TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀረማያ~ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ🔝

ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት የሀረማያ ወረዳ #የሆስፒታሉ_አምቡላንስ ነው አይሱዙ ገብቶበት ነው ወደሀረማያ ዩኒቨርሲቲ መታጠፊያ #ቦይ ውስጥ የገባው፤ ምንም ጉዳት ግን አልደረሰም!

©Dognl
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ለተፈናቀሉ ወገኖች 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ አዴፓ በተለያዩ ምክንያቶች #ተፈናቅለው በክልሉ ለሚኖሩ ወገኖች ነው በመጀመርያ ዙር 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ያስታወቀው፡፡ ተፈናቃዮች በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ለማድረግ እየሰራ መሆኑንም ፓርቲው አስታውቋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በለገጣፎ_ለገዳዲ ከተማ ቤታቸው #የፈረሰባቸው ዜጎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናገሩ...

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢሳት ጋዜጠኞች ETVን ጎበኙ🔝

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮ /ኢሳት/ ጋዜጠኞች ዛሬ ኢቢሲን ጎበኙ። ጋዜጠኞቹ በጉብኝታቸው አሁን አገሪቱ ላይ እየታየ ያለው ለውጥ ለህዝብ ብቻ ሳይሆን ለሚዲያውም ነጻነት የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡ አሁን ያለውን የሚዲያ ነጻነት ተጠቅመው የሚዲያ ተቋማት ስለሀገራቸው ሰላም እና አንድነት በሀላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ ጋዜጠኞቹ ገልጸዋል፡፡ በጉብኝታቸው ያገኙት ተሞክሮ እና ልምድ ለቀጣይ ስራቸው የሚያግዝ እንደሆነም ነው የተናሩት፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ክልል‼️

በህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ዶክተር #ሚልኬሳ_ሚደግሳ ተናገሩ።

በጉዳዩ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የቢሮ ሃላፊው ሰሞኑን እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች የሊዝ አዋጅ 721ን መሰረት ያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። እርምጃው ከተሞች ስርዓት ባለውና ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲያድጉ ለማድረግ ያለመ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ዶክተር ሚልኬሳ በመግለጫቸው ህገ ወጥ ግንባታ መሆኑ እየታዋቀ በወንዞች ዳርቻና አረንጓዴ ስፍራዎች አካባቢ ግንባታዎች መከናወናቸውንም ጠቁመዋል። ከዚህ ባለፈም ግንባታዎቹ ለመኖሪያ #ምቹ_ባልሆኑ ስፍራዎች የሚካሄዱ በመሆናቸው መንግስት ተጠያቂ የሚሆንበትን እድል ይፈጥራልም ብለዋል።

በመግለጫቸው 2004 ዓመተ ምህረት ላይ የወጣውን የሊዝ ህግ ለማስፈፀም 2005 ዓመተ ምህረት ላይ መመሪያ መውጣቱን አስታውሰዋል።

መመሪያውም ከ2005 ዓመተ ምህረት በፊት የተገነቡ ቤቶች ከሳይት ፕላኑ ጋር የሚጣጣሙ ከሆነ ህጋዊ እንዲሆኑ፤ ከፕላኑ ጋር የማይጣጣሙ ከሆነ ደግሞ እንደሚፈርሱ ያስቀምጣል። አሁን እየተወሰደ ያለው እርምጃም ከዚህ አንጻር መሆኑን ነው ያስረዱት።

እርምጃው ከመወሰዱ በፊትም የህገ ወጥ ግንባታዎቹ መንስኤና መፍትሄ ላይ ያተኮረ ጥናት ተደርጓልም ነው ያሉት በመግለጫቸው። በጥናቱም በአንዳንድ አካባቢዎች መንግስት ለአርሶ አደሩ ካሳ ከፍሎ ለልማት ባዘጋጃቸው ቦታዎች ላይ ህገ ወጥ ግንባታ መካሄዱንም ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም በቀበሌ ቤቶች ሳይቀር ግለሰቦች የፈለጉትን ዓይነት ግንባታ አከናውነው መገኘታቸውም በጥናቱ ተደርሷል። ግንባታው ህገ ወጥ መሆኑ እየታወቀ ግንባታ መካሄዱም ትልቁ ችግር መሆኑን ጠቅሰው፥ መንግስትም ህግ የማስከበር ስራ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በቅርቡ በአዳማ፣ በሻሸመኔ እና መቱ ከተሞች በሺዎች የሚቆጠሩ ህገወጥ ግንባታዎች መፍረሳቸውን በማንሳትም፥ እርምጃው በፍንፊኔ ዙሪያ ብቻ እየተወሰደ አለመሆኑን ገልፀዋል። ዶክተር ሚልኬሳ እርምጃ በተወሰደባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎቹ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ከአንድ አመት ጀምሮ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው እንደቆየም አስታውሰዋል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም ቅሬታ ያላቸው አካላት #ቅሬታቸውን ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በማቅረብ መስተናገድ ይችላሉም ነው ያሉት።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ይበቃናል‼️

በየዕለቱ አዳዲስ አጀንዳዎችን እየፈጠሩ ወደ ለውጥ፣ ልማት፣ ሰላምና አንድነት የምናደርገውን ጉዞ #እያደናቀፉ ያሉ አካላት አሉ። እነዚህን ቀንደኛ የሀገር ጠላቶች እና የጥፋት ሀይሎች አምርረን #ልንታገላቸው ይገባናል።

በቃን! በቃን! በቃን! ለብዙ አመታት በጦርነት ተሰቃይተናል፣ ሰዎች ገብረናል፣ ችግር አይተናል፣ ረሀብ ተፈራርቆብናል፣ ድህነት መጠሪያችን ሆኗል፣ ስማችን በዓለም ተዋርዷል፣ የሌላ ሀገር መሬትን ተመኝተን ባህር ገብተን ሞተናል፣ የበረሀ ሲሳይ ሆነናል፣ እርስ በእርሳችን እየተጋጨን የድህነትን ኑሮ ገፍተናል ወገኖቼ አሁን ግን ይበቃናል!!

•ችግሩ ይበቃናል
•ጥላቻው ይበቃናል
•ተንኮሉ ይበቃናል
•ሞቱ ይበቃናል
•ረሀቡ ይበቃናል
•መፈናቀሉ ይበቃናል
•ለቅሶው ይበቃናል
•ለመኖር መስጋቱ ይበቃናል
•ወጥቶ ለመግባት #መፍራቱ ይበቃናል

ኑ ያለፈውን ትተን ለመጪው እንስራ። ኑ ታላቅ እንሁን። ለኛ እንኳን ባይሆን ለልጅ ልጆቻችን ስንል ጠንካራ ሀገር #ገንብተን እንለፍ። ምንም ባናወርስ #ፍቅሯ#አንድነቷ#ሰላሟ የተረጋገጠች ሀገር እናውርስ!

አመሰግናለሁ!
ፀጋአብ ወልዴ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 13/2011 ዓ.ም. #ሼር #Share @tikvahethiopia

የለገጣፎ -ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር አረንጓዴ ቦታዎችን፥ የወንዝ ዳርቻዎችን፥ ከፈቃድ ውጭ የተያዙ እና ካሳ ተከፍሎባቸው ግንባታ የተካሄደባቸው ናቸው ያላቸውን ቤቶች እያፈረሰ ውሏል።
.
.
በሃዋሳ ከተማ ነገ ለሚካሄደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ #ይፋጠንልን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የሃዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
.
.
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በተሽከርካሪ አካል ውስጥ በረቀቀ መንገድ #ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረዬስ ጠብመንጃ እና ከ46 ሺ በላይ ጥይት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታውቋል፡፡
.
.
ዛሬ ጠዋት ጠቅላ ፍርድ ቤት የፌደራል ፖሊስ አቤቱታን ውድቅ በማድረግ ከእስር እንዲፈቱ ትእዛዝ የተሰጠላቸው አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው ሌላ ክስ ተመስርቶባቸው ማረሚያቤት ወርደዋል።
.
.
በምዕራብ ጎንደር ዞን #መቃ በተባለች አነስተኛ ከተማ በትንሹ 17 ሰዎች በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ነዋሪዎች #መታገታቸውን የዐይን እማኝ ተናግረዋል።
.
.
ነገ ለሚደረገው #ሰላማዊ_ሰልፍ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ከዞን ፖሊስ፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና #ከፌደራል_ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሰልፉ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቂ ጥበቃ ያደርጋል።
.
.
ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲንና ልዑካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
የደኢህዴን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ከየካቲት 12/06/2011 ዓ.ም ጀምሮ #በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
.
.
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ለተፈናቀሉ ወገኖች 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
.
.
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬድዮ /ኢሳት/ ጋዜጠኞች ዛሬ ኢቢሲን ጎብኝተዋል።
.
.
የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሁለት ቀናት  በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባም በአራት አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
.
.
አክሱም ሽረ እንደስላሴ መስመር ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ የትራፊክ አደጋው ከሽረ እንደስላሴ ወደ አክሱምና ከአክሱም ወደ ሽረ እንደስላሴ  ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች #በመጋጨታቸው ያጋጠመ ነው ተብሏል፡፡
.
.
በህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ዶክተር #ሚልኬሳ_ሚደግሳ ተናግረዋል።
.
.
በለገጣፎ_ለገዳዲ ከተማ ቤታቸው #የፈረሰባቸው ዜጎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ፣ OBN፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ🔝

ህገመንግሰታዊ #መብታችን_ይከበር በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ሰለማዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው። በሰለማዊ ሰልፉ ከሲዳማ 36 ወረዳዎች እና ከተማ መስተዳድሮች የተውጣጡ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ነው።

ሰለማዊ ሰልፈኞቹ “ህገ መንግስቱ ይከበር ! የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ መልስ ይሰጠው! የሪፈረንደም ቀን ይወሰን !” የሚሉና መሰል መፈክሮችን እያሰሙ ነው።

መነሻውን ከሀዋሳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ያደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በሀዋሳ ዓለምአቀፍ ስታዲየም መደረሻውን በማድረግ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክረሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዲን/ ከወራት በፊት ባደረገው በ10ኛ መደበኛ ጉበኤው የሲደማ ብሔር በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ተቀብሎ ለህዝበ ውሳኔ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መምራቱ ይታወሳል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለገጣፎ ለገዳዲ‼️

የለገጣፎው ቤት የማፍረስ ተግባር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር ደርሷል። Robel Tilahun ጉዳዩን ለ Adequate Housing ልዩ ራፖርተር ሊሊያና ፋራህ ካደረሰ በሁዋላ "ይህ አሳሳቢ ነው። በድርጊቱ ላይ ለተሳተፉት ማስገንዘብ የምፈልገው ሰዎችን ከመኖርያቸው በሀይል ማፈናቀል ቤት የማግኘት መብትን የሚፃረር ነው" ብለው ትዊተር ላይ ፅፈዋል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ🔝

ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት አዲስ አበባ #ካዲስኮ_አካባቢ እየተሰራ ያለ ግንባታ ነው። የህንፃ ግንባታው #የእግረኛ_መንገድ_እንዲዘጋ ምክንያት ሆኗል፤ የሚመለከተው አካል ሊደርስ የሚችለውን #የትራፊክ_አደጋ ከግንዛቤ በማስገባት የእርምት እርምጃ ቢወስድ መልካም ነው እንላለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia