TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ #ለማ_መገርሳ በለገጣፎ ቤት የማፍረሱ እንቅስቃሴ እንዲቆም አዘዋል። ከነዋሪዎቹ ጋርም ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘዋል።" (በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ)
.
.
አቶ #አዲሱ_አረጋ፦ "እኔ ከአቶ #ለማ እንዲህ አይነት ትእዛዝ እንደተላለፈ #አላውቅም። የህግ ማስከበሩ ተግባር #እንደቀጠለ ግን አውቃለሁ።"

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት(አቶ አዲሱ አረጋን በስልክ ጠይቆ የተሰጠው ምላሽ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...ፌክ ኒውሶች ናቸው!"

አቶ አዲሱ አረጋ ከላይ በምትመለከቱት #የዋዜማ_ሬድዮ ሪፖርት ላይ ክልሉ ምን ይላል ተብለው በጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ለቀረበላቸው ጥያቄ ከሰጡት ምላሽ፦

"እነዚህ ህዝብ መሀል #ጥርጣሬ ለመፍጠር የሚሰራጩ #ፌክ_ኒውሶች ናቸው። እንግዲህ ጠ/ሚሩ #ኦሮሞ ነው፣ ከንቲባውም ኦሮሞ ነው በማለት ከተማዋን በኦሮሞ #ለማስወረር ነው በሚል ኦሮሞን ስግብግብ አድርጎ ለመሳል ነው። እኛ ከሶማሌ የተፈናቀሉትን ዜጎቻችንን የማስፈር ስራ #ጨርሰናል። እኛ #በወረራ አዲስ አበባ ላይ ያለንን ጥያቄ እናሳካለን የሚል አቋም የለንም። ስንጠላው እና ስንታገለው የነበረውን አይነት #አሻጥር የመስራት ፍላጎቱም አእምሮውም የለንም።"

Via ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦነግ/WBO‼️

የ'ኦነግ' የቅበላ ቀነ ገደብ ተጠናቋል!
(*የልዩ ሁነት #አምስት የመጨረሻ ቀናት አሉ)
.
.
ከመንግሥት ጋር በተፈጠረው ያለመግባባት ዳግም በውጊያና የተለያዩ ግጭቶች ላይ የቆየው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የከበረውን የገዳ ሥርዓት መርሖዎችና ሕጎች መሰረት አድርጎ ለቀረበው ጥሪና የሰላም አዋጅ ላለፉት ሶስት ቀናት ሲደረግለት የቆየው አቀባበል ትላንት ምሽት 12:00 ላይ መጠናቀቁን የእርቀ ሰላሙ የቴክኒክ ኮሚቴ ይፋ አድርጓል።

በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል እርቀ ሰላም ለማውረድ፤ በኦሮሚያ አባገዳዎች፣ በሀደ ሲንቄዎች(Haadha Siinqee)፣ በአገር ሽማግሌዎች፣ በምሁራንና ለሰላም መስፈን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ በቆዩ በርካታ ዜጎች እንቅስቃሴ ጥረቱ መልካም ፍሬ አፍርቶ #በጫካ የነበረው ሠራዊት ላላፉት ሦስት ቀናት በኦሮሚያ 12 ዞኖችና 22 ወረዳዎች አቀባበል ሲደረግለት ቆይቷል።

ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በአባገዳዎች #የሰላም_አዋጅ ታውጆ የእርቀ ሰላም ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ጥሪው በጎ ምላሽ አግኝቶ ሠራዊቱ መሳርያውን ለአባገዳዎችና ለቴክኒክ ኮሚቴው በማስረከብ ባሕላዊ አቀባበል፣ ባርኮት(Muuda) እና ፍቅራዊ ክብካቤ እየተደረገለት ቆይቷል።

ከነገ ጀምሮም በተዘጋጀለት ካምፕ በመግባት በሰላም ተጠሪዎች፣ በሕግ ባለሙያዎች እና በሌሎች ምሁራን የተለያዩ ስልጠናዎች መውሰድ ይጀምራል። ከሁለት ወር በማይበልጠው በዚህ ቆይታ የሠራዊቱ አባላት እንደየፍላጎታቸው እና ችሎታቸው ስልጠና ወስደው በመስካቸው የሚመደቡ ሲሆን በቆይታቸውም በአባገዳዎች፣ በቴክኒክ ኮሚቴው አባላትና በሰላም ተጠሪዎች አያያዛቸው የሚጎበኝ ይሆናል።

እስካሁን በነበረው ሂደትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የቴክኒክ ኮሚቴው የፊታችን እሁድ ተገናኝቶ አጠቃላይ ምክክርና ግምገማ የሚያደርግ ሲሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በተያያዘ ዜና -- በ'ልዩ ሁነት' በቀነ ገደቡ መግባት ላልቻሉ የሠራዊቱ አባላት ተጨማሪ #አምስት ቀን የተሰጠ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያት በየወረዳው የሰላም ክፍሎች በመገኘት #መሳርያቸውን ማስረከብና ወደካምፕ ገብተው ለቀጣይ ሰላማዊ ሕይወታቸው ጠቃሚ የሆኑትን #ስልጠናዎች መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል።

Via Gulale Post
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስጦታ!

@medachat የሮፍናንን "የኔ ትውልድ" የሙዚቃ ኮንሰርት እንድታደሙ ለ20 አሸናፊ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ነፃ ትኬትና ሌሎች ሽልማቶች አዘጋጅቶልናል!

MedaChat App ስልኮት ላይ ተጭኗል??
1.ካልተጫነ በዚህ ያገኛሉ www.bit.ly/medachatapp

2. በመቀጠል በሜዳ ቻት APP ውስጥ discovery የሚለው ውስጥ በመግባት meda hunt የሚለውን ይክፈቱ

3.ከዛም ከላይ በምስሉ ላይ ያለውን QR code ያንብቡ . . ይሸለሙ

ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት!
#የኔ_ትውልድ #አሞሌ #ሜዳ_ቻት
ማስታወቂያ!!

#ሰዉኛ ፊልም ፕሮዳክሽንና ኢንተርቴይመንት ላለፉት 2 አመታት የክብረ #ዓድዋ_ፌስቲቫልን በደማቅ ሁኔታ ሲያዘጋጅ ቆይቷል፡፡ ዘንድሮም በከፍተኛ ደረጃ ይህንኑ ፌስቲቫል ያከብራል፡፡ከነባሮቹ የፌስቲቫላችን ይዘቶች በተጨማሪ ከቅዳሜ የካቲት 16 እስከ የካቲት 23/2011 በብሔራዊ ቤተ መፃህፍት እና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ (ወመዘክር) መስትያት የተሰኘ አዲስ የፊልም ፌስቲቫል ያካሂዳል፡፡ ከዚህ ፌስቲቫል በተ¹ዳኝ የታሪካዊ መዛግብት አዉደ ርዕይ ይቀርባል፡፡

በመክፈቻው ቀን ቅዳሜ የካቲት 16 በ8፡30 ሰዓት ቁራኛዬ ፊልም ለዕይታ የሚቀርብ ስለሆነ በወመዘክር አዳራሽ ተገኝታችሁ ፊልሙን እንድትከታተሉ እና ከፊልሙ በኋላ ከዳይሬክተሩ ጋር በሚደረገው ውይይት ላይ ተሳታፊ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል።

መግቢያ በነፃ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእርቅ ኮሚቴ አባላት ታፍነው ተወሰዱ‼️

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና በመንግሥትን መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የግንባሩን ወታደሮች #ለመቀበል ወደ #ቄለም_ወለጋ አቅንተው የነበሩ ከሦስት ያላነሱ የአስታራቂ ኮሚቴ አባላት #ታፍነው መወሰዳቸው ተሰምቷል።

የእርቅ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት አባ ገዳ #በየነ_ሰንበቶ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት የኮሚቴው አባላት የሆኑ ሁለት አባ ገዳዎች እና አንዲት ሴት በቄለም ወለጋ #አንፊሎ ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ ታፍነው እንደተወሰዱ ተናግረዋል።

አባ ገዳ በየነ ሰንበቶ ''ለማግባባት ወጣ እንዳሉ ነው ታፍነው የተወሰዱት፤ ክፉ ነገር #እንደማይገጥማቸው እርግጠኛ ነኝ። ይህንም ችግር በቅርቡ እንፈታዋለን'' ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

''ብዙ ፈተናዎች እንደሚኖሩን እየወቅን ነው እርቅ ወደማውረዱ የገባነው። እርቅ ለማምጣት ነው እየሰራን ያለነው። ሰላምም ይሰፍናል። የሚያጋጥሙን ችግሮች ወደ ኋላ አያሰቀሩንም'' ሲሉም ጥረታቸውን በዚህ ምክንያት እንደማያቋርጡም ተናግረዋል።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ቢቢሲ ያነጋገረው የየኮሚቴው ፀሃፊ #ጀዋር_መሃመድም የእርቅ ኮሚቴ አባላት ችግር እየገጠማቸው እንደሆነ ተናግሯል።

''የገጠመ ችግር አለ። በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ ከኮሚቴው አባላት ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ለህዝቡ መግለጫ እንሰጣለን'' ሲል ጀዋር ገልጿል።

ጀዋር ሃሙስ ምሽት ላይ በፌስቡክ ገጹ ላይ ታፍነው ተወስደዋል ያላቸውን አራት ሰዎች ከስም ዝርዝራቸው ጋር አውጥቷል። ታፍነዋል ተወስደዋል የተባሉት ሰዎች የት እንዳሉ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው ተናግሯል።

በተመሳሳይ መልኩ በምዕራብ ወለጋ መነ ሲቡ ወረዳ የቴክኒክ አባላቱ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ከነዋሪዎች ተሰምቷል። ተፈጸሟል ስለተባለው ድብደባ ግን ከቴክኒክ ኮሚቴው አባላት #ማረጋገጥ አልተቻለም።

የእርቅ ኮሚቴ አባላቱን ማን አፈናቸው?

የቴክኒክ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት አባ ገዳ በየነ ሰንበቶም ሆኑ የኮሚቴው ፀሃፊ ጀዋር መሃመድ የእርቅ ኮሚቴውን አባላት ያፈነው ኃይል ይህ ነው በማለት በስም ከመጥቀስ #ተቆጥበዋል

ጀዋር የአባላቱን መታፈን ይፍ ባደረገበት ጽሁፍ ''እየደረሰብን ያለውን #ስቃይ ሁሉ በሆዳችን ይዘን እየሄድን ነው። አሁን ግን የህይወት ጉዳይ ስለሆነ መናገር አለብን። አባ ገዳዎች፣ እናቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ለሃገር ሰላም እና እርቅ ለማውረድ ነው የሚደክሙት እንጂ ምንም በደል አልፈጸሙም። በአስቸኳይ እንዲለቀቁን እንጠይቃለን'' ሲል በፌድቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።

ከዚህ ቀደምም በምዕራብ ኦሮሚያ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር ደለሳ ቡልቻ ለሁለት ቀናት ታፍነው ከቆዩ በኋላ መለቀቃቸው ይታወሳል። ዶ/ር ደለሳ የገጠማቸውንና ማን እንዳፈናቸው ለመናገር ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

በምዕራብ ኦሮሚያ የሚገኙ ባንኮች በተዘረፉበት ወቅትም የባንክ ሰራተኞችም ታፍነው ተወስደው እንደነበረ ይታወሳል።

ምንጭ፦ BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ አዲሱ አረጋ‼️

"...ሰሞኑን #እርምጃ እየተወሰደባቸዉ ካሉ ከተሞች አንዱ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ እና በመደበኛ ሚዲያም ጭምር ህገ ወጥ ግንባታ ላይ እየተወሰደ ያለዉ እርምጃ በለገጣፎ ለገዳዲ ብቻ እየተደረገ ያለ እና #ብሄር ለይቶ #እርምጃ አስመስሎ እየቀረበ መሆኑን አስተዉለናል፡፡ ይህ #ስህተት ነዉ፡፡ እስካሁን በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 25 ከተሞች በተደረገ እንቅስቃሴም ህግን ብቻ ባማከለ 36,117 ህገ ወጥ ይዞታዎች እና ህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ ህግን የማስከበር ስራ ተሰርቷል፡፡"

https://telegra.ph/ህገ-ወጥ-ግንባታን-በተመለከተ-አቶ-አዲሱ-አረጋ-02-22
ትላንት ለአምቦ ልዩ ቀን ነበር!

(Yonas Alemayehu)

ስለ አምቦ ብዙ ፅፈናል፣ ብዙ ጩኸናል። ይህች ከተማ ለኔ ህይወቴ ናት። የዛሬ ማንነት መሰረቴ። አምቦ በወለደቻቸው ልጆች ትመሰላለች። የትም ሄደው የሚያኮሩ ልጆች እናት ናት። አምቦ . . . ዋጋ ከፍላ ሃገር ያቀናች ትልቅ ባለውለታ ናት።

ብዙዎቻችን ሌሎች ከተሞች በተዘዋወርን ቁጥር በከተሞቹ ውስጥ የምናየው የኛዋን #አምቦ እድገት ነው።

ዛሬ ለዚህች ከተማ ይህ ሁሉ ባለሃብት ሊደግፋት ይችላል፤ ካለችበት የኢኮኖሚ አዝቅጥ ቀና ሊያደረጋት ይተባበራል ብዬ አላስብኩም ነበር። በሆነው ነገር ግን ዳግም ተስፋ አደረኩ።

ስለ አምቦ ለማውራት 5 ሆነው ሰብሰብ ብለው ቢጠሩኝ እንኳን አልቀርም። የትላንርናው ግን እንደ ሁልግዜው ለብሶት የተሰባሰብን አልነበረም።

ጠ/ሚሩ፣ የክልሉ ፕሬዝዳንት እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በተገኙበት በሎርየት ፀጋዬ ገ/መድህን "ምነው አምቦ?" ግጥም የተጀመረው መድረክ ከበርካታ ባለሃብቶች ጋር በጋራ ስለ አምቦ መከርን።

1. 12ሺ ተማሪ ማስተናገድ የሚችል በሃገሪቱ የመጀመሪያው የሚሆን ስታንዳርዱን የጠበቀ ሃይስኩል ት/ቤት
(155-170ሚ ብር)

2. 20ሺ ሰው በመቀመጫ የሚያሰተናግድ አለም አቀፍ ስታድየም (350-400ሚ ብር) እና

3. የሎርየት ፀጋዬ ገ/መድህን የአርት ጋላሪ (እስከ 250ሚ ብር) የገቢ ማሰባሰቢያው መነሻ ፕሮጀክቶች ነበሩ።

አምቦን ለመደገፍ በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አስተባባሪነት በHayat Regency Hotel በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ፕሮግራም ጠ/ሚሩ ከሃገር መሪ በስጣታ የተሰጣቸውን የእጅ ሰዓት ለጨረታ ባቀረቡት የተገኘ 5 ሚሊየን ብር መነሻ #ከሁሉም የሃገሪቱ ክፍል ባለሃብቶች በጥቅሉ 350 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ተችሏል። የእርዳታ የባንክ ሂሳብ ቁጥርም ይፋ ሆኗል።

በምሽቱ ጠ/ሚሩ ለአምቦ ህዝብ ይህችን መልዕክት አስተላልፉልኝ ብለዋል፦

"በኦሮሚያ እያለሙ ያሉ የሌሎች አካባቢ ባለሃብቶች በክልሉ በነፃነት እንዲሰሩና ምንም ስጋት እንዳይገባቸው እነርሱን በመጠበቅ ግንባር ቀደም ሁኑ"

ለአምቦ ከተማ እርዳታ ማድረግ ልምትሹ

የአካውንት ስም፦ የአምቦ ከተማ እድገት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Acc.No. 1000273326417
የኦሮሚያ ኢንትርናሽናል ባንክ Acc.No. 1014375
የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ Acc.No. 1000044088421
አዋሽ ባንክ No.01307213953401
.
.
.
በምሽቱ ከተደረጉት ንግግሮች መካከል፦

(Yonas Alemayehu)

" . . . አምቦ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ ናት። በዚህ በነበረው ነገር ሁሉ በየዩንቨርሲቲው ችግር ሲነሳና ሰው ሲሞት አምቦ ላይ አንድም የሌላ ብሄር ተማሪ ሞቶ አያውቅም . . . ዛሬ የመጣሁት ተጋብዤ ሳይሆን ታዝዤ ነው፣ Obboo ለማ "ትመጣለህ!" ስላሉኝ፣ እሳቸው አለቃ ናቸው፤ ታዝዣለሁ። የመጣሁት ግን ስለ ታዘዝኩ ብቻ አይደለም አምቦ ስለሆነም ነው . . ." ጠ/ሚሩ ለአምቦ ከተማ እድገት የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ግብዣ ፕሮግራም ላይ ስለ አምቦ ከተናገሩት
.
.
" . . . አምቦ እንደ ፍልስጤም ቀጠና የምትታይ ነበረች። የአምቦ ህዝብ ግጭት ስላማረው ሳይሆን ምክንያት ነበረው . . ." Obboo Lammaa Magarsaa ለአምቦ ከተማ እድገት ድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ከተናገሩት
.
.
" አቶ ተክለብርሃን አምባዬ . . . እርሳቸው ወጥተዋል፤ ሙሌ አንተ አድርስልኝ፤ አቶ ተክለብርሃን 10 የትግራይ ባለሃብት ይዘው አንተም ከፈለክ ተጨመርበት . . . አምቦ ለማልማት ኑ . . . Obboo Lammaa መሬት ከሊዝ ነፃ መሬት ያዘጋጁላችኋል አምቦ ላይ ኢንቨስት ታደርጋላችሁ። ይሄ . . mallም ከሆነ አንድም እንደ ኢንቨስትመንት ነው፤ አንድም የትግራይ እና የአምቦን ህዝብ አንድነት የሚገነባ ነው" ጠ/ሚሩ ለአምቦ ከተማ እድገት በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ምሽቱን ከተናገሩት
.
.
ምንጭ፦ (Yonas Alemayehu)
@tsegabwolde @tikvahethioia
አምቦ...🔝

በአምቦ ሊገነባ ዲዛይኑ ትናንት ምሽት በገቢ ማሰባሰቢያው ይፋ የሆነውና 250ሚ ብር ወጪ የሚጠይቀው የሎርየት. ፀጋዬ ገ/መድህን የጥብበ ማዕከል (Art Gallery).

Via Yonas Alemayehu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ🔝

በዛሬው ዕለት #የመቐለ_ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ 376 ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል። ከእነዚህ መካከል 245 በመጀመርያ ዲግሪ (ዶክትሬት)፣ 78 በድህረ-ምረቃ፣ ስፔሻሊቲ በተለያዩ የህክምና ዘርፎች ነው። ከአጠቃላይ ተመራቂዎች 97ቱ ሴቶች ናቸው።

ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል!!
Via Mekelle University
ፎቶ፦EZRA(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia