TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ⬇️

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋለው #የመንጋ_ፍትህ እና አላስፈላጊ ሁከት ተቀባይነት የሌለው እና የህግ የበላይነትን አደጋ ውስጥ የሚጥል መሆኑን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በ11ኛው እነ 12ኛው ዙር የሰለጠኑ የመከላከያ መኮንኖችን ባስመረቁበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው።

በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ድርጊቱ የህግ የበላይነትን የሚነድ በመሆኑ በአስቸካይ ሊቆም እንደሚገባው ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ የተሳሳተ መረጃን መሰረት በማድረግ ለህግ ቅድሚያ ሳይሰጥ የሚፈጽማቸው ድርጊቶች እየተገነባች ያለችን ሃገር ከማፍረስ ውጭ ዋጋ እንደሌለውም ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ የህግ የበላይነት ለአንድ ሀገር ማህበረሰብ መጠበቅ መሠረት መሆኑንም በዚህ ወቅት ተናግረዋል።

ከዚህ አንጻርም መንግስት አሁን ላይ እየተስተዋለ ያለውን ከህግ በላይ የመሆን ዝንባሌ እንደማይታገስም አንስተዋል።

#እንደመር ስንል ባለፍንበት መንገድ ያጣነውን ለመመለስ እንጅ ሃገሪቱን ውጤት #ለከፋ_ቀውስ ለመዳረግ አይደለምም” ብለዋል በንግግራቸው።

መንግስትም እነዚህን ክስተቶች ለመቆጣጠር የመከላከል እና #ህግ የማስከበር ስራዎችን ይሰራልም ነው ያሉት።

©FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹በማህበራዊ ሚዲያ #የጥላቻ ንግግሮችን ለሚያወጡ ሰዎች #ህግ እያወጣን ነው፡፡››

◾️▪️ጠ/ሚ ዶክተር ዐብይ አህመድ▪️◾️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጫት ላይ የቀረበው ረቂቅ መግለጫ‼️

የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ #ልዑል_ዮሐንስ ለአማራ ክልል ምክር ቤት #በጫት ጉዳይ ላይ ያለውን ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡

አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ጫት በሃገራችን የጤናና ማህበራዊ #ቀውሶች እያስከተለ ነው፡፡

🔹ጫት ለተለያዩ በሽታዎች ይዳርጋል
🔹የዜጎችን ምርታማነትም ይቀንሳል
🔹ማህበራዊ ትስስርን ያስተጓጉላል
🔹ቤተሰባዊ መስተጋብርን ያዛባል
🔹ለሙስናና ብልሹ አሰራር መስፈንም የራሱ ድርሻ አለው፡፡

እናም፦

🔹የጫት ምርት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ወደ ሌላ ምርት እንዲሰማሩ ቢደረግ
🔹በጫት ንግድ የተሰማሩ ወገኖችን በመምከር ወደ ሌላ ንግድ እንዲሰማሩ በጎ ተጽእኖ ቢደረግ፤ ማበረታቻም ባይሰጣቸው የሚል መነሻ አቅርበዋል፡፡

የተነሱ ሃሳቦች፦

🔹የጫትን ማህበራዊና የጤና መሰናክሎችን ለማስቀረት ጠንከር ያለ አዋጅ በማዘጋጀት ለተግባራዊነቱ መስራት አለብን፡፡

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው -የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የጫት ጉዳይ አጀንዳ ያደረግነው ወጥ አቋም( አመለካከት) እንዲኖረን ነው፡፡

- ጫት ጉጂ በመሆኑ አምራቾችን እና ተጠቃሚዎች ጋር እንወያያለን ፡፡ በአንድ ጊዜ ማቆም አይቻልም፡፡ #እንዳይስፋፋ ይሰራል፤ ጫት የሚያመርቱ አርሶአደሮች ጫት የተሻለ ምርት የሚያስገኝ ምርት ላይ መሰማራት አለባቸው፡፡ ወደ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያመርቱ
#ማበረታታት አለበት፡፡

- ህበረተሰቡ ጋር ከተግባባን በኋላ #ህግ ወደማምጣቱ እንሸጋገራለን፡፡ ነገር ግን ጫት ትምህርት ቤቶች አከባቢ እንዳይሸጡ በአፋጣኝ #መወሰን ይቻላል፡፡

- በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከለከለ እፅዋት እየሆነ ነው፡፡ ጫትን የሚኮንነው ማህበረሰብ እየበዛ ስለሆነ ሌላ አማራጭ መፈለግ ፣ ማሳየት እና መደገፍ ያስፈልጋል፡፡

- ጫት የሚሸጥባቸው ቦታዎችን #የታወቁ ብቻ ሊሆኑ ይገባል፡፡

- ህብረተሰቡ ይህን አደገኛ ሁኔታ መከላከል አለብን በማለቱ ምክር ቤቱ መወሰኑ ተገቢ ነው፡፡

- ምክር ቤቱ በጫት ጉዳይ ተነሱ ሐሳቦች እንዲተገበሩ ምክረ ሀሳብ ወስኗል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የጥላቻ_ንግግሮች: የማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሆነው ትዊተር የጥላቻ ንግግር የሚነዙ ተጠቃሚዎችን ከገጹ እንደሚያግድ አስታወቀ። በተለይም ከሀይማኖት ጋር በተያያዘ ሰብአዊነትን የሚያጎድፉ ይዘት ያላቸው መረጃዎችና እና ጽሁፎችን የሚለቁ አካላትን ሙሉ በሙሉ ከገጹ እንደሚያግድ ነው ያስታወቀው። ኩባንያው ይህንን ለማድረግ የሚረዳው አዲስ #ህግ ማውጣቱም ተነግሯል።

በአዲሱ የትዊተር ሀግ መሰረት ከዚህ በፊት በገጹ የተለቀቁ የጥላቻ ንግግሮችም ከገጹ እንዲነሱ እንደሚደረግ ታውቋል። ሆኖም ግን ግለሰቦቹ የጥላቻ ንግግሮቹን የለቀቁት ህጉ ከመውጣቱ በፊት በመሆኑ ከገጹ እንደማይታገዱ ተነግሯል።

ትዊተር ከዚህ ቀደምም የመተግበሪያውን ህግና ደንብ የሚተላለፉ የሃገር መሪዎችና ፖለቲከኞች የሚያሰራጩትን መልዕክት ሊደብቅ መሆኑን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ትዊተር ይህን ውሳኔ ያሳለፈው የተለያዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች የመተግበሪያውን ህግና ደንብ በመጣስ ተገቢ ያልሆኑ መረጃዎችን ለተከታዮቻቻው በማሰራጨታቸው እንደሆነም ነው በወቅቱ የተጠቀመው።

ከዚህ በተጨማሪም #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው ተከትሎ ችግሩን ከስሩ ለማድረቅ ትዊተር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሀሰተኛ አካውንቶችን ማገዱም ይታወሳል።

ምንጭ፦ www.cnet.com---/#fbc/
🗞ቀን ሃምሌ 3/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia