TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ስለ ጉራጌ ዞን ከDW⬇️

በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በምትገኘው ኢንሴኖ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት #በርካታ ሰዎች መሞታቸውን የአይን እማኞች ተናገሩ። የአይን ዕማኝነታቸውን ለDW የሰጡ የአካባቢው ነዋሪ የማረቆ ወረዳ ዘጠኝ ቀበሌዎች ወደ መስቃን ወረዳ መካከላቸውን በመቃወም ከትናንት በስቲያ ሐሙስ በተቀሰቀሰ ግጭት ከ20 በላይ ሰዎች ሞተዋል። አንድ የአካባቢው ባለስልጣንም ግጭት #መፈጠሩን እና ሰዎች #መሞታቸውን አረጋግጠዋል። 

በማረቆ ወረዳ ቆሼ ከተማ የሚኖሩ የአይን ዕማኝ በሰዎች ላይ ጥቃት ሲፈጸም፣ የመኖሪያ ቤቶች #ሲቃጠሉ መመልከታቸውን አስረድተዋል። "ጥቃቱን ለማስቆም ብንሞክርም አልተሳካልንም" ያሉት የአይን እማኙ "በሁለት ቀናት ሐሙስ እና አርብ ግፋ ቢል #ከ20 ያላነሰ ሰው ሞቷል። በማረቆ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ የሟቾችን አስከሬን አሁን አንቡላንስ እየሰበሰበው ይገኛል። ግማሹ በወራጅ ወሐም ተወርውሯል" ሲሉ አስረድተዋል።

የማረቆ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በለጠ ደራሮ ግጭቱ "የግል ፍላጎት ባላቸው አካላት እንደተቀሰቀሰ" ተናግረዋል። ግጭቱ "በመስቃን እና በማረቆ" መካከል የተፈጠረ አይደለም ያሉት አቶ በለጠ "መነሻው አልገባንም" ሲሉ ለDW አስረድተዋል። "በሰውም ላይም ጉዳት ደርሷል። በንብረትም ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሷል። በማረቆ አካባቢ በርካታ መስቃኖች አሉ። ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰባቸውም። ሽማግሌዎቹ፤ አመራሮቹ እነሱን መንካት እኛን መንካት ነው። እነሱ አልበደሉንም በስመ መስቃን ማንም መነካት የለበትም በሚል በትክክል ሐብቱ የሰው ማንነቱ ተከብሮ የመስቃን ተወላጅ ምንም አልተደረገም። የማረቆ ተወላጅ ግን መስቃን ውስጥ ጥቃት እየደረሰበት ነው። በንብረቱም ላይ በሕይወቱም ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየደረሰበት ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱ የተጠየቁት አቶ በለጠ "ይኸን ያህል የሚል የለንም። እየለየን ነው ያለንው" ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ በለጠ "የመንግሥት አካላት ሰራዊት በመላክ ጉዳዩ እየረገበ ነው። ልዩ ኃይሎችም አሉ። መከላከያዎችም አሉ። እነዚህ ንብረትም ሕይወትም የማዳን ሥራ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ከህዝቡ ጎን በመቆም ከዱርየው ጥቃት ሕዝቡን እያዳኑ ነው ያሉት" ሲሉ አክለዋል።

የቆሼው ከተማ ነዋሪ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የጸጥታ አስከባሪዎች በአካባቢው መሰማራታቸውን ገልጸዋል። "የጸጥታ አስከባሪዎች ወደ ቦታው ከተሰማሩ በኋላ የሰው ሕይወት እየጠፋ አይደለም" ያሉት አቶ በለጠ በበኩላቸው ውጥረቱ አሁንም እንዳልረገበ አስረድተዋል። ግጭቱ የተቀሰቀሰባት #የኢንሴኖ ከተማ ከአዲስ አበባ በ211 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ቡታጅራ አቅራቢያ ትገኛለች። በጉራጌ ዞን ሥር የሚገኙት መስቃን እና ማረቆ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በአንድ ወረዳ ሥር ይተዳደሩ ነበር።

©የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Dr.ABIY

"...እንድገደል የሚፈለግባቸው ጊዜዎች #በርካታ ናቸው!" የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ

"...መስቀል አደባባይማ #የቅርብ ነው። ብዙ ጊዜ ሞት እንደዚሁ ዝም ብሎ እያየሁት አላየሁም እያለ ይሄዳል ለዚህ ነው #ሞት የማልፈራው እኔም። ብዙ ጊዜ እድገደለ የሚፈለግባቸው ጊዜዎች በጣም በርካታ ናቸው። ባለፉት 7 እና 8 ዓመታት ብዙ ሙከራዎች ተደርገዋል። ለምሳሌ ባለቤቴ ከመሄዷ በፊት ኢንሳን ለቅቄ እንደወጣሁ በየጊዜው ማታ ማታ በግቢያችን ድንጋይ ይወረወርብናል ስንወጣ ለመምታት፤ ሌላም ብዙ ሙከራዎች ተደርገውብን ያውቃሉ ግን ሞት #አልፈለገኝም እስካሁን እንግዲ አንድ ቀን ሲመጣ..." ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በሸገር ቅዳሜ ጨዋታ!

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrLiaTadesse "ያለፈው ሳምንት እስካሁን ካሳለፍናቸው ሳምንታት የከፋ ነበር" - ዶክተር ሊያ ታደሰ በኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ብቻ 104 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸውን ተከትሎ ሣምንቱ "የከፋ ሳምንት" ነበር ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።  የጤና ሚኒስትሯ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።…
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ አሁን ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት የአኗኗር ሁኔታችንን እንድንቀይር ያስገዳል ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።

ዶ/ር ሊያ ዛሬ በሱጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው #በርካታ ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ እየተገኘባቸው ነው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ሳይኖራቸው ቫይረሱ የሚገኝባቸውም ሰዎች ቁጥር ጨምሯል ሲሉ ተናግረዋል።

የኮቪድ-19 ስርጭት ጎረቤት አገራት ጋር በማይዋሰኑ አካባቢዎችም ጭምር እየሰፋ መጥቷል ያሉት ዶክተር ሊያ 'ይህም አደጋው ወደ እያንዳንዳችን ቤት እየመጣ መሆኑን ያሳያል' ብለዋል።

'የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ሲከሰት በቀላሉ እየጨመረ የሚሄድ የስርጭት ባህሪ እንዳለው ጠቁመው ፤ ስርጭቱ ምን ያህል ይጨምራል የሚለው ጥያቄ ግን በእያንዳንዳችን ጥንቃቄ ይወሰናል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ያለፈው ሳምንት የቫይረሱ ስርጭት ሁኔታ ይህን በግልጽ ያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመሆኑም ከመደናገጥ ወጥተን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በሚጠይቀው ልክ የአኗኗር ባህሪያችንን መቀየር አለብን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

'መራራቅ ፣ መታጠብ ፣ መቆየት ፣ መሸፈን' የሚሉ አራቱ የኮቪድ-19 “መ” ህጎችን መተግበር ደግሞ ከእያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቅ የጥንቃቄ አማራጭ መሆኑ ዶ/ር ሊያ ገልፀዋል - #ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረባ የሆኑ የፖሊስ አባላት በኮቪድ-19 መያዛቸውን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል።

ጋዜጣው በኮቪድ-19 የተያዙት አባላት ለጊዜው ቁጥራቸው ባይታወቅም ነገር ግን #በርካታ እንደሆኑ ለማወቅ እንደቻለ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OromiaRegion

ጊምቢ ወረዳ በርካታ ሰዎች ተገደሉ።

በዛሬው ዕለት #በምዕራብ_ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ በርካታ ንፁሃን በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል።

መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በአካባቢው ይንቀሳቀሳል ያሉት የታጠቀ ቡድን ጥቃት ከፍቶ #በርካታ ሰዎች መገደለቸውን (ትክክለኛ ቁጥሩን ለማወቅ አዳጋች ነው) ታግተው የተወሰዱ መኖራቸውን እንዲሁም ነፍሳቸውን ለማትረፍ ወደ ጫካ የሸሹ ስለመኖራቸውን ገልፀዋል።

ከሟቾች መካከል ህፃናት እና ሴቶች እንደሚበዙ ፤ ቤቶች መንደዳቸውንም ፤ ጥቃቱ ሲፈፀም የነበረው በከባድ መሳሪያ ጭምር እንደነበር አመልክተዋል።

ለሚመለከተው የወረዳው አካል በሰዓቱ ጥቃት መኖሩን ጥቆማ ቢያደርሱም በቶሎ የደረሰ አካል እንዳልነበረ አስረድተዋል።

የዛሬውን እጅግ አሳዛኝ ጥቃት ክልሉም አምኖ አረጋግጧል። ጥቃቱን ጭካኔ የተሞላበትም ነበር ብሏል።

ክልሉ ባወጣው መግለጫ " የሸኔ ቡድን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ባደረሰው ጥቃት በንጹሃን እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል " ብሏል።

" ቡድኑ መንግሥት እየወሰደበት ያለውን እርምጃ መቋቋም ሲያቅተው በንጹሃን ላይ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት አድርሷል " ሲል ገልጿል።

በቡድኑ ላይ የፌደራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው ይቀጥላሉም ብሏል።

ክልሉ ምን ያህል ንፁሃን እንደተገደሉ እንዲሁም ታፍነው ስለተወሰዱ ሰዎች ምንም ያለው ነገር የለም።

@tikvahethiopia
ከ " ህገ ወጥ የቤቶች ግንባታ " ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን ያልተረጋጋ ሁኔታ ስርአት ለማስያዝ የህግ ማእቀፉን ቀድሞ መረዳት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ከከተማ መሬት አስተዳደር ጋር ተያይዞ የወጣ ህግ መኖሩን እና በህጉ ላይ ያለውን የግንባታ ፍቃድ አሰጣጥ በየደረጃው ያሉ የመንግስት ሀላፊዎች ሊረዱት እንደሚገባ በከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ገልጿል።

የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ኢትዮጵያ በዴቻ ለአሀዱ ሬድዮ ፍና ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፥ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ለሚሰራው ስራ እጃቸው የሚያርፍበት #በርካታ_የመንግስት_ሀላፊዎች በመኖራቸው ከግንባታ ፍቃድ አስጣጥ አንሰቶ የሚስተዋለው ችግር አንዱና ዋንኛው ምክንያት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

በመሰረታዊነት በህግ ማዕቀፉ ላይ ያለውን አሰራር በሚገባ በመረዳት ግንባታ ከመከናወኑ አስቀድሞ ሊጤን የሚገባው ጉዳይ እንደሆነም ነው የተናገሩት።

ከህገወጥ የቤቶች ግንባታ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች በዛን ረገድ የሰዎችን ህይወት ያልተገባ ሁኔታ ውስጥ ከማስገባታቸው አስቀድሞ አሰራሩን በመረዳት ተገቢው ውሳኔ ተግባራዊ ማድረግ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦ አሀዱ ሬድዮና ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
#Mekelle #AddisAbaba

• " ክልከላው ላይ የለንበትም ፤ መፍትሄ እንዲሰጥ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገርን ነው " - የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች

• " ስለተባለው ነገር መረጃ የለኝም። እኛ የምናውቀው ነገር የለም። ... ለአየር መንገዱ ከመንግሥት በኩልም ቢሆን ምንም አይነት ክልከላን የሚመለከት መመሪያ አልተሰጠውም " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

• " ዝርዝሩን ለማወቅ እናጣራለን " - የፌዴራል ፖሊስ

ካለፉት ሶስት ቀናት ወዲህ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ በሚደረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች በረራ ላይ በተለይም #ወጣት መንገደኞች እንዳይጓዙ ክልከላ ስለመኖሩ መንገደኞች እየገለፁ ይገኛሉ።

ትናንት ታህሳስ 30/2015 ዓ/ም ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ የአየር ቲኬት ቆርጠው አሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የተገኙት #በርካታ_ወጣቶች ጉዟቸው መሰረዙ ተሰምቷል።

መንገደኞች እንደሚሉት ከሆነ ክልከላው ከ16 ዓመት በላይ እና ከ64 ዓመት እድሜ በታች በተለይ ደግሞ ወጣቶችን ትኩረት ያደረገ ነው።

አንድ ቃሉን ለቢቢሲ የሰጠ መንገደኛ (የአዲስ አበባ ነዋሪ) ፤ " የልጆች እናት፣ የህክምና ሪፈር ያላቸው እና በእድሜ የገፉት ግን መሄድ እንደሚችሉ ነው የፌደራል ፖሊስ አባላቱ የነገሩን " ብሏል።

ይኸው መንገደኛ ፤ አዲስ አበባ ከተማ እንደሚኖር ፤ መታወቂያውም የአዲስ አበባ እንደሆነ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ እንደሄደና አስፈላጊውን መረጃ እንዳረበ ነገር ግን ሊቀበሉት እንዳልቻሉ አመልክቷል።

የአየር መንገዱ ሠራተኞች ክልከላው ከቁጥጥራቸው ውጪ እንደሆነ ነግረውናልም ብሏል።

አንድ መንገደኛ ደግሞ አዲስ አበባ የሚያስተዳድረው ተቋም መኖሩን የሚገልፅ መረጃ ካሳየ በኃላ በረራ እንደተፈቀደለት ለቢቢሲ ተናግሯል።

ክልከላው ከመቐለ በተጨማሪም #በሽረ ኤርፖርትም ስለመኖሩ ተገልጿል።

ጉዳዩን በተመለከተ ማን ምን አለ ?

የትግራይ ክልልን እያስተዳደሩ ያሉ አካላት ፤ ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ትግራይ ቴሌቪዥን) በሰጡት ቃል በዚህ ክልከላ እንደሌሉበት እና የክልከላው እርምጃ በፌደራል መንግስት የተወሰደ እንደሆነ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ዙርያ መፍትሄ እንዲሰጥ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገረ መሆኑን አሳውቋል።

#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያደቻ (ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል) ፦

" ስለተባለው ነገር መረጃ የለኝም። እኛ የምናውቀው ነገር የለም።

እንደምታውቁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእድሜና ጾታ ክልከላ የለውም። ምክንያቱም በሕግ እና በሥርዓት ነው የሚተዳደረው። እስከ ዛሬ እንዲህ አይነት ክልከላ የለንም። ወደ ድረ ገጻችን ብትገቡም ምንም አይነት ክልከላ እንደሌለ ታያላችሁ።

በተጨማሪም ለአየር መንገዱ ከመንግሥት በኩልም ቢሆን ምንም አይነት ክልከላን የሚመለከት መመሪያ አልተሰጠውም።

ምናልባት #የአካባቢው_መመዘኛ_ወጥቶ እንደሆነ የክልሉ ባለሥልጣናትን ብትጠይቁ የሚሻል ይመስለኛል።

በእኛ በኩል ግን እስካሁን የደረሰን ምንም አይነት መረጃ የለም። ከመንግሥት የተሰጠ ትዕዛዝም የለም። "

የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ (ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል) ፦

" መረጃው የለኝም።

ተጓዦች በእድሜ ተለይተው በአውሮፕላን እንዳይጓዙ ተከልክለዋል የሚለውን መረጃ አሁን ከእናንተ ነው የምሰማው።

ዝርዝሩን ለማወቅ እናጣራለን። "

በጦርነት ምክንያት ለረጅም ወራት ያህል ተቋርጦ የነበረው ወደ መቐለ እና ሽረ እንደስላሴ የሚደረገው የመንገደኞች በረራ በቅርቡ ዳግም መጀመሩ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#OROMIA

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፤ በኦሮሚያ ክልል በተለይ ከመስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ባሉት 2 ዓመታት ያደረገውን ክትትል እና ምርመራ መሠረት በማድረግ ከሕግ/ከፍርድ ውጪ የሆኑ እና በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ መሆናቸውን በማመላከት በተለይ የክልሉ እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት ማረጋገጥን ጨምሮ ዘላቂ መፍትሔ በአስቸኳይ እንዲሰጡ ጥሪ አድርጓል።

ይህን ጥሪ ያደረገው የሁለቱን ዓመታት ግኝቶች ይፋ ባደረገበት ባለ 11 ገጾች ሪፖርት ነው።

ኢሰመኮ ፦

የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች፣

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ኦነግ ሸኔ” በመባል የሚጠራው)

ኢ-መደበኛ የሆኑ የአማራ ታጣቂዎች ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕጎችን በመጣስ በግጭት ወይም በውጊያ ዐውድና ከውጊያ ዐውድ ውጭ #በርካታ ሲቪል ሰዎችን ከሕግ ወይም ከፍርድ ውጪ መግደላቸውን አረጋግጧል።

በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በሲቪል ሰዎች ላይ ለሚደርስ የመብቶች ጥሰት እንደ ዋነኛ ምክንያት የተገለጸው ፦

* በመንግሥት የጸጥታ አካላት በኩል " ለታጣቂ ቡድኖች መረጃ እና ሎጂስቲክስ ታቀርባላችሁ፤ የቡድኑ አባል ናችሁ " በሚል ምክንያት ነው።

* በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ "ኦነግ ሸኔ") በኩል " ለመንግሥት መረጃ ትሰጣላችሁ፣ የቤተሰብ አባላችሁ በመንግሥት ጸጥታ ኃይል ውስጥ እያገለገለ ነው ወይም ከእኛ ጋር በመሆን አልታገላችሁም/ድጋፍ አላደረጋችሁም " በሚል ምክንያት ሲቪል ሰዎችን ማጥቃት፣ ማንገላታት፤ ማገት እና ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማድረግ ነው።

* በኢ-መደበኛ የአማራ ታጣቂዎች ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰኑ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የአካባቢውን ነዋሪዎች በጅምላ " በኦነግ ሸኔነት " በመፈረጅ እና የክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የመሬት ይገባኛል ጥያቄዎችን በማንሳት በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ ዘረፋ እና ማፈናቀል እንደሚፈጸም ኮሚሽኑ ተገንዝቧል፡፡

(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
“ ... ‘ ልጄ በአጋቾች እየተሰቃየች ነው። ገንዘብ ካላክሽ ልጅሽን እንገድላታለን ’ አሉኝ። አጋቾቹ 300 ሺሕ ብር ጠየቁኝ ” - እንባ የሚተናነቃቸው እናት

የ20 ዓመት ሴት ልጃቸው በሳዑዲ አረቢያ እና የመን ድንበር በደላሎች እንደታገተችባቸው፣ አጋቾቹ የጠየቁት ገንዘብ ሰሞኑን ካልተላከላቸው እንደሚገድሏት ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን፣ አጋቾቹ ይህን ያሉት ከአንድ ቀን በፊት መሆኑን የታጋቿ እናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

እያለቀሱ ቃላቸውን የሰጡት እኚሁ እናት፣ “ ‘ልጄ በአጋቾች እየተሰቃየች ነው። ገንዘብ ካላክሽ ልጅሽን እንገድላታለን’ አሉኝ። አጋቾቹ 300 ሺሕ ብር ጠየቁኝ። ይህን ገንዘብ ለመላክ አቅሙ የለኝም። እባካችሁ ወገኖቼ ልጄን አድኑልኝ ” ሲሉ በውስጥም በውጪም ላሉ ወገኖች የእርዳታ ጥሪ አቅርበዋል።

አክለውም፣ “ ልጄም ‘እማዬ ገንዘቡን ካላክሽ ይገድሉኛልና እባክሽ ከዚህ ጉድ አውጪኝ’ አለችኝ። አጋቾቹም ‘ልጅሽ ያለችው በሳዑዲና የመን ድንበር ራጎ ነው’ የልጅሽን ደህንነት የምትፈልጊ ከሆነ ገንዘቡን ላኪ’ ብለው ስልኩን ዘጉት። ልጄን በሕይወት ላጣት ነው። እባካችሁ ወገን ድረሱልኝ ” ሲሉ ተማጸነዋል።

ልጃቸው ይህ ችግር የገጠማት ሕይወቷን ለመለወጥ ወደ ሳዑዲ አረቢያ #እየተሰደደች በነበረበት ወቅት መሆኑን ገለጸው፣ “ የቀን ሥራ እየሰራሁ ነው ያስተማርኳት። የልጄ ደህንነት አስጨንቆኛል። ወላጆች፣ እህት ወንድም ያላች ሁሉ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ እጃችሁን ዘርጉልኝ ” ሲሉ ተማጽነዋል።

የወጣቷን ቤተሰብ መርዳት ለምትፈልጉ በታጋቿ ወንድም መስፍን መኮንን ባዬ ንግድ ባንክ አካውንት 1000264883893 ዳግፋችሁን መላክ ትችላላችሁ።

የታጋቿ ቤተሰብ በስልክ ማነጋገር ለምትፈልጉ በ0945592726 ፍቅር ምስጋንን ማግኘት ይቻላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፥ ስለጉዳዩ ያነጋገራቸው አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ወደ ሳዑዲ የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያንን ደህንነት በተመለከተ በሳዑዲ አስተባባሪ በሰጡት ቃል ፣ “ራጎ ረግረጋማና ከባድ ምሽግ ነው። ደላሎች ተጓዦችን አግተው ከ250 ሺሕ ብር ጀምሮ ይጠይቃሉ ” ብለዋል።

እኝሁ አካል አክለውም ፣ #በርካታ_ኢትዮጵዊያን ስደተኞች “ #ራጎ ” በሌሎች አካባቢዎች በስቃይ እንደሚገኙ፣ ወጣቱ  ከእነዚህ ወገኖች ትሞህርት ወስዶ በእንዲህ አይነት መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ከመሰደድ እንዲቆጠብ አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia