🕊ትግራይ አማራ የሰላም መድረክ🕊
የትግራይና አማራ ክልሎች የሰላም መድረክ #በመቐለ_ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ትላንት ተካሄደ፡፡ በመድረኩ የሁለቱን ህዝቦች ዘመናት የተሻገረ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠነክሩ፣ ስጋት ለፈጠሩ ክስተቶች መፍትሔ የተባሉ ሃሳቦች ቀርበውበታል፡፡
በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን ጨምሮ የተሻለ ምክረ ሀሳብ ለፖለቲካ መሪዎች ለማቅረብ በቀጣይነት እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡
የመድረኩ አስተባባሪና ጥናት አቅራቢ ዶክተር ገብረየሱስ ተክሉ የግጭት ስጋቶች ለማምከን ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና መገናኛ ብዙሃን ገንቢ ሚና መጫወት አለባቸው ብለዋል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የሚስተዋሉ #ግጭቶችና የግጭት ስጋቶች ለመከላከል ሁሉም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ፦ ጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tukvahethiopia