TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ትግራይ ክልልም የክልሉን ግዛት እና ህዝቡን ለመጠበቅ በቂ የፖሊስ ኃይል፣ በቂ ልዩ ኃይል ፣ በቂ ሚሊሻ ይኖረዋል " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ቅዳሜ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ የሰላም ስምምነት በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት " ህወሓት "ን ትጥቅ ስለማስፈታት እና በትግራይ ክልል ውስጥ ምርጫ ተከናውኖ የክልል መንግስት…
በሰላም ስምምነቱ መሰረት ፦

👉 በኢትዮጵያ ውስጥ #አንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ብቻ ይኖራል።

👉 በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት መሰረት የህወሓት ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መበተን እና ወደ ማኅበረሰቡ መልሶ ለመቀላቀል የሚያስችል ዕቅድ ተነድፎ ተግባራዊ የሚሆንበትን ዝርዝር ይዘጋጃል።

👉 ከስምምነቱ መፈረም በኃላ የመንግስት እና ህወሓት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ይነጋገራሉ (የጦር አመራሮች የስልክ ንግግር ማድረጋቸው መነገሩ ይታወቃል) ።

👉 ስምምነቱ በተፈረመ በአምስት ቀናት ውስጥ በክልሉ ካለው ተጨባጭ ፀጥታ ሁኔታ በመነሳት ስብሰባ በማዘጋጀት የጦር አመራሮች የህወሓት ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት ላይ ይነጋገራሉ ፤ ስለሂደቱም ዝርዝር ያወጣሉ። (ይህ ከሰኞ ቀን 28/2/2015 ጀምሮ በኬንያ፣ ናይሮቢ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ከህወሓት ጄነራል ታደሰ ወረደ በተገኙበት ተጀምሯል)

👉 ከፍተኛ የጦር መኮንኖች #ከስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ባሉት #አስር_ቀናት ውስጥ የከባድ መሳርያ ትጥቅ የመፍታቱ ሂደት #ይጠናቀቃል። የተቀመጠው አስር ቀናት ጊዜ ገደብ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በሚሰጡት ሀሳብ እና በሁለቱ ወገኖች አጽዳቂነት ሊራዘም ይችላል።

👉 ከስምምነቱ በኋላ ባሉ 30 ቀናት ቀላል የጦር መሳርያዎችን ጨምሮ የህወሓት ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል።

👉 የህወሓት ታጣቂዎችን የማሰናበት እና መልሶ ወደ ማኅበረሰቡ የመቀላቀል ሥራ ሂደት የክልሉን ሕግ እና ፍላጎት መሠረት ያደርጋል።

@tikvahethiopia