መቃዲሾ‼️
ከሶማሊያ ዋና ከተማ #መቅዲሾ ወጣ ባለ አካባቢ መንገድ ዳር የሚገኙ ቁጥቋጦዎችን በማጽዳት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ታጣቂዎች ዛሬ በከፈቱት የእሩምታ ተኩስ ስምንቱን መግደላቸው ተዘገበ። በዚሁ ከዋና ከተማይቱ ከመቅዲሾ በስተሰሜን 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው «ሃዋ አብዲ» በተባለው አካባቢ በስራ ላይ ሳሉ ከተገደሉት ሌላ ስድስት መቁሰላቸውንም የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። ጥቃት የደረሰባቸው የጽዳት ሠራተኞች አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው። ጥቃቱ የተፈጸመበት ምክንያትም ሆነ ማን እንደፈጸመው እስከ ዛሬ ረፋድ በግልጽ ዐልታወቀም። ሆኖም ሞሀመድ ሀሰን የተባሉ የሶማሊያ የደህንነት ባለሥልጣን ጥቃቱ የተፈጸመው የሶማሊያን መንግሥት በሚወጋው አሸባብ ነው ሲሉ መናገራቸውን የጀርመን ዜና አገልግሎት (DPA) ዘግቧል። የጥቃቱ ሰለባዎች በምግብ ለሥራ መርሃግብር በመንገድ ጽዳት የተሰማሩ ንጹሀን ዜጎች መሆናቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia