TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎችን ከጎዳና ላይ የማንሳቱ ጅምር እሰከ ሰኔ መጨረሻ ድረስ 10ሺህ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ገለፀ፡፡ ከዚህ ውስጥም በጎዳና ያሉ 5 ሺህ ሰዎችን የከተማ አስተዳደሩ በመደበው በጀት ሲያነሳ ቀሪዎቹን ደግሞ ከአለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ ተፈፃሚ እንደሚሆን በአስተዳደሩ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የማህበራዊ ችግር ተጎጂዎችን መልሶ ማቋቋም ዳይሬክተር አቶ #እንዳሻው_አበራ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይድረስ ለኢትዮጵያ ህዝብ‼️
#ሼር #Share

"...እኛ ጋር ግጭት ከጀመረ #ማቆሚያ የለውም! ብዙ ሰው ሲናገር "የሩዋንዳ ግጭት እንዳያጋጥም ኢትዮጵያ ውስጥ" ያላል...የሩዋንዳ ግጭት ኢትዮጵያ ውስጥ ቢያጋጥም #ቀላል ነው የሚሆነው ምክንያቱም ሩዋንዳ ውስጥ ሁቱና ቱትሲ በአይን ተያይተው #ይተዋወቃሉ። ይሄ ሁቱ ነው ይሄ ቱትሲ ነው የሚለውን በመልክ ይተዋወቃሉ። የትኛው ሱማሌ ነው በመልክ ከኦሮሞ #የሚለየው?? የትኛው አፋር ነው በመልክ የሚለየው?? እርስ በእርስ ነው #የምንጨራረሰው! እኛን የሚለይ ነገር ብዙ የለም። በቀላሉ አፋርን ከሱማሌ፤ ሱማሌን ከኦሮሞ ወይም ከሌላ መለየት አይቻልም። ወደጋምቤላ አካባቢ ስትሄዱ ኑዌርን እና አኝዋክ የሚለያዩበት ምልክት አላቸው ያ ምልክት የሌለው አኝዋክ እና ኔዌር በምን ይተዋወቃል?? አስቸጋሪ ነው የሚሆነው...መገዳደል ለኛ አያስፈልግም። ከተጀመረ ግን ማቆሚያ የለውም!! #እንዳይጀመር በሀላፊነት ስሜት በጋራ እንስራ!" ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዜና እረፍት‼️

አንጋፋው ባለዋሽንት ዩሃንስ አፈወርቅ በ72 አመታቸው በዛሬው ዕለት ከሰዓት በኋላ #ከዚህ_አለም_በሞት_ተለዩ፡፡

አርቲስቱ በተለይም ፍቅር እስከ መቃብር የተተረከበት ዋሽንትን በመጫወት ይታወቃሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ህዝብ ለህዝብ በተሰኘው የኪነ ጥበብ ጉዞ አባል በመሆን ተሳታፊም ነበሩ፡፡

አርቲስት ዩሃንስ አፈወርቅ በአዲስ አበባ ባህልና አደራሽ ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል፡፡ አርቲስቱ የተወለዱት ጎጃም ውስጥ በቀድሞው የአገው ምድር አውራጃ ባንጃ ወረዳ በሚል በሚታወቀው ስፍራ ታህሳስ 3 ቀን 1939 ዓ.ም ነበር ፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ቀናት በድምሩ 1,506,260 ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ #ጅግጅጋ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ በቁጥጥር ስር የዋለው ኮንትሮባንድ ኬሚካል፣ ስኳር እና የቁም እንስሳት የሚያካትት ነው፡፡ በዚህ መሰረት በእግር እየተነዱ ከሀገር ሊወጡ የነበሩ ግምታዊ ዋጋቸው 112,500 ብር የሆነ ዘጠኝ በሬዎች የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ሌሊት 7፡00 ጅግጅጋ ውስጥ በሚሊሻና በጉምሩክ አባላት ሲያዙ ተጠርጣው ለጊዜው ማምለጡን ነው የተገለፀው፡፡

Via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቃዲሾ‼️

ከሶማሊያ ዋና ከተማ #መቅዲሾ ወጣ ባለ አካባቢ መንገድ ዳር የሚገኙ ቁጥቋጦዎችን በማጽዳት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ታጣቂዎች ዛሬ በከፈቱት የእሩምታ ተኩስ ስምንቱን መግደላቸው ተዘገበ። በዚሁ ከዋና ከተማይቱ ከመቅዲሾ በስተሰሜን 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው «ሃዋ አብዲ» በተባለው አካባቢ በስራ ላይ ሳሉ ከተገደሉት ሌላ ስድስት መቁሰላቸውንም የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል። ጥቃት የደረሰባቸው የጽዳት ሠራተኞች አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው። ጥቃቱ የተፈጸመበት ምክንያትም ሆነ ማን እንደፈጸመው እስከ ዛሬ ረፋድ በግልጽ ዐልታወቀም። ሆኖም ሞሀመድ ሀሰን የተባሉ የሶማሊያ የደህንነት ባለሥልጣን ጥቃቱ የተፈጸመው የሶማሊያን መንግሥት በሚወጋው አሸባብ ነው ሲሉ መናገራቸውን የጀርመን ዜና አገልግሎት (DPA) ዘግቧል። የጥቃቱ ሰለባዎች በምግብ ለሥራ መርሃግብር በመንገድ ጽዳት የተሰማሩ ንጹሀን ዜጎች መሆናቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update 123ኛ የአደዋ ድል በአል በአጼ ምኒልክ የትውልድ ቦታ በአንጎለላ ኪዳነ ምህረት ተከበረ። በተያያዘ መረጃ123ኛው የአድዋ ድል በዓል ”የአድዋ ድል የአንድነታችን ማህተም!" በሚል መሪ ቃል በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚከበር መንግስት አስታውቋል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአምቦ የልማት ፕሮጀክት ተሰማርተው ለመስራት የሚመጡ ኢንቨስተሮች የጸጥታ ስጋት ሊኖርባቸው እንደማይገባ ተገለጸ። የምዕራብ ሸዋ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ዶክተር #መንግስቱ_ቱሉ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት በአምቦ ከተማ ፍጹም #ሰላም የሰፈነበት እንቅስቃሴ መኖሩን ጠቅሰው ኢንቨስተሮች ያለምንም የጸጥታ ስጋት መዕዋለ ንዋያቸውን ማፍሰስ ይችላሉ ብለዋል። ሀላፊው የአምቦ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪ ከመንግስት ጎን በመቆም ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ሰላምን ለማስፈን ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው ህዝቡ በሶስት መንግስታት ከልማት ርቆ የቆየ በመሆኑ አሁን የመጣውን ለውጥ ተከትሎ ለመልማት ራሱን አዘጋጅቷል ብለዋል።

Via ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው ሰው ቁጭ ብዬ ልብላ የሚል መሆኑ ነው ችግር የሆነው፤ ቁጭ ብዬ ልተች ከዚያ ጫፍ እስከዚያ ጫፍ #መሳደብ፣ መተቸት ነው እንጂ፤ እጄን አስገብቼ ልድከም የሚል ሰው ካለ መጠቀም ጥሩ ነው ምክንያቱ ከፍተኛ የሚችሉ ሰዎች እጥረት አለ።" ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በእስር ላይ የሚገኙት እነ አቶ በረከት ስምዖን #ኮምፒውተር#ስልክ እና #የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤት #ውድቅ አድርጎባቸዋል። ተጠርጣሪዎቹ አቶ በረከት ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ ከዚህ በፊት ምስክሮችንና የሕግ ባለሞያዎችን ምክር ለማገኘት እንዲረዳቸው የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎቶች በባህር ዳር ማረሚያ ቤት እንዲሟላላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ ሆኖም ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት ኮምፒዩተሮችና የስልክ አገልግሎት በማረሚያ ቤቱ ስለሚገኙ ተጠርጣሪዎቹም በዛው እንዲገለገሉ በማለት የባሕር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥያቄውን ዛሬ ወድቅ ማድረጉን የጀርመን ራድዮ ዘግቧል። ፍርድ ቤቱ ግለሰቦቹ እንደሌሎች ጠጠርጣሪዎች ማረሚያ ቤቱ የሚያቀርበውን ማንኛውንም ቁሳቁስ እንዲጠቀሙ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው አርብ እለት የአማራ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ #ተጠርጣሪዎቹ ለመጋቢት 2 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲቀርቡ አዟል።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በናይጄሪያ #ሰላማዊ_ምርጫ መካሄዱን የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ አቶ #ኃይለማሪያም_ደሳለኝ አስታወቁ፡፡ ባሳለፍነው ቅዳሜ በናይጄሪያ የተካሄደው ምርጫ ሰላማዊ እንደ ነበር የአፍካ ህብረት የናይጀሪያ ምርጫ ታዛቢ ቡድን መግለጹ ተነግሯል፡፡ ከምርጫ #ግብዓቶች ጋር በተያያዘ ለአንድ ሳምንት በተራዘመውና በሳለፍነው ቅዳሜ በተካሄደው የናይጄሪያ ምረጫ ላይ አስተያየቱን በመስጠት የህብረቱ ታዛቢ ቡድን የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የናይጀሪያን ምርጫ ቆጠራ በተደረገባቸው ግዛቶች ፕሬዝዳንት ሙሐማዱ ቡሀሪ #እየመሩ ነው፡፡ ከ73 ሚሊዮን በላይ መራጮች በተሳተፉበት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መጠነኛ ግጭቶች ቢታዩበትም ከ70 በላይ ለፕሬዝዳንትነት የቀረቡ ዕጩዎችን አሳትፎ ተጠናቅቋል፤ የድምፅ ቆጠራው ግን በሂደት ላይ ነው፡፡

በሌላ መረጃ...

#ማኪ_ሳል በሴኔጋል ፕርዝዳታዊ ምርጫ አሸነፉ፡፡ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል እሑድ በተደረገው ምርጫ አሸናፊ የሆኑት 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን መራጮች በተሳተፉበት ምርጫ 57 በመቶውን በማግኘት መሆኑን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ፣ አፍሪካ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ልጇን አጣች‼️

ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ደንበል አካባቢ በደረሰው #የመኪና_አደጋ የAAiT መምህር የሆኑት አቶ #ሳምሶን_ዋለልኝ ህይወታቸው አልፏል።

እንደወጣን እየቀረን ነው...

•TIKVAH-ETHIOPIA ለወዳጅ፤ ዘመዶች እንዲሁም ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ #መፅናናትን ይመኛል!

#ነብስ_ይማር!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሌላ አሳዛኝ መርዶ...

"ፀግሽ ትላንት ለሊት የኩሪፍቱ አዳማ #ማኔጀር የነበረው #መለሰ_ደጀኔን በመኪና አደጋ ከጎናችን አተነዋል! ቀን ሰርግ ውሎ ማታ ወደ አዳማ እየሄደ ከሲኖትራክ ጋር #ተጋጭቶ በደረሰ አደጋ በመሞት አተነዋል። መለሰ ማለት በጣም መልካም ሰው ነበር፣ ይህ የመኪና አደጋ በዚህ ሳምንት 2ተኛዬ ነው እንጠንቀቅ!"

Via Dagi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጎንደር ከተማ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ዘመናዊ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ተመረቀ። ፀሐይ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒየን በጎንደር ከተማ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባውን ዘመናዊ የምግብ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ አስመርቋል። ፋብሪካውን ዛሬ #መርቀው የከፈቱት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ መላኩ አለበልና የፌደራል ሕብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ #ኡስማን_ሱሩር ናቸው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እባካችሁ ጥንቃቄ አይለየን...‼️

ይህ በፎቶው የምትመለከቱት የመኪና አደጋ የደረሰው ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ ጉርድ ሾላ አካባቢ ነው። በቦታው የነበሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት እንደነገሩኝ በአደጋው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia