#update አቶ በረከት ስምዖን⬇️
የAssociated Press ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ከአቶ በረከት ስምዖን ጋር ያደረገው ቃለ-ምልልስ።
(ከእንግሊዘኛ የተተረጎመ)
በኤልያስ መሰረት(AP)
=====☆☆☆======☆☆☆=====
▪️#ጥያቄ: በመጀመርያ ብአዴን ሰሞኑን እርስዎ ላይ ስለወሰደው እርምጃ እናውራ። እርምጃው የተወሰደበት አካሄድ ምን ይመስል ነበር? እርስዎስ እንዴት ያዩታል? ተቀብለውታል?
▫️አቶ በረከት : መሰረተቢስ እርምጃ ነው። እንዲታወቅ የምፈልገው እኔ ስብሰባው ላይ እንዳልነበርኩ እና ይህንንም ለእነርሱ ማሳወቄን ነው። ይህም የሆነው በአሁኑ ሰአት በክልሉ ላይ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ነው። በአሁን ሰአት ክልሉ ላይ የህግ የበላይነት የለም። እርግጥ እየሆነ ያለው የደቦ ፍርድ (mob justice) ነው። ይህንንም የክልሉ መንግስት መቆጣጠር የቻለበት ሁኔታ አይታይም። የተጠቀሰውን የንግድ ድርጅት በተመለከተ ስለተባለው ጉዳይ ያለኝ ሪከርድ ይመሰክራል።
በእኔ አስተዳደር ምንም #የጠፋ ነገር የለም። እንደ እኔ አስተሳሰብ ይሄ እርምጃ የመጣው አንደኛ ምክትል ጠ/ሚሩን በቅርቡ በተካሄደው የመተካካት ወቅት አለመደገፌ፣ በአቋሜ የማልደራደር ስለሆነ እና ፊት ለፊት ስለምናገር እንዲሁም የማጥራት አካሄድ (cleansing move) ነው። ምክንያቱም በረከት ከተለየ አካባቢ የመጣ ነው ስለሚባል ነው። እርግጥ ቤተሰቦቼ የኤርትራ ስር መሰረት ቢኖራቸውም እኔ ተወልጄ ያደግኩት ጎንደር ነው። የንግድ ድርጅቱን በተመለከተ አመታዊ የኦዲት ሪፖርት አለው። የእኛ ድርጅት ከኤፈርት ድርጅቶች አንደኛ ነው ታክስን በመክፈል ጨምሮ። በዚህ እኔ እርግጠኛ ነኝ።
▪️#ጥያቄ: በብአዴን የተወሰደውን እርምጃ ሲሰሙ አዘኑ፣ ደነገጡ ወይስ ሌላ ስሜት አጫረቦት?
▫️አቶ በረከት: ይሄ የሚጠበቅ ነገር ነበር። ይሄ ገና የመጀመርያቸው ነው (just a tip of the iceberg)። ወደፊት ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች ይመጣሉ ብዬ እገምታለሁ። እኔ ላይ ግን ምንም ችግር ይመጣል ብዬ አልፈራም ምክንያቱም ንፁህ ነኝ በዛ ላይ ለመብቴ እታገላለሁ።
▪️#ጥያቄ: የጠ/ሚር አብይን ፈጣን ለውጦች እንዴት ያዩዋቸዋል?
▫️አቶ በረከት: በእርግጥ ጠ/ሚሩ እየተገበሩት ያለው ለውጥ ኢህአዴግ ባለፈው ዲሴምበር ያሳለፈውን ነው። ሁላችንም የዚህ ለውጥ አካል ነበርን። ስለዚህ ስለ ለውጥ አስፈላጊነት ምንም ጥርጥር የለኝም። ጥሩ ለውጦች እያየን ነው።
▪️#ጥያቄ: ከሳምንታት በፊት እርሶ አሉበት ተብሎ የታሰበ በአማራ ክልል የሚገኝ ሆቴል እና መኪና ጥቃት ደርሶበት ነበር። ጥቃቱ አላስደነገጥዎትም? እርስዎስ በወቅቱ እዛ ነበሩ?
▫️አቶ በረከት: በወቅቱ እኔ #እቤቴ እንጂ እዛ #አልነበርኩም። ይህ የሚሳየው ግን በክልልሉ ያለው አስተዳደር ቁጥጥር ማጣቱን ነው። ህግ ያለው በቡድኖች እጅ ሆኖዋል።
▪️#ጥያቄ: የወደፊት የፖለቲካ ህይወቶ ምን ሊመስል ይችላል? ወይስ ፖለቲካ በቃዎት?
▫️አቶ በረከት: አሁን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ከእኔ ግለ- አስየሳሰብ ጋር አብሮ ስላማይሄድ አልቀጥልም። I'm thinking of coping with it Lidetu's style (የልደቱን ስታይል ለመከተል እያሰብኩ ነው)። አሁን ያለው ሁናቴ ፖለቲካን fair በሆነ መልኩ ለማካሄድ ያመቻል ብዬ አላምንም።
▪️#ጥያቄ: በቅርቡ የቀድሞው ጠ/ሚር ታምራት ላይኔ ባለቤት እርስዎ ላይ ወቀሳ ሰንዝረዋል። እርሳቸው በመታሰራቸው በእርግጥ ደስተኛ ነበሩ? ከሆነስ ለምን?
▫️አቶ በረከት: የእርሱ ጉዳይ በፍርድ ቤት ተወስኖ ከዛ ደሞ በህግ መሰረት ተፈቷል። 12 አመት ትምህርት ካላስተማረው እኔ ምንም ማረግ አልችልም። እስር ላይ የቆየው ባላደረገው ነገር አይደለም። ማንም ጣቱን ወደ እኔ አሁን ላይ ቢቀስር ለእኔ ምንም ማለት አይደለም።
▪️#ጥያቄ: አንድ ምክር ለጠ/ሚር አብይ ለግሷቸው ብልዎት እርሱ ምን ይሆናል?
▫️አቶ በረከት: እኔ እየሰራህ ያለውን ጥሩ ስራ ቀጥልበት ነው የምለው። ቃል የገባሀቸውን ነገሮችም ፈፅማቸው ልለው እወዳለሁ። ይህ የይቅርታ እና ምህረት ግዜ ወደፊትም መቀጠል አለበት። ዋናው ግን ይህ ሀገር sensetive ስለሆነ የ balance ስራ ሁሌ መሰራት አለበት። ጠ/ሚሩ እንዲሳካላቸው እመኛለሁ።
▪️#ጥያቄ: ጠ/ሚሩ ሹመት ሊሰጥዎ አስበዋል እንበል። ሹመቱን ይቀበላሉ ወይስ በተቃራኒው?
አቶ በረከት: በፍፁም! የእስካሁኑ ይበቃኛል።
📌ማሳሰብያ: ይህ ለAP ዜና ታስቦ የተደረገ እና አንድ ሁለት ፓራግራፍ ከእሳቸው ለማግኘት ታስቦ የተደረ ቃለ መጠይቅ ነው። ስለዚህ አላማው ለአለም አቀፍ ዜና መሆኑን ተረድታችሁ ይሄንን ሳይጠይቅ፤ ያንኛውን ሳያነሳ እንደማትሉ ተስፋ አረጋለሁ።
©ኤልያስ መሰረት(የAP ጋዜጠኛ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia

FAKE NEWS‼️
"ሰበር ዜና!! የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል president ሙክታር ከድር እና የቀድሞ አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ ዛሬ ከመኖሬያ ቤታቸው በፌደራል ፖሊስ #ተይዘዋል!!ምንጭ፦ OBN"
.
.
የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ #አድማሱ ወሬው #የሀሰት መሆኑን ለAPው ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት አረጋግጠዋል። አቶ አዲሱ አረጋም "fake news" ብለው በሜሴጅ ለአለም ኣቀፉ ጋዜጠኛ አሳውቀዋል።

ወ/ሮ ሰናይት...‼️
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ አንድ ፅ/ቤት በቅርቡ ሸገር ሬድዮ ላይ ቀርባ ስለ #መታወቂያ አሰጣጥ አስተያየቷን የሰጠችው ወ/ሮ ሰናይት ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ጋር በነበራት ቆይታ ይህን ብላለች፦
"ብዙ ተወርቶ እንደነበረው አስተያየቱን ለሸገር ሬድዮ ከሰጠሁ በሁዋላ ወደ ስራ አልተመለስኩም ነበር። ትናንት ግን #ወደስራ_ተመለሺ የሚል ደብዳቤ ተፅፏል። አሁን ወደ ቢሮ እየሄድኩ ነው። ውጤቱን በሁዋላ እነግርሀለው። ሰዎች #እያስፈሯሯት ነው ተብሎ በሶሻል ሚድያ የተወራው ግን #ሀሰት ነው። እዛ ደረጃ ነገሮች ከሄዱ ወደ መንግስት አካላት እና ሚድያዎች እሄዳለሁ!"

ጋዜጠኛ አሌያስ መሰረት~እናመሰግናለን!
TIKVAH-ETH ለጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ያለውን ልባዊ ምስጋና ለማቅረብ ይወዳል። አለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በፍቃደኝነት በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሰተኛ ዜናዎች በማጋለጥ፤ እንዲሁም ትክክለኛውን መረጃ ከምንጩ በመጠየቅ ሊደርሱ የሚችሉ በርካታ ጥፋቶችን መታደግ ችሏል።
"Fake News Alert" የምትለው መጠሪያም አሁን አሁን እጅግ በጣም እየተለመደች መጥታ በርካታ ሰዎች የሱን አርዐያነት በመከተለ ሀሰተኛ መረጃዎች የማጋለጥ ስራ እየሰሩ ናቸው።
ጋዜጠኛው በፍቃደኝነት በማህበራዊ ሚዲያ እየሰራ ላለው ትልቅ ሀገራዊ ስራ ምስጋና ይገባዋል! ቻናላችን እንደመረጃ ምንጭ ከሚጠቀማቸው #እውነተኛ የፌስቡክ ገፆች መካከል አንዱ የጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ገፅ ነው!
ለሀገርህ፤ ለኢትዮጵያ እየሰራኸው ላለው ስራ ከልብ ከልብ እያመሰገንን ዘውትር ከጎንህ ሆነን የምታጋልጣቸውን ሀሰተኛ መረጃዎችን ለቤተሰባችን የምናጋራ መሆን እንገልፃለን!
እግረ መንገዳችንን~ጋዜጠኛው ከሳምንታት በፊት ነው የተሞሸረው እንኳን ለዚህ አበቃህ፤ ትዳራቹ የአብርሃም የሳራ ይሁን! ፈጣሪ ትዳራችሁን ይባርክላችሁ ለማለት እነወዳለን!
የምስጋና ባህላችን ይደግ!!
የጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት መረጃዎች የሚገኙት በዚህ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው፦
https://www.facebook.com/Elias-Meseret-517243322140049/

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
ሰበር መረጃ‼️
ዛሬ ከሰአት በቃሊቲ መድህን ዲኮር አዳራሽ እንዲደረግ እቅድ ተይዞለት የነበረው "የአዲስ አበባ በለአደራ ምክር ቤት/ባልደራስ" ስብሰባ የፀጥታ ችግር ሊያጋጥመው እንደሚችል አሳማኝ መረጃ ስለደረሰን ለሌላ ግዜ የተላለፈ መሆኑን አንገልፃለን።
እስክንድር ነጋ ለጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት እንደገለፀው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ ከሰአት በቃሊቲ መድህን ዲኮር አዳራሽ እንዲደረግ እቅድ ተይዞለት የነበረው "የአዲስ አበባ በለአደራ ምክር ቤት/ባልደራስ" ስብሰባ የፀጥታ ችግር ሊያጋጥመው እንደሚችል አሳማኝ መረጃ ስለደረሰን ለሌላ ግዜ የተላለፈ መሆኑን አንገልፃለን።
እስክንድር ነጋ ለጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት እንደገለፀው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ናዝራዊት ቻይና ውስጥ #በሞት እንድትቀጣ አልተፈረደም!"
ቻይና ውስጥ ላለፉት #ሶስት_ወራት እፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ እስር ላይ ስለምትገኘው #ናዝራዊት_አበራ በዛሬው ዕለት የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ #ነቢያት_ጌታቸው ከአለም አቀፉ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ጋር ቆይታ አድርገው ነበር። የሰጡት መረጃምይህንን ይመስላል፦
"ቻይና ሀገር ያሉ የኛ የቆንስላ ፅ/ቤት ሰራተኞች ሶስት ግዜ እስር ቤት ሄደው አይተዋታል። የመጨረሻው ጉብኝት እንደውም ያለፈው አርብ ነበር። ላረጋግጥልህ የምችለው የሞት ፍርድ ተፈረደባት የሚባለው ውሸት መሆኑን ነው። ሂደቱ ገና ነው። የሀገሪቱ አቃቤ ህግ ገና ክሱን ያቀርባል። ከዛ በሁዋላ ነው ጉዳዩ ፍርድ ቤት ሄዶ የሚወሰነው። እስካሁን እፅ ነክ በሆነ ወንጀል ተጠርጥራ ነው ያለችው። እንደ ዜጋችን አሁን መጠየቅ የምንችለው የኮንሱላር ድጋፍ ማረግ ነው። እሱን ደሞ እያገኘን ነው። #ትክክለኛ_ፍርድ እንድታገኝ እና ጠበቃ የማግኘት መብት እንዲኖራት ክትትል ይደረግበታል። የፍርድ ደረጃ ላይ ሲደረስም clemency (ምህረት) የሚጠየቅበት ሁኔታ የተለመደ ነው። እነሱም ያሉን ጉዳዩ በቻይና ህግ የተያዘ ነው ብለውን ነው።"
ምንጭ፦ ETHIO-NEWSFLASH

ያያ ቪሌጅ ሪዞርት ማናጀር ዛሬ ጠዋት በስልክ በአለም አቀፉ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ጋር በስልክ ባደረጉት ቆይታ የሚከተለውን ብለዋል፦
"ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ አምስት የሪዞርቱ ሰራተኞች በጥርጣሬ ተይዘዋል። እነዚህ በወቅቱ የሆቴል ክፍሎችን ቁልፎች ይዘው የነበሩ ናቸው። አሻራ እና ቃል ሰጥተዋል። ምን ያህል ብር እንዲሁም ምን አይነት የእጅ ሰአት እንደተሰረቀበት አላወቅኩም። ሆቴሉ ካሜራ የለውም ስለዚህ ሰራተኞቹ በጥርጣሬ ነው የተያዙት። ሞ ፋራህ አሁንም በሪዞርቱ ይገኛል። ነገር ግን ፌስቡክ ላይ እንደፃፈው ሳይሆን እኛ በጣም ተባብረነዋል። ሶስት እና አራት ግዜ በየቀኑ ፖሊስ ጣብያ እኔ እራሴ እየተመላለስኩ ነበር። የምርመራው ውጤት እስኪያልቅ ትብብራችንን እንቀጥላለን።"

በአለም አቀፉ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት የታሰበ፦
"የሀገራችን አክቲቪስቶች፣ ተፅእኖ ፈጣሪዎች እንዲሁም opinion leaders ከቀናት በሁዋላ በአንድ ጠረጴዛ ዙርያ ቁጭ ብለው ይወያያሉ። የውይይቱ አላማ ምንም ያህል የተለያየ ሀሳብ ቢኖረን አንድ ላይ ቁጭ ብለን በጉዳዮቻችን ዙርያ ልንመክር እንደምንችል ማሳየት እና መፍትሄም መፈለግ ነው። ውይይቱ ላይ ለመካፈል እሺታችሁን ለለገሳችሁኝ ግለሰቦች እንዲሁም ለዚህ ፓነል ማካሄጃ የሆቴል አዳራሹን በነፃ ለፈቀደልኝ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ምስጋና አቀርባለሁ!"

#FakeNewsAlert
/ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/
አቶ አረጋዊ በርሄ "መቐለ ላይ ታሰሩ" ተብሎ በአንዳንድ ሚድያዎች የተዘገበው ዘገባ የሀሰት መሆኑ ታውቋል።

ሰኔ 15 ጦር ሀይሎች አካባቢ ምን ተከሰተ?
/ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/
ሰኔ 15 ቀን አመሻሽ ላይ በአማራ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ውስጥ ቦሌ አካባቢ የተከሰተው ግርግር እና ግድያ ብዙ ትኩረት ቢስብም #ጦር_ሀይሎች በተለምዶ ሲግናል (በድሮ አጠራሩ #መኮ) የተከሰተው ሁነት ግን እስካሁን ይፋ አልሆነም።
ጋዜጠኛ ኤልያስ ቢያንስ ሶስት ምንጮች አረጋገጡልኝ እንዳለው ጦር ሀይሎች አካባቢ በነበረው ግጭት ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። እስከ ለሊቱ ስድስት ሰአት ገደማም የጥይት ተኩስ ይሰማ ነበር። ይህ ክስተት በእለቱ ከነበሩት ሌሎች ግድያዎች ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ግልፅ አይደለም።
በቅርቡ ስለ ጉዳዩ በAPው ጋዜጠኛ የተጠየቁ አንድ የመንግስት የስራ ሀላፊ "ስለ ጉዳዩ መረጃ የለኝም። አጣርቼ መልስ ልሰጥህ እሞክራለሁ" የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።
በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ አለኝ ያለ አንድ ግለሰብ ለጋዜጠኛው ተከታዩን መረጃ አቀብሎ ነበር፦
"ስለ ሰኔ 15ቱ (የጦር ሀይሎች አካባቢ ጉዳይ) የተወሰነ መረጃ አለኝ። መረጃውን ላገኝ የቻልኩት ደግሞ በዛ ምሽት ከሞቱት ሶስት የፌዴራል ኮማንዶዎች አንዱ የአክስቴ ልጅ ስለነበር ሬሳ ለመቀበል ከቤተሰብ ጋር በሄድንበት ጊዜ የአሟሟቱ ጉዳይ ስለተነገር ነው። እናም ጉዳዩ ከጀነራሎቹ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠረ አንድ ኮሎኔል ለመያዝ በሄዱበት ጊዜ በተፈጠረው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ነው። ግን እስካሁን አንድ የመንግሥት አካል ስለ ጉዳዩ ምንም ነገር አለማለታቸው እጅግ በጣም አሳዝኖኛል።"
Via #EliasMeseret

የዕለቱ መልዕክት፦
እናስተውል!
/ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/
አሁን ላይ ሀገራችን ያለችበት ሁኔታ በእርግጥ በጣም ወደ #ከፋ ሌላ መንገድ ሊወስደን እንደሚችል በዚህ ወቅት መገንዘብ ካልቻልን ችግር ውስጥ ነን። #የመበታተን እና #የመጠፋፋት ምልክቶች እያየን ነው። ቤተሰብ ያለው ስለቤተሰቡ ያስብ፣ ሀገሩን የሚወድ የሀገሩ እጣ ፈንታ ያስጨንቀው፣ ህይወቱን የሚወድም እንዴት እሆናለው ብሎ ያሰላስል።
በስሜታዊነት እና በደመ ነፍስ የሚደረጉ ድርጊቶች እና የሚወሩ ጉዳዮች እዚህ አድርሰውናል። እነዚህ ነገሮች አሁኑኑ ካልተገቱ ሀገራችንን በምናውቃት መልኩ #በቅርቡ ላናገኛት እንችላለን።
ፖለቲከኞች ህዝብ ላይ #አትቆምሩ፣ ህዝቤ ፖለቲካ ቀነስ አርገህ ስራህ ላይ አተኩር፣ አክቲቪስቶች አደብ ግዙ፣ እኔን ጨምሮ ጋዜጠኞች ለማንም ሳንወግን ስራችንን እንስራ።
አሜን!
/ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/
ሰላም ህልውናችን ነው!
ሰላም እደሩ!!
🗞ቀን ሃምሌ 8/2011 ዓ/ም

#update በኦሮሚያ ክልል ውስጥ #በሚገኝ አንድ የኢንዱስትሪ መንደር በሰባት የቻይና ዜጎች ላይ በተፈፀመ የዘራፊዎች ጥቃት አንድ ቻይናዊ መገደሉንና ሌላ አንድ መቁሰሉን የቻይና ኤምባሲን ጠቅሶ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በጉዳዩ ላይ የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ #አሰግድ_ጌታቸው እሁድ ቻይናውያን ላይ ደረሰ ስለተባለው አደጋ ለጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ይህን ብለዋል፦ "ድርጊቱ የተፈፀመው አዳማ ኢንደስትሪ ፓርክ አቅራቢያ እሁድ አንድ ሰአት ገደማ ነው። እራት ከበሉ በሁዋላ በግሩፕ ወጡ። የሄዱበት ቦታ ከፓርኩ ሶስት ኪ.ሜ ርቀት ላይ ያለ ሲሆን ጭለማ እና ገደላማ ስፍራ ነው። የአካባቢው ሰው እንኳን አይሄድበትም። ለምን ወደዛ እንደሄዱ ገና እየተጣራ ነው። ከዛም ቻይናዎቹ እርስ በርስ እንደተወጋጉ ሟቹ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ተናግሮ ነበር። ከዛ በሁዋላ ግን ሌሎች ሰዎች እንዳረጉት ለማስመሰል ተሞክሯል። በጥርጣሬ የተወሰኑ ቻይናውያንም፣ የአካባቢ ሰዎችም ተይዘዋል። ዝርፊያ ስለተባለው ግን አላውቅም እነሱም ተዘረፍን ብለው ሪፖርት አላደረጉም።"

ችግኝ ተከላውን ጊነስ መዝግቧል❓
/ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/
"ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ የዛፍ ተከላ ሪከርዱን እንዲመዘግብ ተጋብዞ ነበር፣ ግን ለፕሮግራሙ አልደረሱም!" ሲሉ የግብርና ሚንስትር አቶ ኡመር ሁሴን ተናገሩ።
ሚኒስትሩን "ሰኞ የተተከለውን 343 ሚልዮን ችግኝ ጊነስ መዝግቧል ወይ?" ተብለው ከጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ለተጠየቁት ጥያቄ ይህን ምላሽ ሰጥተዋል፦
"አሜሪካ ባለው ኤምባሲ በኩል ጥሪ ደርሷቸው ነበር። አምባሳደር ፍፁም አረጋ ጉዳዩን ይዞት ነበር። ነገር ግን ለፕሮግራሙ አልደረሱም። ኮሚኒኬሽኑ ትንሽ ዘግየት ብሎ ነበር መሰለኝ። ተከላው እና የቆጠራ ሂደቱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የውጭ ዜጎችም እንዲያዩት ክፍት ሆኖ ነበር። ነገር ግን የኛ ሀሳብ ከዛ የዘለለ ነው። አሁን ይህንን ያህል ስራ ከሰራን መድገምም እንደምንችል እናውቃለን።"