#update የግብፅ የፀጥታ ኃይሎች 16 ታጣቂዎችን መግደላቸውን አስታወቁ።
የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በሰሜናዊ ሲና አሪሽ ከተማ በሁለት የማጥቃት ዘመቻዎች 16 ተጠርጣሪ ታጣቂዎችን #መግደላቸውን አል አህራምን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል። በመንግሥት ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበርም ነው በዘገባው የተመላከተው። ከታጣቂዎች መካከል 10ሩ በኦቤይዳት አካባቢ ስድስቱ ደግሞ በአቡ ኤታ ሰፈር ነው የተገደሉት። ቁጥሩ ያልታወቀ የጦር መሳሪያ፣ ፈንጂ እና ጥይት ታጣቂዎች በተገደሉበት ስፍራ መያዙም ተገልጿል። ግብፅ በሰሜናዊ #ሲና_በረሃ ከፈረንጆቹ 2013 ጀምሮ ጥቃት ከሚፈጽሙ ሰርጎ ገብ ታጣቂዎች ጋር ውጊያ እያደረገች ነው።
ምንጭ፦ ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia