#Update የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን #ጅማ_አባ_ጅፋር የእግር ኳስ ክለብን ከማንኛውም ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ማገዱን አስታወቀ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለfbc እንዳስታወቀው፥ ጅማ አባ ጅፋር የእግር ኳስ ክለብ ከየካቲት 29 2011 ጀምሮ ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ላይ ታግዷል። እንደ ፌዴሬሽኑ ገለጻ፥ ጅማ አባ ጅፋር የእግር ኳስ ክለብ የታገደው አብዱልፈታህ ከማል ለተባለው ተጫዋቹ ተገቢውን ክፍያ ባለመፈፀሙ ነው። አብዱልፈታህ ከማል የተባለው የእግር ኳስ ተጫዋች ከክለቡ ጋር ውል እያለው ከመስከረም ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ ወሉ በክለቡ በመቋረጡ ለፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን፥ ኮሚቴውም የተጫዋቹን አቤቱታ በመመልከት ለአመልካች ያልተከፈለው ደመወዝ ታስቦ በአምስት ቀናት ውስጥ እንዲከፈለው የካቲት 12 2010 ዓ.ም ለክለቡ በተፃፈ ደብዳቤ ማሳወቁን ገልጿል። ጅማ አባ ጅፋር የእግር ኳስ ክለብም ይህንን ተግባራዊ ሳያደርግ በመቆየቱ የዲሲፕሊን ኮሚቴው ሚያዝያ 12 2010 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ በክለቡ ላይ ቀጣይ እርምጃ እንደሚወስድ ያሳወቀ ቢሆንም ክለቡ ግን ለተጫዋቹ ክፍያውን ሳይከፍል ቆይቷል ብሏል። በመሆኑም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ጅማ አባ ጅፋር የእግር ኳስ ክለብ ከየካቲት 29 2011 ዓ.ም ጀምሮ ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጃቸው የእግር ኳስ ውድድሮች የታገደ መሆኑን አስታውቋል።
Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia