TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አከራካሪው ፍኖተ ካርታ!

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ትናንት ባወጣው #መግለጫ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የአማርኛ ቋንቋ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንዲሰጥ መደረጉና የ8ኛ ክፍል ፈተና ሃገራዊ መሆኑን #እንደማይቀበለው ማስታወቁን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የ8ኛ ክፍል ፈተናን ሃገራዊ ማድረግም የክልሉን ሥልጣን የሚጋፋ ነው ሲል #ተችቶታል

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ትናንት ባወጣው መግለጫ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የአማርኛ ቋንቋ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንዲሰጥ መደረጉና የ8ኛ ክፍል ፈተና ሃገራዊ መሆኑን #እንደማይቀበለው ማስታወቁን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የ8ኛ ክፍል ፈተናን ሃገራዊ ማድረግም የክልሉን ሥልጣን የሚጋፋ ነው ሲል ተችቶታል።

መግለጫው አክሎም "ፍኖተ ካርታው በምሁራን የተጠና ነው በሚል ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ሳይሰጥ ወደ ተግባር እየተለወጠ ነው" ሲል ይኮንናል። ፍኖተ ካርታው የተለያዩ የትምህርት ፖሊሲውን የሚነካ ሆኖ ሳለ የሃገሪቱ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮችና የፖሊሲ ለውጥ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች ውሳኔ #ሳያሳልፉና አስተያየት ሳይሰጡበት #ወደተግባር መግባታቸው ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጫው ተመልክቷል።

ከዚህ ባሻገርም ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ደረጃውን 6-2-4 ብሎ መግለጫ ከማውጣቱ በፊት በቂ ማብራሪያ መሰጠት ነበረበት ይላል። "ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ትምህርት የሚሰጠው በአፍ መፍቻ ቋንቋ ሆኖ ሳለ የ8ኛ ክፍልን ፈተና ሃገራዊ ማድረግ ምን አመጣው?" ሲልም ይጠይቃል። "የትግርኛ ቋንቋ ከአማርኛ ቋንቋ ጋር ይወራረሳል" የሚለው መግለጫው፤ የሰባት ዓመት ሕፃን እነዚህን ቋንቋዎች በአንድ ላይ መስጠት #ማደናገር ነው ብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-24-4

Via #BBC
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA🇪🇹 #በኢትዮጵያ_መንግስት እና #በህወሓት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ይዘት የሚገልፅ 12 ነጥብ ያለው #የጋራ_መግለጫ ከላይ ተያይዟል። ነገ ሁለት ዓመት የሚደፍነውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲበጅለትና ህዝቡም እረፍት እንዲያገኝ ፤ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ፣ አርሶ አደሮችም ወደ እርሻቸው ፣ ሰራተኞችም ወደ ስራቸው፣ ነጋዴዎችም ወደንግዳቸው እንዲመለሱ አጠቃላይ…
ስለ " ሰላም ስምምነቱ " ምን ተባለ ?

🕊 የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ኢትዮጵያ ለሰላም ያላት ቁርጠኝነት አሁንም የፀና መሆኑን ገልፀው " ስምምነቱ #ወደተግባር እንዲለወጥ አስፈላጊውን ትብብር ለማድረግ ጠንካራ አቋም / ቁርጠኝነት አለን " ብለዋል።

🕊 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (አንቶኒዮ ጉተሬዝ) ፦

በደቡብ አፍሪካ የተደረሰው የ " ሰላም ስምምነት " የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ህይወት የቀጠፈውና ሁለት ዓመት ያስቆጠረውን አስከፊ ጦርነት ለማስቆም ወሳኝ የሆነ የመጀመሪያ እርምጃ ነው ብለዋል።

#ሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል አመራሮች ለሰላም የወሰዱትን እርምጃ እንዲደግፉ አሳስበዋል።

የጦርነት ማቆም የሚሰጠውን እድል በመጠቀም ለተቸገሩ ሰላማዊ ዜጎች ሁሉ ሰብአዊ እርዳታን ከፍ ለማድረግ እና በጣም አስፈላጊ የህዝብ አገልግሎቶች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

🕊 አሜሪካ ፦

ከአፍሪካ ኅብረት፣ ተመድ፣ ኢጋድ እና ከሌሎችም ጋር በመሆን የተደረሰው ስምምነት #ተግባራዊ እንዲሆን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ድጋፏን እንደታደርግ ገልጻለች። የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር በሰሜን ኢትዮጵያ በጦርነቱ የደረሰውን ውድመት መልሶ ለመገንባት እና ለልማት ያላቸውን ፍላጎት እንደምትደረግፍም አሳውቃለች።

🕊 የአውሮፓ ህብረት (ጆሴፕ ቦሬል) ፦

የሰላም ስምምነቱ ባስቸኳይ ሊተገበር ይገባል ያሉ ሲሆን በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ ማቅረብ ፤ በትግራይ ክልል የተቋረጡ መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንደገና መጀመር #ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/ETHIOPIA-11-03

@tikvahethiopia
#ተስፋ

በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከምንም በላይ ለበርካታ ወራት የእናት አባቶቻቸውን ፤ የእህት ወንድሞቻቸውን ፣ የወዳጆቻቸውን ድምፅ ያልሰሙ እጅግ በርካቶች ስምምነቱ በፍጥነት #ወደተግባር ገብቶ ያናፈቋቸውን ሁሉ ድምፃቸውን ሊሰሙ ጓግተዋል።

ከዚህ ቀደም የባንክ አገልግሎት በመኖሩ እያገዟቸው የነበሩ መላ ቤተሰቦቻቸውን ዳግም አግኝተዋቸው የየትኛውም የእርዳታ ድርጅት እና ተቋም /አካል ደጅ እንዳይጠኑ ለማድረግና ያለባቸውን ችግር ለመቅረፍ እየተጠባበቁ ነው።

ቤተሰቦቻቸው " በህይወት ይኑሩ አይኑሩ " እርግጠኛ ያልሆኑ ሚሊዮኖች የሰላም ስምምነቱ እጅግ በፍጥነት ተተግብሮ ፣ መሰረታዊ አገልግሎት ጀምሮ ለማየት ተስፋን ሰንቀዋል።

ከማንም ከምንም በላይ የጦርነቱ ቀጥተኛ ተጎጂዎች ህመማቸው ፣ ናፍቆታቸው ፣ ሀዘናቸው የከፋ ነውና ይህ የሰላም ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን እና እፎይ እንዲሉ በተለይ #በማህበራዊ_ሚዲያ አፍራሽ ስራ የሚሰሩ ፣ የበለጠ ጥላቻን የሚዘሩ ፤ ሰላም በመሆኑ ጥቅማቸው የሚጎድልባቸው አካላት ከድርጊታቸው ቢታቀቡ መልካም ነው።

የሰላም ስምምነት መፈረሙ " የመጀመሪያው እርምጃ " እንጂ የመጨረሻ አይደለምና በተለይ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ለስኬቱ የራሳቸውን በጎ ድርሻ መጫወት ይጠበቅባቸዋል። በሰላም ሁሉም አሸናፊ ነውና ከብሽሽቅ ፣ ከጥላቻ ከአጉል የአሸናፊነት ስሜት መራቅ ይገባል።

#ሰላም

@tikvahethiopia