TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ጥንቃቄ አድርጉ!

በሀዋሳ ከተማ #የኮሌራ በሽታ በመከሰቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የክልሉ ጤና ቢሮ አሳሰበ። የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀድራላ አህመድ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በከተማዋ ምልክቱ   ከታየባቸው 56 ሰዎች ውስጥ አራቱ በኮሌራ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በከተማዋ አዳሬ እና በሀዋሳ አጠቃላይ ሆስፒታሎች ጊዜያዊ የህክምና ማዕከላት መቋቋማቸውን እንዲሁም በአዳሬ ጤና ጣቢያ በቋሚነት ህሙማን የሚስተናገዱበት ልዩ ስፍራ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

በሽታው በንጽህና ጉድለት ምክንያት እንደሚመጣና በቀላሉ ተላላፊ በመሆኑ ህብረተሰቡ ያልበሰሉ ምግቦችን ከመመገብና ንጽህናው ያልተጠበቀ ውሀ ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳስበዋል። ለመጠጥ የሚጠቀመውን ውሀ #አፍልቶ በማቀዝቀዝ አልያም  በማከሚያ ዘዴ  እንዲጠቀም የማይቆም #ተቅማጥና #ትውከት ሲገጥመውም በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋም እንዲሄድም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SNNPRS

በደቡብ ክልል ወባና ኮሌራ የመሳሰሉ በሽታዎች ወደ ወረርሽን ደረጃ እንዳይሸጋገሩ ህብረተሰቡ ተገቢውን የመከላከል ስራ እንዲያከናውን የክልሉ ጤና ቢሮ አሳሰበ።

የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ በሀዋሳ እየተካሄደ ባለው የሴክተር መስሪያ ቤቱ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት የአካባቢ ቁጥጥር ስራው እየተዳከመ በመምጣቱ የወባ በሽታን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ እየተቻለ ከነአካቴው ወደ ወረርሽኝነት የማደግ ምልክቶች እየታዩ ነው።

በተለይ አመራሩ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ሲያከናውነው የነበረው የመከላከል ስራ እየተዳከመ በመምጣቱ በክልሉ መዲና ሀዋሳ ጭምር በሽታው በወረርሽኝ ደረጃ እየታየ መሆኑን አስረድተዋል።

ከወባ በተጨማሪ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች #የኮሌራ በሽታ መከሰቱን ገልፀው በሽታው የህዘቡ የጤና ችግር ሆኖ እንዳይቀጥል በሽታው በተከሰቱባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ባለሙያዎችና አመራሮች ጠንካራ የክትትልና የቁጥጥር ስራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
" የችግሩ ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየከፋ ነው "

በአማራ ክልል ፣ በሰሜን ጎንደር 202 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

በዞኑ በተከሰተው ድርቅ 452 ሺ ዜጎች መጎዳታቸው ተገልጿል።

የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ይፋ እንዳደረገው ፤ በዞኑ ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮ በተከሰተው ድርቅ 452 ሺህ ዜጎች ተጎድተዋል፤ 202 ሺህ ዜጎችም አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ከፅህፈት ቤቱ በተገኘው መረጃ ፦

- ጃናሞራ ፣ ጠለምት ፣ የበየዳ ወረዳዎችን ጨምሮ፣ ምሥራቅና ምዕራብ ጠለምትና የተወሰኑ የደባርቅ አካባቢዎች በድርቅ ተጎድተዋል፡፡

- ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮ ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ ሳቢያ 6 ወረዳዎች ለድርቅ ተጋልጠዋል።

- በድርቁ ሳቢያ 19 ሺህ 500 ሄክታር ሰብል ጉዳት ደርሶበታል።

- በዝናብ እጥረት 103 ሺሕ እንስሳት ለድርቅ አደጋ የተጋለጡ ሲሆን 53 ሺሕ የሚደርሱ እንስሳት በድርቁ ሳቢያ #ሞተዋል

- በጠለምትና ጃናሞራ ወረዳዎች በድርቁ ምክንያት ከ4 ሺሕ በላይ ዜጎች ከአካባቢያቸው ለቀው ወደ ወረዳ ማዕከላት ሄደዋል።

- ዞኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ድጋፍ ለማቅረብ ጥረት በማድረግ ላይ ነው ብለዋል፡፡

- በድርቁ አካባቢዎች ላይ ተላላፊ በሽታዎች በተለይም #የኮሌራ_በሽታ ተከስቷል።

- ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ ለሚገኙ ዜጎች አስቸኳይ የዕለት ምግብ፣ መድኃኒቶች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ውሃና የእንስሳት መኖ ድጋፍ አስፈላጊ ነው።

- የችግሩ ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየከፋ ነው። በድርቁ ሳቢያ ዜጎች ለከፋ ችግር እየተጋለጡ በመሆኑ ሁሉም አካላት እንዲረባረቡ ፤ መንግሥት፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ አጋር አካላት የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያቀርቡ መልዕክት ተላልፏል።

እስካሁን ምን ድጋፍ ተደረገ ? ፅ/ቤቱ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ክልሉ ከአንድ ሺሕ 500 ኩንታል በላይ የምግብ ድጋፍ ማድረጉንና ድጋፉን 14 ሺሕ ዜጎች ማድረስ እንደተቻለ ገልጿል።

Via EPA

@tikvahethiopia