TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ የመመርመር አቅምን በሚመለከት፦

- እስካሁን በአንድ ቦታ ነው ምርመራ እየተደረገ የሚገኘው። በEPHI ውስጥ ብቻ ነው።

- በሁለት (2) ሳምንት ውስጥ እስከ 25 በሚሆኑ ቦታዎች ላይ የምርመራ ስራው ይስፋፋል። በተለይም የክልል ላብራቶሪዎች ላይ እንዲስፋፋ ይደረጋል። አዲስ አበባ ውስጥም የግል የህክምና ተቋማት ላይም ይስፋፋል።

- በአጭር ጊዜ ውስጥ በመላው ሀገሪቱ ሰፊ ምርመራ የማድረግ አቅም ይፈጠራል፤ ይጠናከራል።

- ከተለያዩ ሀገራት የተገኙ የመርመሪያ መሳሪዎች አሉ፤ እነሱም ለዚህ አገልግሎት ይውላሉ።

- ቴስት ሲደረግ የቫይረሱ ተጠቂ ሊገኝም፣ ላይገኝም ይችላል በዚህ ወቅት ሳይታወቅ አልፎ ህብረተሰቡ ውስጥ ወርዷል? ወይስ አልወረደም የሚለው መለየት ይችላል።

- እስካሁን እየተሰራ ያለው በምልክት እና ከሰዎቹ ጋር ያላቸው ንክኪ ነው የሚታየው። ይሄ ይሻሻላል።

#DrDerejeDuguma #MoH

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrDerejeDuguma

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ህክምና ማገገሚያ ሊሆን ነው!

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ደረጄ ድጉማ በዛሬው ዕለት የሆስፒታሉን ዝግጅት በተመለከቱበት ወቅት ነው ሆስፒታሉ ሙሉ ለሙሉ የኮሮና ቫይረስ ህክምና የሚሰጥበት እንዲሆን መመረጡን የተናገሩት፡፡

(የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EkaKotebeHospital የኮሮና ቫይረስን በማከም ስራ ላይ ለተሰማሩ ሃኪሞችና ባለሙያዎች ከከፋ ዞን የአገር ሽማግሌዎች የማርና በግ ስጦታ ተበረከተላቸው። የከፋ ዞን አስተዳደርና የአገር ሽማግሌዎች በአዲስ አበባ ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ተገኝተው የኮሮናቫይረስን በማከም ስራ ለተጠመዱ ባለሙያዎች ግምቱ ከ100 ሺህ ብር በላይ የሆነ የማርና በግ ስጦታ ዛሬ አበርክተዋል። የከፋ ዞን የአገር…
#DrDerejeDuguma #DrYaredAgidew

የኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው ከከፋ ዞን አባቶች፣ ወጣቶችና የዞኑ አስተዳደር ስለቀረበላቸው ስጦታና መልካም ምኞት ምስጋና አቅርበዋል።

"እኛም ለእናንተ መልዕክት አለን" ያሉት ዶክተር ያሬድ፤ ''ለእኛ ያላችሁን ፍቅርና አክብሮት ራሳችሁን ከወረርሽኙ በመጠበቅ ልታሳዩን ይገባል'' ብለዋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ በበኩላቸው ''የከፋ ዞን የአገር ሽማግሌዎች ወረርሽኙን ለመከላከል ያደረጉት ድጋፍ ለሌሎችም አካባቢዎች አርዓያ የሚሆን ነው'' ብለዋል።

ከእነዚህ የከፋ ዞን ደግ አድራጊዎች በመማር በሌሎች ዞኖችና ወረዳዎች ያሉትም ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችል የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ኅብረተሰቡ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረግም ባለፈ ራሱን ከአካላዊ ንክኪ በመጠበቅ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrDerejeDuguma

በአዲስ አበባ ሁለተኛ ዙር በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ የቤት ለቤት የኮቪድ-19 አሰሳ መጀመሩን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ አሳውቀዋል።

አሰሳው ህብረተሰቡን ማስተማር እና የተገኙ መረጃዎችን በፍጥነት በማስተላለፍ በሽታውን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት እንደሚችል ዶ/ር ደረጄ ተናግረዋል፡፡

ለተጀመረው በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ የቤት ለቤት አሰሳ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ትብብር ማድረግ እንዳለበትም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር በዜጎች ዘንድ ፍቃደኛ ያለመሆን ፣ ቤት ዘግቶ የመጥፋት እና መልክቶችን መጨመርን ጨምሮ ሌሎች ያለመተባበር ችግሮች እንደተስተዋሉ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrDerejeDuguma

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ኪት ከአንድ ወር በኋላ ማምረት እንደሚጀመር #ለኢዜአ አስታውቀዋል።

ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ከአንድ ወር በኋላ ከቻይና መንግሥት ጋር በመተባበር የመመርመሪያ ኪት ለማምረት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለእዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ድጋፉን ከምታደርገው የቻይና መንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ እየመከሩ መሆኑን ገልጸዋል።

'የመመርመሪያ ኪቱን ሀገር ውስጥ ማምረት ሲጀመር ከውጭ የሚገባውን ኪት ሙሉ በሙሉ ያስቀራል' ያሉት ዶክተር ደረጀ ፣ ምርቱ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንደሚዳረስ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia