረጃዎች እውነት ስለመሆናቸው ፈጣሪ ታማኞች አድርጎ ስለፈጠራችሁ አያሳስበኝም።

መረጃዎች #እንደወረዱ የሚቀርቡት በፍፁም የኔ እጅ እንዳይገባበት ነው። መረጃ ስትልኩልኝ ነጥብ አላስተካክልም። የላካችሁትን አቅርባለሁ። ይህ እኔ ምፈነጭበት እና እራሴን ማስተዋውቅበት መድረክ አይደለም። ይሄ የናተ ገፅ ነው! የፃፋችኋትን #ምንም ኢዲት ሳላደርግ ቃል በቃል አቀርባለሁ። ወደፊትም በዚሁ ቀጥላለሁ።

ማጠቃለያው፦ እዚህ ቤት #ትንሽ ጉዳይ የለም! ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩባት ምድር ምንም የማልፈው ነገር የለም። ይህ አቋሜ ነው። ደረጃ እና ጥራት እያሉ መመፃደቅ አይሰራም። ከእናተ ቤት ተነስተን እንስከ ሀገር ድረስ መረጃዎችን እንዳስሳለን። ለማቅራራት እና ዝነኛ ወይም ገንዘብና ስልጣን ባላቸው ሰዎች ለመወደድ አይደለም የምሰራው! እኔም ሆንኩ ቻናሉ ለእያንዳንዱ ጥቃቅን ጉዳይ info እንሰጣለን። ይህን ማድረግ ትንሽነት እና አለማወቅ ከሆነ ትንሽ እና አላዋቂ ሆኜ ልሙት!
.
.
አዎን የተላከ ሁሉ አይቀርብም! መረጃ ሲላክ ለአካባቢው እና ለሌላ ቦታ ይህ ነገር ይጠቅማል?? የሚለውን ጠይቄ ነው። ሌላው በውስጥ በኩል መረጃ የምሰጣቸው አሉ።
.
.
TIKVAH-ETH ለዝና የሚንቀሳቀስ አይደለም! ለሰላም፣ ለፍቅር እና ለተስፋ ነው የሚሰራው።

እዚህ የሰበሰበን ሰውነት ነው፤ ከዛም ኢትዮጵያዊነት! ነፁ ኢትዮጵያዊ ደግሞ እራሱን የሚያውቅ ሁሉንም የሰው ፍጡር እንደራሱ የሚያይና #የሚያከብር ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሴትነት!

#ሴትነት ሰው የመሆን ሁለንተናነት ነው። አንድ ሰው የሴትነትን ታላቅነት ካልተረዳ ገና #ሰው የመሆንን ሚስጢር አልተገነዘበም ማለት ነው። ምክንያቱም ሴት እናት ነች። እናት ደግሞ የማያልቅ ዘላለማዊ ፍቅርን በስስት የምትለግሰን #የፍቅርን ምንነት መገለጫ ናት። ታዲያ ከፍቅርና ፍቅርን ከማወቅ በላይ ምን ታላቅ የህይወት ሚስጢር ይኖራል? ምንም አይኖርም።

ሌላው ታላቅ ከሚያደርጓት ነገሮች ደግሞ በህይወት ውስጥ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተጋፍጣ #በብልሃት እና #አሸናፊነት የምትወጣ ጠንካራ ፍጥረትነቷ ነው።

ሩህሩህነትን ከአፍቃሪነት ጋር ታድላ የተፈጠረች ለወንድ የህይወቱ ማገር እና ምሶሶ ናት። ወንድ ያለ ሴት ሙሉነት እና የህይወት ጣእም የሌለው ያላለቀ የእግዜር ጅምር ስራ ነው።

ሴት ልጅ ስቃይዋን እና ሃዘኗን መደበቅ ካስፈለጋት መከፋትዋን ሳታሳይ ደስተኛ በመምሰል ለምትወደው ሃሴትን መስጠት የምትችል ረቂቅ ፍጠረት ናት።

ሴትነትን ሆነው ካላዩት በእርግጥ ስለ ሴትነት ሙሉ በሙሉ መናገር የሚቻለው አይኖርም። ረቂቅ እና የህይወት ጣእም ሚስጢር አድርጎ ከፈጠራት ፈጣሪ በስተቀር።

ሴት ልጅ ከወንድ የጎን አጠንት ብትሰራም በህይወት ዘመኑ የጀርባ አጥንቱ ሆና ብርታትን እና ፀናትን የምትሰጠው “ሃይል” ናት። የታላላቅ ስኬቱ ጀንበር ሆና የምትፈነጥቅለት ነገር ግን ከእርሱ ልቃ የማትታይ የመድመቂያው ጮራ መፍለቂያ ናት።

ሴት ልጅ ከልብ የመነጨ ክብር ይገባታል። ሴትን የሚያከበር ራሱን #የሚያከብር ነው። ሴትን የማያከብር ቢኖር የህይወትን ጣእም እና ፍቅርን ካለማወቁም በላይ ሰው የመሆን ብቃት የጎደለው ነው።

ምንጭ ፦ ደንቢያ(ከማህበራዊ ድረ ገፅ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia