TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አብዲ ኢሌ ከእስር ለማምለጥ ሞክረው ነበር‼️

የሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ከእስር ቤት #መስኮት ሰብረው ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ሲል ፖሊስ ገለጸ።

አቶ #አብዲ_መሐመድ ከሐምሌ 26 ቀን እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ፥ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሳቢያ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

አቶ አብዲ ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀጠሮ ችሎት በቀረቡበት ወቅት፥ ለደህንነታቸውና ለጤናቸው ሲባል የፖሊስ ቢሮ ውስጥ ታስረው መቆየታቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ይሁንና አቶ አብዲ የታሰሩበትን ቢሮ መስታወት በመስበርና አንድ የጥበቃ አባልን ጉሮሮ በማነቅ ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ብሏል ፖሊስ በማብራሪያው።

አቶ አብዲ መሐመድ በበኩላቸው ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን በመጥቀስ፥ ሆን ተብሎ ስሜን ለማጥፋትና እኔን ለመምታት የተደረገ ሴራ ነው ብለዋል።

ድርጊቱን ፈጽመዋል መባሉ ውሸት መሆኑንና በእርሳቸው ላይም ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው እንደሆነም ተናግረዋል።

ምቹ ባልሆነ እስር ቤት መታሰራቸውን፣ የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነ ታሳሪ የታሰሩበትን ክፍል በር ገንጥሎ በመግባት ሁለት ቀን ጉዳት ሊያደርስባቸው እንደሞከረና ይህም በደህንነታቸው ላይ ስጋት እንደፈጠረባቸውም ገልጸዋል።

በአንድ አጋጣሚም አንድ እስረኛ የሽንት ቤት በር ገንጥሎ እሳቸው ላይ በመጣል ጉዳት ሊያደርስ መሞከሩንም ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

የታሰሩበት እስር ቤትም የማይመችና በጤናቸው ላይ እክል እንደፈጠረባቸውም ነው አቶ አብዲ የተናገሩት።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ አቶ አብዲ መሐመድ ማንኛውም እስረኛ በሚቆይበት እስር ቤት እንደታሰሩ ጠቅሶ፥ በእርሳቸው ላይ ምንም አይነት ጫና አለመደረጉን ገልጿል።

በተጨማሪም ፖሊስ ከእርሳቸው ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ለግጭቱ መቀስቀስ ተጠያቂ መሆናቸውንና በዚህም ተጸጽተው ይቅርታ መጠየቃቸውንም አስረድቷል።

ፖሊስ በአብዲ መሐመድ የክስ መዝገብ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ የ10 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱም ምርመራውን እያካሄደ ያለው ፖሊስ የምርመራውን ውጤት ለጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ.ም ይዞ እንዲቀርብ በማሳሰብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተማሪዎች ግጭት በወልደያ ዩኒቨርስቲ...

ትናንት ረቡዕ ሌሊት በወልደያ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት ከ10 በላይ ተማሪዎች መጎዳታቸው ተሰማ። በድንጋይ እና በዱላ በተደረገው ድብድብ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት አንድ ተማሪ ለከፍተኛ ህክምና መላኩ ተገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተፈራ አስናቀ በተለይ ለዶይቼ ቬለ DW እንደገለፁት፤ በግጭቱ ተማሪዎች ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ የመኝታ ክፍሎቻቸው #መስኮት እና #በሮችም ተሰባብረዋል። የፀቡ መነሻ ከሰሞኑ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከተፈጠሩ ግጭቶች ጋር ሳይገናኝ እንዳልቀረም አመልክተዋል።

በተመሳሳይ ከሰሞኑን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ግጭት ትምህርት የተቋረጠ ሲሆን ዛሬም ትምህርት እንዳልተጀመረ እና ተማሪዎችም ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር እየተወያዩ እንደሆነ ታውቋል። ሰሞኑን በደብረ ማርቆስ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች በተማሪዎች መካከል በተፈጠሩ ግጭቶች የሁለት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉ አይዘነጋም።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia