TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አበኞች ግንቦት 7~ደብረ ማርቆስ🔝

"ጥፋትን በጥፋት ለማረም መሞከር ተገቢ አይደለም!!" ፕ/ር #ብርሃኑ_ነጋ
.
.
#የአርበኞች_ግንቦት_7 ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ታላቅ ህዝባዊ ዝግጅት በደብረማርቆስ ተካሄደ። የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የሀገር ሽማግሌዎችና ባልሰጣናትም በቦታው ተገኝተው ነበር።

አግ7 #የዜግነት_ፖለቲካ ብቸኛው ብሎም ሀገራችን ከገባችበት የዘርና የመከፋፈል አደጋ የምንወጣበት ስልት ነው ብሎ እንደሚያምን አመራሮቹ ተናግረዋል።

በአደባባይ የውጣው ህዝብ ለድርጅቱ ያላቸውን እምነት በመግለፅ መሪዎቹ ለሃጋራቸው ያበረከቱትን አስተዋጽኦ #አመስግነዋል

#አዘጋጆቹም ህዝቡን በማመስገን ህዝቡ ወደ ድርጅቱ የደብረማርቆስ ቢሮ እየመጣ እንዲመዘገብና አባል እንዲሆን ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ አግ7
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አግ7~ደብረ ማርቆስ🔝

''ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ከአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን እና ከብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን ጎን ልንቆም ይገባል'' አርበኞች ግንቦት ሰባት
.
.
በሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ከአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን እና ከብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን ጎን ልንቆም ይገባል ሲል የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ #አሳሰበ፡፡

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ከደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች፣ ከደጋፊዎቹ እና ከአባላቱ ጋር ዛሬ በደብረ ማርቆስ ከተማ ዉይይት አካሂዷል፡፡

የፓርቲዉ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር #ብርሃኑ_ነጋ የጎጃም ህዝብ በተለያዩ ጊዜያት ፍትሃዊ አሰራር እንዲሰፍን እንደ ሌሎች የሃገሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ ለለዉጡ መስዋዕትነት መክፈሉን ተናግረዋል፡፡

"ወገኖቻችን የደሙላት ፣ ህይወታቸዉን ያጡባትን ሃገር ሰላም አስጠብቀን ለልጅ ልጆቻችን ልናወርስ ይገባል፤ ይህ ካልሆነ ግን ወገኖቻችን ደግመን እንደገደልናቸዉ ነዉ የሚቆጠረዉ" ነው ያሉት፡፡

ሰላም የመኖርና ያለመኖር የህልዉና ጉዳይ በመሆኑ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን እና የብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን ለሚሰሩት ስራ ከጎናቸዉ ልንቆም ይገባልም ብለዋል፡፡

አብመድ እንደዘገበው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ጸሃፊ አቶ #አንዳርጋቸዉ_ጽጌ ስልጣን በህዝብ የተገነባ እንዲሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አና ጎሜዝ🔝

ሁሉም #ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ አስተዋጽኦ ስላለው አንዱ የበላይ አንዱ የበታች ነኝ ብሎ ማሰብ እንደሌለበት #አና_ጎሜዝ ተናገሩ። በኢትዮጵያ በ1997 ዓ/ም በተደረገ ምርጫ ታዛቢ የነበሩት አና ጎሜዝ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ስለአንድነት እንጂ ስለመከፋፈል ማሰብ የለባቸውም ብለዋል።

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት አባል የሆኑት ጎሜዝ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ለውጥ መጥቷልም ብለዋል። ይሁንና በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች ሚሊዮኖች #እንዲፈናቀሉ አድርገዋል ብለዋል። አና ጎሜዝ ኢትዮጵያውያን አንድነት ላይ ከሰሩ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንደሚችሉ ዕምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport በበርኒግሀም የቤት ውስጥ ሩጫ ውድድር በሴቶች 3 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀቁ፡፡ በዚህም #አልማዝ_ሳሙኤል በ8 ደቂቃ 54 ሰከንድ 60 ማይክሮሰከንድ አንደኛ ደረጃን በመያዝ  አጠናቅቃለች፡፡ #አክሱማዊት_እምባየ በ8 ደቂቃ 54 ሰከንድ ከ97 ማይክሮሰከንድ እና #መስከረም_ማሞ በ8 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ03 ማይክሮሰከንድ በመግባት ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡ ሌላኛዋ #ኢትዮጵያዊ አትሌት #እጅጋየሁ_ታየ በ8 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ28 ማይክሮሰከንድ በመግባት የአራተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ🔝

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ አባላት ከአዳማ አባ ገዳዎችና ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው። የአዳማ ከተማ አባ ገዳዎችና ነዋሪዎች ለኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ አባላት በአባ ገዳ አዳራሽ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በአሁኑ ስዓትም የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ አባላት ከአዳማ አባ ገዳዎችና ነዋሪዎች ጋር በአባ ገዳ አዳራሽ እየተወያዩ መሆኑን ከኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport ዛሬ #በመቀለ በተደረገው የመቀሌ 70 እንደርታ እና የባሕር ዳር ከነማ ጨዋታ ባለሜዳው መቀሌ 70 እንደርታ ባሕር ዳር ከነማን 1ለ 0 #አሸንፏል

@tsegabwolde @tikvahethiopia