TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለሚመለከተው አካል⬆️

"በ12/1/2011 ከድሬደዋ ወደ አ/አ በባቡር ከብዙ #ሕፃናት ጋር ተጉዘን ማታ 1 ሰዓት ላይ መተሃራ አቅራቢያ ባቡር 13 ግመል #በመግጨቱ በግምት ያለመስማማት ምክንያት ከ15 ሰዓት በላይ ያለምግብና ውሃ ከሕፃናት ጋር በግመሉ ባለሃብቶች ታግተናል እስከአሁን 13/1/2011 ዓ/ም 5 ሰዓት ድረስ መፍቴ ስለኣላገኝን የሚመለከተው አካልም ሆነ መንግስት መፍትሄ እንዲወስድ እንጠይቃለን። ከተሳፋሪዎቹ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የምርመራ_ሪፖርት

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምሥራቅ ወለጋ ዞን ፤ " ጎቡ ሰዮ ወረዳ " አኖ ከተማ በጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በዋናነት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ኢላማ በማድረግ ጥቃት የተፈፀመ ሲሆን ይህ በተመለከተ #ኢሰመኮ ምርመራ አድርጓል።

ምርመራውን በተመለከተ ከላከልን መግለጫ ፦

- ጥር 25/ 2015 ዓ.ም. ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው የወታደር ልብስ የለበሱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) መሆናቸው በነዋሪዎች የተገለጹ ታጣቂዎች በ3 አቅጣጫ ወደ " አኖ ከተማ " መግባታቸውን፤ በመቀጠል በከተማዋ የተለያዩ አቅጣጫዎች ተከታታይ የሆነ የተኩስ ድምፅ መሰማት መጀመሩን እና የሲቪል ሰዎች ግድያና የአካል ጉዳት፣ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት መድረሱ ታውቋል።

- በጥቃቱ ዋና ኢላማ የተደረጉት ከ " ጎቡ ሰዮ ወረዳ " የተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች የተጠለሉ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ናቸው።

- በታጣቂ ቡድኑ በተፈጸመ ጥቃት አንድ የክልል የሥራ ኃላፊ ከነሾፌሩ፣ የከተማ ፖሊስ እና የቀበሌ ሚሊሻ አባላትን ጨምሮ ቢያንስ ሃምሳ (50) ሰዎች ተገድለዋል። ከእነዚም መካከል 42 ተጎጂዎች በተፈናቃዮች የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እና ከተቀባይ ማኅበረሰብ ጋር ተቀላቅለው ይኖሩ የነበሩ ተፈናቃዮች እንዲሁም መንግሥትን ይደግፋሉ የተባሉ ነዋሪዎች ነበሩ፡፡

- ከሟቾች መካከል አራት #ሴቶች እና ሦስት #ሕፃናት ናቸው፡፡

- ታጣቂዎቹ ‘ሰኞ ገበያ’ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ ተፈናቃዮችን ቤት ለቤት እየዞሩ በተለይ የአማራ ብሔር ተወላጆችን ለይተው ገድለዋል፡፡

- በከተማዋ ውስጥ የሚገኝ እና ቀደም ሲል የቀበሌ አስተዳደር ንብረት የነበረና ወደ አረጋውያን፣ ሴቶች እና ሕፃናት ተፈናቃዮች መጠለያነት ተቀይሮ በማገልገል ላይ ይገኝ የነበረ ግቢ ውስጥ በመግባት በፈጸሙት ጥቃት፤ በግቢው ውስጥ የነበሩ ማምለጥ ያልቻሉ ወንድ ተፈናቃዮችን መርጠው ገድለዋል። ከእነዚህም መካከል ከተገደሉ በኋላ #ሬሳቸው_በእሳት የተቃጠለ ሰዎች አሉ፡፡ በጥቃቱ ምክንያት ተፈናቃዮቹ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የተበተኑ ሲሆን መጠለያውም በጊዜያዊነት ተዘግቶ ነበር፡፡

- የሟቾችን አስከሬን ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት እና በማግስቱ የአካባቢው ማኅበረሰብ መቅበሩን የተጎጂዎች ቤተሰቦች አስረድተዋል።

- 8 ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

- በተፈጸመው ጥቃት በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የግለሰቦች የንግድ መደብሮች፣ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አኖ ቅርንጫፍ እና ሌሎች ተቋማት መጠነ ሰፊ ዘረፋ እና ውድመት ተፈጽሞባቸዋል፡፡ 

ሙሉ ሪፖርት ፦ https://t.iss.one/c/1370522004/23484

@tikvahethiopia