TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የመንግስት ማስተባበያ⬇️

ኢትዮጵያ ጦሯን ከኤርትራ ድንበር እያነሳች ነው ተብሎ የተሰራጨው መረጃ #ሐሰት ነው ሲል መንግሥት አስተባበለ፡፡

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር በተለይም በሽራሮ ግንባር የሚገኘው ጦሯን ኢትዮጵያ እያነሳች እንደሆነ፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው አውቶብሶችና ኦራል ወታደራዊ የጭነት ተሽከርካሪዎች ጦሩን ሲያጓጉዙ መታየታቸውን፣ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲሰራጭ ነበር፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ የተጠየቁት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ መረጃው ሐሰት ነው ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

‹‹እውነት ነው ሽራሮ ግንባር ላይ እንቅስቃሴዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን የተለመደ አሠራር ነው ሲሉ፤›› ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ ላለፉት 20 ዓመታት ከነበሩበት የጥላቻ መንፈስ ተላቀው ሰላም ካወረዱ ጥቂት ወራት እየተቆጠሩ ሲሆን፣ በመካከላቸው ያለውን የጠላትነት ስሜት አጥፍተው በሰላም ለመኖር መስማማታቸው ይታወሳል፡፡ ከዚህ ባለፈ የኢኮኖሚ ትስስር ለመፍጠር፣ በተለይም ኢትዮጵያ የኤርትራን ወደቦች መጠቀም የሚያስችላት ስምምነት መደረጉ አይዘነጋም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በኤርትራ ድንገተኛ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

‹‹ሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ ያሉ ወታደሮቻቸውን ለማንሳት እስካሁን የተፈራረሙት ስምምነት የለም ሲሉ፤›› አቶ ሞቱማ አክለዋል፡፡

ሁለቱ አገሮች እንደገና ወዳጅነት የጀመሩት የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአልጀርስ ስምምነትን ሙሉ በሙሉ መቀበሉን ካስታወቀ በኋላ ነበር፡፡ እስካሁን ድረስ ይኼንን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የተጀመረ ሥራ ባለመኖሩ፣ ከድንበር ላይ ጦር የማንሳት እንቅስቃሴ ሊኖር አይችልም ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

©ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም የተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አብራሪዎች ሥልጠናን በተመለከተ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ዛሬ ያወጣውን ዘገባ «#ሐሰት» ሲል አስተባብሏል። የዩናይትድ ስቴትሱ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ በድረ-ገጽ ዘገባው፦ «የኢትዮጵያ አየር መንገድ የማክስ 8 ምስለ-በረራ (ሲሙሌተር) ነበረው፤ የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪ ግን ስልጠናውን አላገኘም» በሚል ርእስ ዘለግ ያለ ጽሑፉን አስነብቧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ ቅር መሰኘቱን በማኅበራዊ መገናኛ አውታሩ ዐሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎቹ ቦይንግ 737-8-ማክስን ማብረር ከመጀመራቸው በፊት፤ ቦይንግ-737 NG በሚባለው እና በቦይንግ-737 ማክስ መካከል ያለውን ልዩነት በቦይንግ ምክረ-ሐሳብ እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትሱ የፌዴራል የበረራ አስተዳዳር (FAA) ልዩነታቸውን አስመልክቶ ባጸደቀው መሰረት ሥልጠና ማጠናቀቃቸውን ገልጧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፦ የቦይንግ-737-ማክስ ሙሉ ምስለ-በረራ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የMCAS ሥልት ችግርን ምስለ-በረራ ለማድረግ ተደርጎ የተቀናጀ አይደለም ብሏል። የMCAS ሥልት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በአደገኛ መልኩ ወደላይ አስግገው መብረር ሲጀምሩ የአውሮፕላኖቹን አፍንጫ በራሱ ጊዜ ወደታች የሚጎትት ስልት ነው። በኢትዮጵያም ኢንዶኔዢያም የተከሰከሱት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የአደጋ መንስኤ አንዳንድ ግልጽ መመሳሰሎች እንደተገኘባቸው የኢትዮጵያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ #ዳግማዊት_ሞገስ በተለይ ለ«ጀርመን ራድዮ» ተናግረዋል። ደብረዘይት/ ቢሾፍቱ አጠገብ ወድቆ የተከሰከሰዉ አዉሮፕላን ሁለቱን ፓይለቶች ጨምሮ አሳፍሯቸዉ የነበሩ 157 ሰዎች በሙሉ አልቀዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNewsAlert

በሶማሌ ክልል መፈንቅለ መንግስት ተሞከሮ ከሸፈ መባሉ #ሐሰት መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።

የክልሉ የኮሙንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ ሂቦ መሃመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ እንዳሉት በክልሉ መፈንቅለ መንግስት ተደረገ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተናፈሰ ያለው መረጃ ሃሰት ነው ብለዋል።

ወሬውን የሰማነው ከማህበራዊ ድረገጽ ነው እንጂ የክልሉ አጠቃላይ አመራር በኮሮና ቫይረስ መከላከል ስራ ላይ እየተንቀሳቀሰ ያለው ሲሉ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"...ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የክብር ዶክትሬት የመስጠት ምንም አይነት ሃሳብ የለንም" - ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ እንደሆነ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች መረጃዎች እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በመረጃው ዙሪያ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የውጭ ግንኙነትና ፓርትነርሺፕ ዳይሬክተር የሆኑትን ማንእንዳንተ ሙሉጌታ (ዶ/ር) ጠይቋል።

"የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት የክብር ዶክትሬት ለመስጠት የሚያስባቸው ሰዎች አሉ። ገና በዕጩነት የቀረቡ ሰዎች አሉ፤ ይሁን እንጂ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዕጩዎቹ ዝርዝር ውስጥ የሉም" ብለዋል።

"በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚዘዋወረው መረጃም #ሐሰት" መሆኑን ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 300 በላይ ተማሪዎች ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም ማስመረቁ ይታወሳል።

ሌላ ዙር የምረቃ ስነ ስርዐት በመስከረም 2014 ዓ.ም መጨረሻ ወይም ጥቅምት 2014 ዓ.ም መጀመሪያ ሊኖር እንደሚችል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ይቀላቀሉ : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ተራዝሟል ? የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ግዜ አለመራዘሙን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ገልጿል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ሐምሌ 06/2013 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ፤ ፈተናው በጥቅምት አጋማሽ ይሰጣል ማለታቸው አይዘነጋም። ሰሞኑን ፈተናው የሚሰጥበት ቀን እንደተራዘመ…
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጥቅምት ወር አጋማሽ እንደሚሰጥ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አረጋግጧል።

ብሔራዊ ፈተናው ከሚሰጥበት ቀን ጋር ተያይዞ በርካታ ጥያቄዎች ለ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ @tikvahuniversity ደርሰው ነበር።

በጉዳዩ ዙሪያ የጠየቅናቸው የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ "የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ግዜ #አለመራዘሙን" በድጋሜ አረጋግጠዋል።

ሰሞኑን ፈተናው የሚሰጥበት ቀን እንደተራዘመ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው መረጃ #ሐሰት መሆኑን ገልጸዋል።

"ምንም የተቀየረ ነገር የለም" ያሉት ዳይሬክተሩ ፤ "ፈተናው በጥቅምት ወር አጋማሽ ይሰጣል" ብለዋል።

ተጨማሪ ተያያዥ መረጃዎችን ከካርድ / CARD ጋር በመቀናጀት በሚሰራው የቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገፅ ይከታተሉ : https://t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity
#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቹን አካውንት ለግዜው ያግዳል የተባለው ወሬ ሐሰት ነው አለ።

ንግድ ባንክ " መረጃ አሟሉ አልኩ እንጂ የባንክ ሂሳብ አግዳለሁ አላልኩም " ብሏል።

ዛሬ የደንበኞችን መረጃ የመሰብሰቢያ ቀን የመጨረሻ ነው የተባለውም #ሐሰት ነው ሲል ባንኩ ገልጿል።

የባንኩ የኮምዩንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ያብስራ ከበደ ባንኩ የደንበኞችን መረጃ ለመሰብሰብ አገልግሎቱን ለጊዜው ገደበ እንጂ አለማገዱን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኤቲ.ኤምና የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን መገደብ ያስፈለገው የብሔራዊ ባንክ ለሁሉም የግል ባንኮች የላከውን መመሪያ ለመተግበር በመገደዱ መሆኑን ተገልጿል።

ደንበኞች ለጊዜው በኤቲኤም እና በሞባይል ባንኪንግ የገንዘብ ማስተላለፍና ማውጣት አገልግሎት ባያገኙም ወደ ቅርንጫፍ መጥተው ሀብታቸውን እና ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ መታወቅ አለበት ብሏል ባንኩ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞችን መረጃ ለመፈለግ የመጨረሻው ቀን ዛሬ አርብ ነው የተባለው ትክክል እንዳልሆነ ባንኩ ገልጿል።

አክሎም " ደንበኞች በየቅርንጫፉ መጉላላት፣ መሰለፍ እና ጊዜያችሁን ማባከን የለባችሁም ባመቻችሁ ጊዜ ባንኩ የሚጠይቀውን መረጃ መስጠት ትችላላችሁ " ሲል ማሳወቁን #ሸገር_ኤፍ_ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀናት በፊት ባወጣው ማሳሰቢያ ላይ ደንበኞቹ እስከ መጋቢት 2 /2014 ድረስ አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጡ ከመጋቢት 2 /2014 በኃላ ግን ማንኛውም የባንክ አገልግሎት (የሞባይል ባንኪንግ፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ ፣ እንዲሁም የATM እና የፖስ አገልግሎት ማግኘት አይችሉም ብሎ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia