TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አቶ አህመድ ሽዴ⬇️

በአዲስ አበባ ከተማ ሰዎች ታፍሰው ተወሰዱ ተብሎ የሚሰራጨው ወሬ የተሳሳተ መሆኑንና ህብረተሰቡን ለማደናገር የሚሰራ ስራ እንደሆነ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትሩ አቶ #አህመድ_ሽዴ
አስታወቁ።

ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳይ በሰጡት መግለጫ፥ በተለያዩ አካባቢዎች ህይወት እንዲጠፋና ንብረት እንዲወድም በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች በህጋዊ መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

መንግስት በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ከመስከረም 2 ጀምሮ የፖለቲካ ኃይሎችን ለመቀበል በደጋፊዎቹ መካከል በተፈጠረው ያልተገባ #ፉክክር ግጭቶች መፈጠራቸውን አስታውሰዋል።

እየሰፋ ቤደው ግጭትም በቡራዩ 27 ሰዎች በአዲስ አበባ 28 በጥቅሉ 55 ሰዎች #ህይወታቸው እንዳለፈ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በቡራዩ ከተማ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እንዳጋጠመና 3 ሺህ 50 ሰዎችም መፈናቀላቸውን ገልፀዋል።

እነዚህን ግጭቶች የብሄር ማስመሰልና በማህበራዊና በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የተዛቡ መረጃዎችን በማቅረብ ግጭቱን ለማባባስ እንቅስቃሴ ተደርጓል ብለዋል።

በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ከተማ ከግጭቱ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው 170 ሰዎችና በቡራዩ ከተማ ደግሞ 390 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተናግረዋል።

እንዲሁም በአዲስ አበባ ሁከቱና ብጥብጡን ለማማባባስ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ 1200 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

ችግሩን ለመቆጣጠር የፍትህና የፀጥታ አካላት ባደረጉት ርብርብ ችግሩ በቁጥጥር ስር እንደዋለ አስታውቀዋል።

#መንግስት በደረሰው የህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት የተሰማውን #ሀዘን ሚኒስትሩ ገለፀዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የተኩስ ልውውጡ ምክንያት በአፓርታማው ጠባቂ(ፌደራል ፖሊስ) እና በሌሎች የፌደራል ፖሊሶች መካከል የተፈጠረ #አለመግባባት እንደነበረና በተኩስ ልውውጡም 2 አባሎች #ህይወታቸው ሲያልፍ 4 አባሎች ላይ #ቀላል ጉዳት መድረሱን ኮማንደር ብርሃነ ለetv በስልክ መስመር ገብተው ገልፀዋል። #በነዋሪዎች ላይ የደረሰ ምንም ጉዳት የለም።

ቦሌ መንገድ በሚገኘው የፓርላማ አባላት መኖሪያ አፓርታማ አካባቢ ከሌሊት ጀምሮ በነበረው የተኩስ ልውውጥ የቦሌ መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ መቆየቱ ታውቋል። እንዲሁም ከመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድም ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ነበር። አሁን ላይ መንገዶቹ መከፈታቸው ተከፍተዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢቲቪ (ጤና ይስጥልኝ ኢትዮጵያ), ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በአዲስ አበባ በመኪና አደጋ ሁለት ሰዎች ሞቱ። ዛሬ ጥቅምት 24/2011 ዓ/ም ከጠዋቱ 1:00 ገደማ ፈረንሳይ አንቆርጫ በተለምዶ #ጥንስስ ወንዝ ተብሎ በሚጠራው ቦታ አካባቢ ዳገት
እየወጣ እያለ ፒካፕ መኪና ግራቸውን ይዘው ወደ አታክልት ተራ ይሄዱ የነበሩ ሁለት የ28 አመት ወጣቶች #ህይወታቸው አለፈ፡፡ መኪናውም ከአስፓልቱ መቶ ሜትር እርቆ ገደሉ ውስጥ ገብቷል፡፡ የአሽከርካሪው ሹፌርም ለግዜው ተሰውሯል፡፡

ነብስ ይማር!!

ምንጭ፦ ዋልተንጉስ አብነህ
@tsegabwolde @tikavhethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

3 የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የወሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ(water treatment pond) ውስጥ ገብተው #ህይወታቸው_አልፎ መገኘቱ ተሰምቷል። ተማሪዎቹ መቼ ገንዳ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው እንዳለፈ እስካሁን #አልታወቀም። የአንደኛው ተማሪ አስክሬን ትላንት 5:00 የተገኘ ሲሆን የቀሩት ሁለት ተማሪዎች አስክሬን ዛሬ ጥዋት 3:00 እና 5:00 በፍለጋ ተገኝቷል። ስለተማሪዎቹ ህልፈትም የተማሪዎች ህብረቱን ጠይቄ አረጋግጫለሁ። ስለአሟሟታቸው በፖሊስ ማጣራት እየተደረገ ይገኛል። የተማሪዎቹ አስክሬን ለህክምና ምርመራ ወደሆስፒታል ተወስዷል።

🔹መረጃውን ያረጋገጠልኝ የተማሪዎች ህብረት ተወካይ የሟች ተማሪዎችን ስም ዝርዝር አድርሶኛል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አ.ሳ.ቴ.ዩ‼️

ሶስቱ የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አማሟት ላይ ፍንጭ ለማግኘት ፖሊስ #ምርመራ እያደረገ እንደሆነ ገለፀ።

ከሰሞኑ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ለፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ባዘጋጀው የውሃ ገንዳ ውስጥ ሶስት ተማሪዎች #ህይወታቸው_አልፎ መገኘቱ በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ስለተማሪዎቹ አሟሟት ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተለያዩ መላምቶች ቢሰነዘሩም ይሄ ነው የሚባል ተጨባጭ መረጃ አልተገኘም ነበር።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ቢቢሲ የአዳማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ደረጀ ሙልዕታ ስለሁኔታው ማብራሪያ ጠይቋቸዋል።

ኮማንደሩ እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው ፍሳሽ ቆሻሻን ተመልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚረዳ የውሃ ማጠራቀሚያ ኩሬ ውስጥ አንድ ሰው ህይወቱ አልፎ እንደታየ ለፖሊስ በዩኒቨርሲቲው በኩል ጥቆማ ይደርሰዋል።

ጉዳዩን ለማጣራትም የፖሊስ አባላት የተላኩ ሲሆን እንደተባለውም አንድ ሬሳ መርማሪ ፖሊሶቹ በማግኘታቸው፤ የሞቱን ምክንያት ለማጣራት ጥረት የተደረገ ሲሆን ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ሬሳው ወደ አዲስ አበባ ተልኳል።

በማግስቱም ሌላ ሬሳ በውሃ ኩሬው ውስጥ እንደታየ ጥቆማ ለፖሊስ መድረሱን ኮማንደሩ ገልፀው ፖሊሶች በቦታው ሲደርሱም ተጨማሪ ሁለት ሬሳዎች በውሃው ውስጥ አግኝተዋል።

ፖሊስ ባደረገው ማጣሪያ መሰረትም ሶስቱም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ሲሆኑ "በጣም የሚዋደዱና የማይለያዩ የአራተኛ ዓመት ተማሪዎች እንደነበሩ አረጋግጠናል" ብለዋል ኮማንደር ደረጀ።

ተማሪዎቹን ለሞት ያበቃቸው ምክንያት ምን እንደሆነ ለማጣራት የጀመሩት ምርመራ እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ የህክምና ማስረጃ ለማግኘት ሶስቱንም አስከሬኖች ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል የተላኩ ሲሆን የምርመራው ውጤት ሲደርሳቸው ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ኮማንደሩ በተጨማሪ ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ የሞቱት ከዘር ጥቃት ጋር በተያያዘ እንደሆነ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘስ ምን አይነት መረጃ አግኝታችኋል? ሲል ቢቢሲ ለኮማንደሩ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

ኮማንደሩ ሲመልሱም "ተማሪዎቹ ከመጡበት አካባቢ ጋር ተያይዞ ጥቃት እንደደረሰባቸው የሚያሳይ ምንም አይነት መረጃ አላገኝንም፤ ተማሪዎቹም ከተለያየ አካባቢ ነው የመጡት" ብለዋል።

''እንደውም ተማሪዎቹ ከአዲስ አበባ፣ ከባህርዳርና ከአሰላ የመጡ ጓደኛሞች ሲሆኑ በምርመራ ወቅትም ሰውነታቸው ላይ ምንም አይነት ምልክት አላገኘንም።'' ብለዋል።

ከዚህ በኋላ መሰል ክስተቶች እንዳያጋጥሙ ፖሊስ በውሃ ማጣሪያ ኩሬው አካባቢ ጥበቃ እየተደረገ እንደሆነና ኩሬው ለወደፊቱ በአጥር እንዲከለል ከዩኒቨርሲቲው ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አክለዋል።

በመጨረሻም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ የተሳሳቱ መልእክቶችን ሳያጣሩ ከማመን ማህበረሰቡ እነዲቆጠብና እንዲህ አይነት ክስተቶች ሲያጋጥሙ ትክክለኛውን መረጃ ከሚመለከተው አካል እንዲጠብቁ ኮማንደሩ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia