TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የወጣቶችድምጽ

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥር ያለባት ሀገር ናት።

ካለው ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥር አንጻር ያለው የስራ እድል አነስተኛ ነው። የስራ እድል ቢገኝ እንኳን የሚከፈለው ክፍያ ዝቅተኛ በሆኑ ህይወትን መቀየር እና ያሰቡትን ማሳካት ፈተና ነው።

በዚህ ምክንያት ብዙ ወጣቶች የተሻለ ኑሮና ገቢ ፍለጋ ከሀገር ለመውጣት ይፈልጋሉ።

ወጣቶቹ ያደጉ ሀገራት / በኢኮኖሚ የተሻሉ ሀገራት ሄደው ሰርተው ፣ ጥሩ ገቢ አግኝተው ለራሳቸው ተርፈው ፤ ዋጋ ለከፈለላቸውና ተቸግሮ ላሳደጋቸው ቤተሰባቸው እንዲሁም ለህብረተሰባቸው መድረስ እና ' አለሁላችሁ ' ማለት ይፈልጋሉ።

እድሜ ቆሞ አይጠብቅምና ፈጣሪ በሰጣቸው የወጣትነት ጊዜ ጉልበትና እውቀታቸውን ተጠቅመው ቢያንስ እነሱ ባይደላቸው ለልጆቻቸው የሚሆን ነገር ማስቀረት ትልቁ ምኞታቸው ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወጣቱ ዘንድ ከሀገር ወጥቶ ለመስራት የሚታየው ፍላጎት እጅግ በጣም መጨመሩን በተለያየ መንገድ ለመገንዘብ ችሏል።

በተለይ ወደ ካናዳ፣ ጣልያን፣ አሜሪካ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሳዑዲ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ሮማኒያ፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ... ሌሎችም የውጭ ሀገራት በትምህርት እና በስራ ለመሄድ ፕሮሰስ የሚያደርጉ በርካታ ወጣቶችን ማነጋገር ችለናል። ሀሳባቸውንም ተቀብለናል።

አንድ ካናዳ ለመሄድ በዝግጅት ላይ ያለ ወጣት ፥ " እኔ ከዩኒቨርሲቲ በትልቅ ውጤት ከተመረቅኩ አንስቶ ባለፉት 3 ዓመታት ያልሞከርኩት የስራ ሙከራ የለም ባለሁበት አካባቢ አጠቃላይ የቅጥር ሁኔታ ተስፋ አስቆራጭ ሆኖብኝ በግሌ ለመንቀሳቀስ ሞክሬ አይደለም ህይወቴን ላሻሻል ዳግም የቤተሰብ እጅ ጠባቂ ሆኛለሁ " ሲል ገልጿል።

" በዚህም ምክንያት ከሰዎች ብር አፈላልጌ ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ያለውን ነገር ሁሉ ለመስራት እየጣርኩኝ ነው " ብሏል።

ሌላኛዋ ወጣት በተመሳሳይ የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ስትሆን " በተግባር የስራ እድል ማግኘት አስቸጋሪ እየሆነ ነው ፤ የሚሰራው በትውውቅ በብሄር እና በዝምድና ነው እንዴት ይሄንን ማለፍ እንዳለበኝ አላውቅም " ብላለች።

ለበርካታ ወራት እዚሁ ሀገር ውስጥ ሆኖ ሰርቶ ለመቀየር በሚል ብዙ ሙከራ ብታደርግም ስላልተሳካ የውጭ ሀገር እድል እየሞከረች እንደሆነ አመልክታለች።

ሌላኛው ቃሉን የሰጠ ክሩቤል የተባለ ወጣት ፥ ምንም እንኳን በስራ ላይ በሚገኝም በወር የሚያገኘው ገቢ አነስተኛ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ትዳር ይዞ፣ የራሱን ሃሳብ አሳክቶ፣ ለቤተሰብ ፣ ለወገን ተርፎ መኖር የማይታሰብ ስለሆነበት ውጭ ሀገር ሰርቶ የመመለስ ፍላጎት እንዳለውና ይህን ለማድረግ እየሞከረ እንደሆነ ጠቁሟል።

ሌሎች ያናገርናቸው ወጣቶችም ባለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ፣ ስራም ለማግኘት የሚያደርጉት ጥረት ተስፋ ስላስቆረጣቸው ውጭ ሀገር ለመሄድና ማንኛውም ስራ ለመስራት ሲሉ እድላቸውን እየሞከሩ እንደሆነ ተናግረዋል።

" ማንኛውም ሰው ሀገሩን ጥሎ የሚወጣው ሀገሩን ጠልቶ ሳይሆን የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ነው " የሚሉት ወጣቶቹ በዚህ እድሜ ካልሰራን መቼ ልንሰራ ነው ? ሲሉ ጠይቀዋል።

ቃላቸውን የሰጡት ወጣቶች ፦
- በሀገር ውስጥ ያለው የስራ እድል እንዲሰፋ ፣
- በትውውቅ፣ በብሄር፣ በዝምድና የሚፈጸም ቅጥር እንዲቆም
- በገንዝብ የሚፈጸም ቅጥር እንዲቀር ካልተደረገ ወጣቱ እዚህ ሰርቶ የመለውጥ ተስፋው እንደሚሞት አስገንዝበዋል።

ሌላው " በሙስና የሚዘረፈው ብር ብዙ ነው እሱን ተከላክሎ ለወጣቶች አንዳች ነገር እንኳ ማድረግ ይቻላል ፤ ግን ዘራፊው የበለጠ ሃብቱን እያካበተ ወጣቱ የበለጠ ተስፋ እየቆረጠ ነው " ብለዋል።

አሁን ላይ በየመስኩ ሙስና መንሰራፋቱን ስራ ለመቀጠር፣ ጉዳይ ለመጨረስ እጅ መንሻ ካልተሰጠ እንደማይሆን በተግባር እንደተመለከቱ ጠቁመው ይሄ እያደር መዘዙ የከፋ ይሆናል ሲሉ አሳስበዋል።

" በሙስና በየአመቱ የሚዘረፈው የዚህች ሀገር ሃብት ለስንት ወጣቶች ህወይት መቀየሪያ ይበቃ ነበር ? " ሲሉም ጠይቀዋል።

ወጣቶች በሀገራቸው ላይ ሰርተው እንዲቀየሩ ምቹ ሁኔታ ከሌለ፣ እድሎችና ለስራ ለፈጠራ የሚሆን ሀቀኛ መደላደሎች ካልተፈጠሩ በሀገር ሰርቶ መቀየር አስቸጋሪ ስለሚሆን ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል።

" ፖለቲከኞችም ሆኑ ለሀገር እናስባለን ተፅእኖ ፈጣሪ ነን የሚሉ ሰዎችም የወጣቶችን የኢኮኖሚ ጉዳይ አጀንዳ ሊያደርጉ ይገባል ዘውትር እነሱን የሚጠቅም ነገር ካልሆነ የመናገር እና ተፅእኖ የመፍጠር ፍላጎት የላቸውም " ሲሉ ተችተዋል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ አ/አ)

#ቲክቫህኢትዮጵያ #የወጣቶችድምጽ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የወጣቶችድምጽ

" በየት በኩል እንስራ ? "

ከሰሞኑን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የኮንስትራክሽን እና ሌሎች ስራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ወጣቶች በምሬት አንድ ሃሳባቸውን አካልፈዋል።

" እንናገረውና ሰው ሰምቶት ይወጣልን ብለን ነው "  ሲሉ ስለደረሰባቸው ነገር አጋርተዋል።

እኚ ወጣቶች በክልል ከተሞች ተንቀሳቅሰው ለመስራት የሚታትሩ ናቸው።

ግን በብሄር፣ በዝምድና በትውውቅ የሚሰሩ ስራዎች ፈተና ሆነውባቸዋል። ተስፋም እያስቆረጣቸው ነው።

በቅርቡ ለአንድ ስራ ይወዳደራሉ ፤ ይህንን ስራ እንደሚያሸንፉ ባለሙሉ ተስፋ ሆነው ስራውን ለማሰራት ማስታወቂያ ወዳወጣው አካባቢና ቢሮ ያመራሉ።

ከአንድ ኃላፊ ተሰጠን ያሉት መልስ ግን " አትልፉ ፤ ይሄንን ስራ ወስዳችሁ ልትሰሩ የምትችሉ አይመስለኝም " የሚል ነው።

ይህ የሆነው ደግሞ " ከሌላ አካባቢ የመጡ ናቸው " በሚልና ከየት አካባቢ እንደመጡ በማጣራት እንደሆነ አስረድተዋል።

በዚህም " ከሌላ አካባቢ " በሚል አደገኛ አመለካከት ብቻ ስራውን ሌላ ሰው እንዲወስደው ስለመደረጉ በምሬት ተናግረዋል።

ድርጊቱ እጅግ እንዳሳዘናቸው ይሄ የብሄር፣ የዝምድና፣ የትውውቅ፣ የአካባቢ መርጦ ስራ ብዙ ወጣቶች አቅም እያላቸው እንዳይሰሩ እያደረገ ያለ እጅግ አደገኛ መርዝ መሆኑን ሳይናገሩ አላሉፍም።

ሌላ ቃላቸውን የተቀበልናቸው ወጣቶች ለስራ ጉዳይ ካለው የተንዛዛ ሂደት ባለፈ የዝምድና የትውውቅ ስራ ተስፋ አስቆርጧቸው ምን እንደሚያደርጉ ግራ እንደገባቸው ተናግረዋል።

በአንድ ሀገር በአንድ ባንዲራ ስር ከአንዱ ክልል ወደ ሌላው ሄዶ ስራ መስራት ፈተና እንደሆነና ስራዎች በዝምድና፣ ለተወላጅ፣ ለአካባቢ ሰው በትውውቅ እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።

" ሚዲያውም ሆነ ሌላው አካል እነዚህን መሰል ጉዳዮች ሳይሆን ለራሱ የገቢ ትርፍ እና ተመልካች የሚያስገኝለትን ጉዳይ እየመዘዘ ነው የሚሰራው " በማለትም ወቀሳ አቅርበዋል።

" ጨረታ፣ ውድድር በሚኖር ሰዓት እንኳን ዘመድ ያለው፣ ገንዘብ ያለው በእጅ አዙር ስራውን ያገኛል ይሄ ምንም የሚደበቅ አይደለም " ብለዋል።

ወጣቶች በፈለጉት ቦታ ተንቀሳቅሰው መስራት ካልቻሉ ሀገር ውስጥ እንዴት ይቀመጣሉ ? ቆይ በገፍ ቢሰደዱስ ምን ይገርማል ? ሲሉም ጠይቀዋል።

በዙሪያቸው ያለ እጅግ ብዙ ወጣት ባለው አሰራር ምክንያት ተማሮ ከሀገር ለመውጣት ብዙ እንደሚጥር ጠቁመዋል።

" አሁን ላይ ያለው ነገር ሁሉ ብሶበት ቁጭ ብሏል። የወጣቱን፣ የህዝቡን ድምጽ ሰምቶ ችግር ከማስተካከል ይልቅ ህዝብን ዝቅ ብለው እንዲያገለግሉ የተቀመጡ አካላት ሌላ ስም መስጠት እና መፈረጅ ስራቸው ሆኗል " ሲሉ አክለዋል።

ከአንድ ክልል፣  ዞን ፣ ወረዳ ሌላ ቦታ ሄዶ ለመስራት ችግር ከሆነና ስራው ሁሉ ብቃት ላለው ሳይሆን በብሄር፣ ትውውቅ፣ ዝምድና፣ በሙስና እየተመረጠ የሚሰጥ ከሆነ እንዴት ለውጥ ሊመጣ ይችላል ? ወደኃላ መጓዝ ማለትስ ይህ አይደለም ? ይህ የበርካታ ወጣቶች ጥያቄና ድምጽ ነው።

#TikvahEthiopia
#የወጣቶችድምጽ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM