TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የትብብር ጥሪ፦

#በአርባምንጭ_ከተማ ለምትገኙ የሆቴል ባለቤቶች እና የህትመት ድርጅት ባለቤቶች፦

እኛ TIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በሀገራችን ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደጊዜ #በሚያስፈራ ሁኔታ እየተንሰራፋ የመጣውን የጥላቻ ንግግርን ለማስቆም ያለመ ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ የStopHateSpeech ዘመቻ እያከናወንን እንገኛለን። የመጀመሪያው ምዕራፍ ስራም በሁሉም የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሲሆን የመጀመሪያው ዝግጅትም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እጅግ በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።

ይህ ዘመቻ ያለምንም ድጋፍ በቻናሉ ብቻ ነው የተጀመረው፤ በመጀመሪያው ዝግጅትም ከፍተኛ ወጪ በግል አውጥተናል በተለይ ለህትመት እና ለፕሮግራም ዝግጅት። እኛ እንደግል ይህን ማድረግ ከቻለን ድርጅቶች በትንሹ ብትተባበሩን በርካቶችን በጥላቻ ንግግሮች እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መስራት እንችላለን። ሀሳብችንን ለሚደግፉ አካላት አሁንም ጥሪ እያቀረብን እንገኛለን።

በአርባምንጭ የምትገኙ የሆቴል ባለቤቶች እና የህትመት ድርጅቶች ይህን ሀገር አድን ጥሪ ሰምታችሁ የዘመቻው አካል በመሆን ከጎናችን እንድትቆሙና እንድትተባበሩን እንጠይቃለን።

ሰላም ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው!
ሁላችንም ከጥላቻ ንግግሮች እንቆጠብ!

ልትደግፉን የምትችሉ ፦ 0919 74 36 30 ላይ ደውሉልን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia