የፍርሀት ደመና በድሬ ስማይ ስር‼️
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የድሬዳዋ ከተማ ከባድ የጸጥታና የደህንነት ችግሮችን ተጋርጦባታል። የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት #አብዲ_መሀመድ_ኡመር ከስልጣንናቸው ተነስተው ክልሉ በሰላም እጦት የታመሰ ሰሞን ድሬዳዋም #ከፍተኛ የጸጥታ ችግር አጋጥሟት ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታም መሞታቸው ይታወሳል።ይህ የሆነው ባለፈው አመት መጨረሻ ላይ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የከተማዋ ነዋሪዎች #በከፍተኛ_ስጋት ውስጥ እንዳሉ ይናገራሉ።
ስለጉዳዩ ዝርዝር ዋዜማ ራድዮ ያሰባሰበውን መረጃ ያንብቡት፦
https://telegra.ph/የፍርሀት-ደመና-በድሬ-ስማይ-ስር-01-25

Telegraph
የፍርሀት ደመና በድሬ ስማይ ስር፦
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የድሬዳዋ ከተማ ከባድ የጸጥታና የደህንነት ችግሮችን ተጋርጦባታል። የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት አብዲ መሀመድ ኡመር ከስልጣንናቸው ተነስተው ክልሉ በሰላም እጦት የታመሰ ሰሞን ድሬዳዋም ከፍተኛ የጸጥታ ችግር አጋጥሟት ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታም መሞታቸው ይታወሳል።ይህ የሆነው ባለፈው አመት መጨረሻ ላይ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የከተማዋ ነዋሪዎች በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳሉ ይናገራሉ። …
አብዲ ኢሌ‼️
ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ህግ በሶማሌ ክልል የቀድሞ ርእሰ መስተዳደር #አብዲ_መሀመድ የክስ መዝገብ ላይ የምስክሮች ማንነት ለተከሳሶች እንዳይገለጽ ያቀረበውን አቤቱታ ተቀበለ።
ከሀምሌ 28 እስከ 30 ቀን 2011 ዓ.ም በሶማሌ ክልል የተፈጠረውን ሁከትና ብጥብጥ በተመለከተ ምርመራ ተጠናቆ ክስ መመስረቱ ይታወሳል።
ክስ ከተመሰረተባቸው 47 ግለሰቦች ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሳቸው የተነበበላቸው አብዲ መሀመድ ዑመር፣ ራህማ መሀመድ ሀይቤ፣ አብዱራዛቅ ሰሀኔ ኢልሚ፣ ፈርሃን ጣሂር በርከሌ ናቸው።
ጉሌድ ኦበል ዳውድ እና ወርሰሜ ሼህ አብዲ የፍርድ ቤቱን የስራ ቋንቋ ባለማወቃቸው ምክንያት እስካሁን ድረስ ዐቃቤ ህግ ያቀረበባቸውን ክስ እንዲረዱት አልተደረገም።
ፍርድ ቤቱም ዛሬ በዋለው ችሎት የሶማሊኛ ቋንቋ አስተርጓሚ በቋሚነት እንደሚመደብ አዟል።
ከዚህ ቀደም በነበረው ችሎት ዐቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰው ምስክሮች ከተከሳሾች መዝገብ ጋር በማያያዝ በምስክሮች ላይ ሞራላዊ፣ አካላዊ እና የደህንነት ስጋት እንዳይደርስባቸው ጥበቃ ለማድረግ እና ህጉም የሚፈቅድ መሆኑን በማስረዳት የተከሳሾች ማንነትና አድራሻ እንዳይገለፅ በጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን ተቀብሎታል።
የተከሳሽ ጠበቆችም የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ለተከሳሾች እንዲገለጹ የተጠየቀበት ምክንያት የተከሳሾችን ህገ-መንግስታዊ መብት ለማስከበር እና ከጉዳዩ ጋር ለማጣጣም መሆኑን ነው ለፍርድ ቤቱ ያስረዱት።
የግራ ቀኙን ክርክር የተመለከተው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎትም ያልቀረቡ ተከሳሾችን እንዲቀርቡ ለመጠባበቅና ክሳቸው ያልተነበበላቸው በአስተርጓሚ እንዲረዱት ለማድረግ እንዲሁም ተገቢውን ትዕዛዝ ለመስጠት ለየካቲት 20 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙን ከፌደራል አቃቤ ህግ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።
ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia