TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአምቦ የልማት ፕሮጀክት ተሰማርተው ለመስራት የሚመጡ ኢንቨስተሮች የጸጥታ ስጋት ሊኖርባቸው እንደማይገባ ተገለጸ። የምዕራብ ሸዋ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ዶክተር #መንግስቱ_ቱሉ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት በአምቦ ከተማ ፍጹም #ሰላም የሰፈነበት እንቅስቃሴ መኖሩን ጠቅሰው ኢንቨስተሮች ያለምንም የጸጥታ ስጋት መዕዋለ ንዋያቸውን ማፍሰስ ይችላሉ ብለዋል። ሀላፊው የአምቦ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪ ከመንግስት ጎን በመቆም ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ሰላምን ለማስፈን ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው ህዝቡ በሶስት መንግስታት ከልማት ርቆ የቆየ በመሆኑ አሁን የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ለመልማት ራሱን አዘጋጅቷል ብለዋል።

Via ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው ሰው ቁጭ ብዬ ልብላ የሚል መሆኑ ነው ችግር የሆነው፤ ቁጭ ብዬ ልተች ከዚያ ጫፍ እስከዚያ ጫፍ #መሳደብ፣ መተቸት ነው እንጂ፤ እጄን አስገብቼ ልድከም የሚል ሰው ካለ መጠቀም ጥሩ ነው ምክንያቱ ከፍተኛ የሚችሉ ሰዎች እጥረት አለ።" ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በእስር ላይ የሚገኙት እነ አቶ በረከት ስምዖን #ኮምፒውተር#ስልክ እና #የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤት #ውድቅ አድርጎባቸዋል። ተጠርጣሪዎቹ አቶ በረከት ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ ከዚህ በፊት ምስክሮችንና የሕግ ባለሞያዎችን ምክር ለማገኘት እንዲረዳቸው የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎቶች በባህር ዳር ማረሚያ ቤት እንዲሟላላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ ሆኖም ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት ኮምፒዩተሮችና የስልክ አገልግሎት በማረሚያ ቤቱ ስለሚገኙ ተጠርጣሪዎቹም በዛው እንዲገለገሉ በማለት የባሕር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥያቄውን ዛሬ ወድቅ ማድረጉን የጀርመን ራድዮ ዘግቧል። ፍርድ ቤቱ ግለሰቦቹ እንደሌሎች ጠጠርጣሪዎች ማረሚያ ቤቱ የሚያቀርበውን ማንኛውንም ቁሳቁስ እንዲጠቀሙ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው አርብ እለት የአማራ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ #ተጠርጣሪዎቹ ለመጋቢት 2 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲቀርቡ አዟል።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በናይጄሪያ #ሰላማዊ_ምርጫ መካሄዱን የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ አቶ #ኃይለማሪያም_ደሳለኝ አስታወቁ፡፡ ባሳለፍነው ቅዳሜ በናይጄሪያ የተካሄደው ምርጫ ሰላማዊ እንደ ነበር የአፍካ ህብረት የናይጀሪያ ምርጫ ታዛቢ ቡድን መግለጹ ተነግሯል፡፡ ከምርጫ #ግብዓቶች ጋር በተያያዘ ለአንድ ሳምንት በተራዘመውና በሳለፍነው ቅዳሜ በተካሄደው የናይጄሪያ ምረጫ ላይ አስተያየቱን በመስጠት የህብረቱ ታዛቢ ቡድን የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የናይጀሪያን ምርጫ ቆጠራ በተደረገባቸው ግዛቶች ፕሬዝዳንት ሙሐማዱ ቡሀሪ #እየመሩ ነው፡፡ ከ73 ሚሊዮን በላይ መራጮች በተሳተፉበት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መጠነኛ ግጭቶች ቢታዩበትም ከ70 በላይ ለፕሬዝዳንትነት የቀረቡ ዕጩዎችን አሳትፎ ተጠናቅቋል፤ የድምፅ ቆጠራው ግን በሂደት ላይ ነው፡፡

በሌላ መረጃ...

#ማኪ_ሳል በሴኔጋል ፕርዝዳታዊ ምርጫ አሸነፉ፡፡ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል እሑድ በተደረገው ምርጫ አሸናፊ የሆኑት 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን መራጮች በተሳተፉበት ምርጫ 57 በመቶውን በማግኘት መሆኑን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ፣ አፍሪካ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ልጇን አጣች‼️

ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ደንበል አካባቢ በደረሰው #የመኪና_አደጋ የAAiT መምህር የሆኑት አቶ #ሳምሶን_ዋለልኝ ህይወታቸው አልፏል።

እንደወጣን እየቀረን ነው...

•TIKVAH-ETHIOPIA ለወዳጅ፤ ዘመዶች እንዲሁም ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ #መፅናናትን ይመኛል!

#ነብስ_ይማር!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሌላ አሳዛኝ መርዶ...

"ፀግሽ ትላንት ለሊት የኩሪፍቱ አዳማ #ማኔጀር የነበረው #መለሰ_ደጀኔን በመኪና አደጋ ከጎናችን አተነዋል! ቀን ሰርግ ውሎ ማታ ወደ አዳማ እየሄደ ከሲኖትራክ ጋር #ተጋጭቶ በደረሰ አደጋ በመሞት አተነዋል። መለሰ ማለት በጣም መልካም ሰው ነበር፣ ይህ የመኪና አደጋ በዚህ ሳምንት 2ተኛዬ ነው እንጠንቀቅ!"

Via Dagi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጎንደር ከተማ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ዘመናዊ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ተመረቀ። ፀሐይ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒየን በጎንደር ከተማ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባውን ዘመናዊ የምግብ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ አስመርቋል። ፋብሪካውን ዛሬ #መርቀው የከፈቱት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ መላኩ አለበልና የፌደራል ሕብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ #ኡስማን_ሱሩር ናቸው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እባካችሁ ጥንቃቄ አይለየን...‼️

ይህ በፎቶው የምትመለከቱት የመኪና አደጋ የደረሰው ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ ጉርድ ሾላ አካባቢ ነው። በቦታው የነበሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት እንደነገሩኝ በአደጋው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እኔ በእውነቱ ከተማው ፈርሶ እየተሰራ ነው እየተባለ #ዐይናማዎቹ ሲያወሩም ሲያስወሩም እሰማለው። ፈርሶ መሰራት ያለበት ግን የሰው #አስተሳሰብ ነው። #የሰው አስተሳሰብ ፈርሶ ካልተሰራ፤ የተሰራ ከተማ #ይፈርሳል። ጃፓን እና ቻይና ሀገራቸውን ያለሙት መጀመሪያ አስተሳሰባቸውን #አልምተው ነው"-- መጋቤ ሀዲስ አሸቱ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን #ጅማ_አባ_ጅፋር የእግር ኳስ ክለብን ከማንኛውም ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ማገዱን አስታወቀ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለfbc እንዳስታወቀው፥ ጅማ አባ ጅፋር የእግር ኳስ ክለብ ከየካቲት 29 2011 ጀምሮ ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ላይ ታግዷል። እንደ ፌዴሬሽኑ ገለጻ፥ ጅማ አባ ጅፋር የእግር ኳስ ክለብ የታገደው አብዱልፈታህ ከማል ለተባለው ተጫዋቹ ተገቢውን ክፍያ ባለመፈፀሙ ነው። አብዱልፈታህ ከማል የተባለው የእግር ኳስ ተጫዋች ከክለቡ ጋር ውል እያለው ከመስከረም ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ ወሉ በክለቡ በመቋረጡ ለፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን፥ ኮሚቴውም የተጫዋቹን አቤቱታ በመመልከት ለአመልካች ያልተከፈለው ደመወዝ ታስቦ በአምስት ቀናት ውስጥ እንዲከፈለው የካቲት 12 2010 ዓ.ም ለክለቡ በተፃፈ ደብዳቤ ማሳወቁን ገልጿል። ጅማ አባ ጅፋር የእግር ኳስ ክለብም ይህንን ተግባራዊ ሳያደርግ በመቆየቱ የዲሲፕሊን ኮሚቴው ሚያዝያ 12 2010 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ በክለቡ ላይ ቀጣይ እርምጃ እንደሚወስድ ያሳወቀ ቢሆንም ክለቡ ግን ለተጫዋቹ ክፍያውን ሳይከፍል ቆይቷል ብሏል። በመሆኑም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ጅማ አባ ጅፋር የእግር ኳስ ክለብ ከየካቲት 29 2011 ዓ.ም ጀምሮ ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጃቸው የእግር ኳስ ውድድሮች የታገደ መሆኑን አስታውቋል።

Via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጨፌ ኦሮሚያ 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት ማካሄድ #ጀምሯል። ጨፌው ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው የክልሉን መንግስት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም እንደሚገመግም ይጠበቃል። እንዲሁም በክልሉ ያለው #ሰላም#መረጋጋት እና የህግ የበላይነትን ማስከበር ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚመክርም ተገልጿል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

የትራፊክ አደጋው በትናንትናው እለት የደረሰ መሆኑን ከምስራቅ ወለጋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

#ከነቀምቴ ከተማ ወደ #ሲቡ_ስሬ ወረዳ 22 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ጪንጊ በተባለች ከተማ አቅራቢያ በመገልበጡ ነው አደጋው የደረሰው።

በትራፊክ አደጋውም በሚኒባስ ተሽከርካሪው ተሳፍረው ሲጓዙ ከነበሩ 22 ሰዎች ውስጥ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ ነው የተገለፀው።

ምንጭ፦ Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትላንት ምሽት 5:15 የተላከ...
(እንደወጣን እየቀረን ነው)

"ሀይ ፀጊሽ ዛሬ #ከነቀምት ወደ ሲቡ ሲሬ ሲጓዝ የነበረ #ሀይሩፍ_ተገልብጦ ከ10 ሰው በላይ ሞቷል። በወቅቱ ከባኮ ወደ ነቀምት ስንጓዝ ነበር። በጣም ያሳዝናል ከቀኑ 11:30 ገደማ ነበር አደጋው የተከሰተው።"

Via Yididiya Silshi(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጎንደር ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ባለው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ-ግብር እስከ 10 ሚሊዮን ብር ቃል እንደተገባ ማረጋገጡን የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴው እንዳሳወቀው ከሁለቱ ዞኖች ለተፈናቀሉ ዜጎች ማቋቋሚያ እስከ 80 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ ታቅዷል፡፡ የተፈናቃዮቹ ጉዳይ የአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ መሆኑን የገለጸው ኮሚቴው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፏል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia