TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለወጣቶች⬇️

"ሰላም ፀግሽ! ትናንት ቀን ላይ 6 ሰዓት ገደማ ወደ 18 ማዞሪያ ዘመድ ጥየቃ ሄጄ ነበር፡፡ የሆነው ነገር አሳዝኖኛል! #እናቶች ህፃን ልጆቻቸውን ትተው እንደወጡ መግቢያ አተው፡፡ እኔም ያለ እቅዴ አደርኩ እኔ የነበርኩበት ቤት 3 ቤተሰብ አደሯል፡፡ 2 አራስ ልጅ ትተው ለጉዳይ ጠዋት የወጡ ናቸው፡፡ ሚያውቁት ሰው የሌላቸውን አስብ፡፡ እባካችሁ ወጣቶች ጊዜያዊ #ስሜት አይምራን! ሊከተል የሚችለውንም ሰከን ብለን እናስብ፡፡ ሀገር ወዳድ ዜጋ ለእናቶቹ፣ ለእህቶቹ፣ በአጠቃላይ ለወገኖቹ ሰላምና ነፃነት ቅድሚያ የሚሰጥ ነው፡፡ "ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ፡፡" መልካም ምሽት፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የብአዴን ተወካይ በህወሓት 13ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

⊙ የትግራይ እና አማራ ህዝቦች በደም የተሳሰሩ፣ እንዳይለያዩ ሆነው የተገመዱ ናቸው፡፡

⊙ የትግራይ #እናቶች ከአማራ የወጡ ታጋዮችን እንደልጆቻቸው ይንከባከቡ ነበር

⊙ ህውሃትና ብአዴን በአላማ የተሳሰሩ እራሳቸውን የቻሉ ድርጅቶች ናቸው

⊙ ማንኛውም ሰው በብሄሩ፣ በሀይማኖቱ የማይሞትባትን ኢትዮጵያ ለመገንባት ከፍተኛ ጥረት ልናደርግ ይገባል፡፡

⊙ ብአዴንና ህውሃት ሊለያያቸው የሚችሉ ጉዳዮች በመቀነስ አንድነቻውን ሊያጠናክሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ከቀድሞ በተለየ መስራት ይገባቸዋል፡፡

⊙ የህውሃት ጥንካሬ የብአዴን ጥንካሬ መሆኑን እናምናለን

⊙ በችግራችሁም በጥንካሬያችሁም ከጎናችሁ መሆናችንን እናረጋግጣለን

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቀለ ዩኒቨርሲቲ🔝

የኢትዮጵያ የሰላም አምባሳደር እናቶች #በመቐለ_ዩኒቨርስቲ ተገናኝተው ነበር።

"በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሰላም #እናቶች ልብ በሚነካ መልኩ በተማሪዎች መማሪያ ክፍል እየገቡ ተንበርክከው ስለ ሰላም አልቅሰዋል፤ ተማሪዎችንም ቃል አስገብተዋል።"

©ቀኔ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
* የቀጠለው የግጭት ይቁም ጥሪ !

በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት ካገረሸ ቀናት ያለፈ ሲሆን ግጭቱ ከቀን ወደ ቀን እየተባበሰ የሚደርሰው ጉዳትም እየጨመረ መጥቷል።

እስካሁን የቀረቡ የሰላም ጥሪዎችም ሰሚ ያገኙ አይመስልም።

በአሁን ሰዓት የአማራ እና የአፋር ክልሎች ዳግም ጦርነት እያስተናገዱ ዜጎችም ክፉኛ እየተሰቃዩባቸው ይገኛሉ።

እስካሁን ድረስ ዳግም ባገረሸው ጦርነት ንፁሃን ተገድለዋል፣ ተፈናቅለዋል ፣ በርካቶች በጦርነትና ስጋት ጭንቀት ላይ ወድቀዋል ፤ ዜጎች ተዘርፈዋል ፣ አቅም ያላቸው ሰላምን ፍለጋ በእግር ሊሸሹ ተገደዋል።

ያንን ከወራት በፊት የነበረን የጦርነት ወቅት ፈፅሞ ማስታወስ የማይፈልጉ #እናቶች ልጆቻቸውን ሰላም ወዳሉባቸው ቦታዎች ለማምጣት ዋጋ እየከፈሉ ነው።

ይህ ሁሉ በሚሆንበት በዚህ ወቅት ሰላም እንዲሰፍን እና ግጭት እንዲቆም በሀገር ውስጥ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጥሪዎች መቅረባቸውን ቀጥለዋል።

ዛሬ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

ኮሚሽኑ የግጭት ሰለባ በሆኑ አካባቢዎች ያለው ሲቪል ህዝብ ቀድሞ ከደረሰበት ስቃይ ያላገገመ ፣ የሚወዷቸው ያጣ፣ መሰረታዊ አገልግሎት ማግኘት ያልቻለ ማገገምን እና ፍትህን የሚጠብቅ ነው ብሏል።

ኢሰመኮ ሁሉም የግጭቱ ተሳታፊዎች ግጭት በማቆም ለሰላማዊ መፍትሄ የቆመውን ንግግር እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፤ በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመመርመር በተመድ የተቋቋመው ኮሚሽን ዳግም ግጭት መቀስቀሱ እንዳሳሰበው እና እንዳስቆጣው ገልጿል።

ግጭቱ ሰላማዊ ሰዎች ያለባቸው ችግር ይበልጥ ያባብሳል ብሏል። ሁሉም ወገኖች ውጊያ አቁመው ወደ ውይይት ይመለሱ ሲልም ጠይቋል።

(ተጨማሪ ከላይ ተይያዟል)

@tikvahethiopia