#update በመጪው ቅዳሜ በጅግጅጋ ከተማ ለሚካሄደው ስምንተኛው ሀገር አቀፍ የከተሞች ፎረም አስፈላጊው ዝግጅት #መጠናቀቁን የፎረሙ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የፎረሙ ተሳታፊዎች በቆይታቸው የሚያርፉበት ስፍራዎችና አንድ ሺህ ሁለት መቶ የእንግዶ ማረፊያ ክፍሎች በከተማው በሚገኙ ሆቴሎች መዘጋጀታቸውም ታውቋል።
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሜቴክ ሀላፊዎች ላይ ክስ ተመሰረተ‼️
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ 71 ሚሊዮን ብር የመንግስት ገንዘብ አጥፍተዋል ባላቸው የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የቀድሞ ኃላፊዎች ላይ የሙስና ክስ መሰረተ። በሙስና የተጠረጠሩት ስድስት ኃላፊዎች ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሳቸውን አዳምጠዋል።
ጠቅላይ አቃቤ ህግ “ስልጣንን ያለአግባብ በመገልገል እና በከባድ የሙስና ወንጀል” የከሰሳቸው ኃላፊዎች ሌተናል ኮሎኔል ሰጠኝ ካህሳይ፣ ሌተናል ኮሎኔል መንግስቱ ከበደ፣ ሻለቃ ፍፁም አፅበሃ፣ ሻለቃ ዋልተንጉስ ተስፋው፣ ሻምበል ዊንታ በየነ እና ሻለቃ ክንድያ ግርማይ ናቸው። ተጠርጣሪዎቹ በሜቴክ ስር ባለ ሃይ ቴክ ኢንዱስትሪ በተሰኘ ድርጅት በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ ይሰሩ በነበረበት ወቅት በአስመጪነት ከተሰማሩ ባለሃብት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል እንደፈጸሙ በክሳቸው ላይ ተጠቅሷል። ስድስቱ ተከሳሾች ይመሩት የነበረው ድርጅት ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት "የኃይል ትራንስፎርመር እና ባለ ሶስት ፌዝ ተርሚናል ኮኔክተር" ለማቅረብ ውል ከገባ በኋላ ዕቃዎቹን የማቅረብ ስምምነቱን ያለ ጨረታ አቶ ወልዳይ ገብረማርያም ለተባሉ አስመጪ መስጠታቸው በክሱ ተገልጿል።
የዕቃዎቹን ግዢ ከኃላፊዎቹ ጋር በመመሳጠር “እጅግ በተጋነነ ዋጋ” ፈጽመዋል የተባሉት አቶ ወልዳይም 71.6 ሚሊዮን ብር “አላግባብ ጥቅም አግኝተዋል” በሚል “በልዩ ወንጀል ተካፋይነት” ተከሰዋል። ተጠርጣሪዎቹ የሜቴክ ኃላፊዎች በኮርፖሬሽኑ የግዥ መመሪያ መሰረት ዓለም ዓቀፍ ጨረታ ቢያወጡ ኖሮ እቃዎቹ የተለያዩ ወጪዎችን ጨምሮ በ14.3 ሚሊዮን ብር ብቻ ይገዙ እንደነበር አቃቤ ህግ በክሱ ላይ አመልክቷል። ሃይ ቴክ ኢንዱስትሪ በገባው ውል መሰረት እቃዎቹን በወቅቱ ማቅረብ ባለመቻሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ዓለም ዓቀፍ ጨረታ አውጥቶ በ12.3 ሚሊዮን ብር ዕቃዎቹን በቻይና ኩባንያ አማካኝነት ማስገዛቱም ተብራርቷል።
የሙስና ወንጀል ክሱን የሚመለከተው የከፍተኛው ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሾች ለቀረበባቸው ክስ የሚያቀርቡትን ምላሽ ለማድመጥ ለየካቲት 18 ቀን 2011 ዓ. ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ

በአዲስ አበባ 29 የቤት አልሚ ኩባንያዎች ቦታቸውን #እንዲነጠቁ ተወሰነ‼️
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ #ታከለ_ኡማ አስተዳደራቸው ባስጠናው ጥናት መሠረት ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡ 29 የቤት አልሚ (‘ሪል ኢስቴት’) ኩባንያዎች ቦታቸው ተነጥቆ በቤቶች ልማትና አስተዳደር በኩል በማኅበር ለሚደራጁ ኗሪዎች እንደሚያስተላለፉ መወሰኑን አስታወቁ።
ዛሬ፣ የካቲት 6 በጽሕፈት ቤታቸው የአጥኚ ቡድኑ ግኝት በቀረበበት ወቅት እንደተገለጸው ጥናቱ በቦሌ፣ በየካ፣ በንፍስ ስልክ ላፍቶ፣ በኮልፌ ቀራኒዮ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ቤት ለማልማት መሬት የተረከቡ ኩባንያዎች ላይ መካሔዱ ተጠቁሟል። በጥናቱ ውጤት መሰረት በአምስቱ ክፍለ ከተሞች መሬት ከተረከቡት ቤት አልሚ ኩባንያዎች መካከል 19 ኩባንያዎች የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ ቤት ገንብተው ለባለ ቤቶቹ ያስረከቡ ሲሆን 52ቱ ኩባንያዎች ደግሞ መካከለኛ አፈፃፀም በማስመዝገብ በተለያዩ የግንባታ ደረጃ ላይ የሚገኙ መሆኑም ታውቋል።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ

አቶ ኢሳያስ ከእስር #እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠ‼️
የሥር ፍርድ ቤት ማለትም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አሥረኛ ወንጀል ችሎት በ100 ሺሕ ብር ዋስ እንዲፈቱ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ፣ ትዕዛዙ በይግባኝ ታግዶ ለአንድ ወር ታስረው የከረሙት አቶ #ኢሳያስ_ዳኘው በተመሳሳይ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማክሰኞ የካቲት 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
የሥር ፍርድ ቤትን ትዕዛዝ በመቃወም የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ብሎ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመሄድ፣ በተጠርጣሪው ላይ ቀሪ ምርመራ እንዳለው በማስረዳት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር፡፡ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ግን ይግባኙን ውድቅ ሲያደርግበት፣ ሐሳቡን በመቀየር የክስ መመሥረቻ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡
ፍርድ ቤቱም አሥር ቀናት በመፍቀድ በተሰጠው ቀናት ውስጥ ክስ ማቅረብ ካልቻለ፣ የሥር ፍርድ ቤት ቀደም ብሎ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ተጠርጣሪውን ከእስር እንዲፈታቸው ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡
ዓቃቤ ሕግ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በተሰጠው አሥር ቀናት ውስጥ ክሱን መመሥረት ባይችልም፣ የሥር ፍርድ ቤት የክስ መመሥረቻ 15 ቀናት እንዲፈቅድለት አቅርቦ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪ ጠበቆች አስተያየት እንዲሰጡበት ሲጠይቅ፣ የሥር ፍርድ ቤት የበላይ ፍርድ ቤትን ትዕዛዝ መፈጸም እንጂ ያንን አልፎ የሚያከራክርበት ሥልጣን እንደሌለው በመግለጽ፣ ደንበኛቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሠረት ከእስር እንዲፈቱላቸው ጠይቀው ነበር፡፡
ዓቃቤ ሕግ በበኩሉ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 109(1) መሠረት ክስ የመመሥረቻ ጊዜና ቀናት ብቻ መሆኑን ቢደነገግም፣ በተለያዩ አዋጆች ተጨማሪ ጊዜ ማስፈቀድ የሚቻል መሆኑን ለማስረዳት ሞክሮ ነበር፡፡
ፍርድ ቤቱ ግን የሁለቱንም ወገኖች መከራከሪያ ሐሳብ በማለፍ፣ ቀደም ብሎ ከሰጠው ትዕዛዝ ውጪ ተጨማሪ ትዕዛዝ የመስጠት ሥልጣን እንደሌለው በመግለጽ፣ ተጠርጣሪው በሌላ ፍርድ ቤት አመልክተው ከእስር እንዲፈቱ ማድረግ እንደሚችሉ (HabeasCorpus) በመግለጽ መዝገቡን ዘግቶት ነበር፡፡
የተጠርጣሪው ጠበቆች በድጋሚ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለት፣ ቀደም ብሎ የሰጠው ትዕዛዝ ተግባራዊ አለመሆኑንና የሥር ፍርድ ቤት መዝገቡን እንደዘጋው በመግለጽ አመልክተዋል፡፡ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት ለዓቃቤ ሕግ የተፈቀደለት አሥር ቀናት ሲጠናቀቅ ተጠርጣሪን እንዲፈታ ትዕዛዝ መስጠቱን አስታውሶ፣ ግለሰቡ አቤቱታው እስካቀረበበት ቀን ድረስ (ከየካቲት 1 እስከ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ) ለሕገወጥ እስር መዳረግ እንዳልነበረባቸው በመግለጽ፣ ከእስር እንዲፈቱ በድጋሚ ትዕዛዝ መስጠቱ ታውቋል፡፡
ምንጭ፦ ረፖርተር

በትግል ብቻ እድሜያችን እንዳያልቅ‼️
በትግል ብቻ እድሜያችን #እንዳያልቅ ቆም ብለን #እናስብ። 24 ሰዓት መስራት፤ መልፋት አለብን፤ በርካታ ሀገራት ጥለውን እየሄዱ ነው(ጎረቤቶቻችን ሳይቀሩ)። #ህብረታችንን ለልማት እናድርግ፤ #አንድነታችንን ይህ አስቀያሚ የድህነት ኑሮ ለመቀየር እናድርግ!!
መልካም ምሽት~TIKVAH-ETH

#update እንቦጭ አረምን ለመቆጣጠር የተሰበሰበው 54 ሚሊዮን ብር እስካሁን ሥራ ላይ #አለመዋሉን ሸገር ዘግቧል፡፡ ከአምና ጀምሮ የአማራ ክልል ሃላፊዎች የሚመሩት የጣና ትረስት ፈንድ ተቋቁሞ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቡ ይታወሳል፡፡ ቦርዱ እስካሁን በተለያዩ ቸግሮች ሳቢያ ብሩን ፈሰስ ማድረግ አልቻለም ነበር፡፡ በቅርቡ ግን 23 ሚሊዮን ብር ያህል ለመልቀቅ ወስኗል፡፡ ገንዘቡ አረሙን በጉልበታቸው ለሚያሰወግዱ የአካባቢው አርሶ አደሮች ክፍያ፣ ለጀልባ ግዥና ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ለጀመረው አረም የሚበላ ጥንዚዛ ማራባት ሥራ ይውላል፡፡ አሁን እንቦጭ የወረረው የሐይቁ ስፋት 2 ሺህ 300 ሄክታር ያህል ይገመታል፡፡
Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦነግ ሰራዊት አባላት‼️
ከ1 ሺህ በላይ የሚሆኑ የኦነግ ሰራዊት አባላት ወደ ተዘጋጀላቸው #ካምፕ ገብተዋል።
የሰራዊት አባላቱ ጦላይን ጨምሮ በኦሮሚያ ክልል በተዘጋጁ የተለያዩ ካምፖች በመግባት #ስልጠና እየወሰዱ ነው።
ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የሰራዊት አባላቱ፥ የተደረገላቸው የሰላም ጥሪና እየታየ ያለው የፖለቲካ ለውጥ ለሃገርና ህዝብ ጥቅም በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።
በሃይል ትግል ማድረጉም ለህዝቡ ስለማይጠቅም ሰላማዊ የትግል መንገድ መምረጣቸውንም ነው የተናገሩት።
ከዚህ በተቃራኒው የትጥቅ ትግልን አማራጭ በማድረግ በሃይል የሚንቀሳቀስ ቡድን አካሄድ ተቀባይነት እንደሌለውም ገልጸዋል፤ ለውጡን ለማስቀጠል መናበብና መመካከር አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ።
ከዚህ ባለፈም የበርካቶች ህይወት ያለፈበትን ትግል ማደናቀፍ እንደማይገባ የጠቀሱት አባላቱ፥ የአንድ ሃገር እድገትን ለማረጋገጥ በሰላማዊ መንገድ መታገል አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል።
በትጥቅ ትግል ላይ ለሚገኙ ሌሎች ጓዶቻቸውም ትጥቃቸውን ፈተው ሰላማዊ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የጦላይ ስልጠና ማዕከል አስተባባሪ ኮሚሽነር ፀሃይ ነጋሽ በበኩላቸው አባላቱ በህገ መንግስቱ፣ በፌደራሊዝሙና በሃገራዊ ለውጡ ዙሪያ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ

#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድና ም/ጠ/ሚር #ደመቀ_መኮንን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለዉጥ የጋራ ኮሚቴ ጋር የካቲት 6 ቀን 2011 ተወያዩ። ካለፈው የቀጠለው ይህ ውይይት በዋናነት የኮሚቴውን የስራ እንቅስቃሴዎችና የተገኙ ውጤቶችን ገምግሟል። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድም ኮሚቴው ያስመዘገባቸውን ውጤቶች እንዲያጠናክር አቅጣጫ በመስጠት የበኩላቸውን ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በስልጤ ዞን ዛሬ ቢያንስ 2 ሰዎች የገደሉ‼️
በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን ገርቤ በር ወረዳ ባሎቀሪሶ በተባለ ቦታ በዛሬው ዕለት በአካባቢው ነዋሪዎች እና በጸጥታ አስከባሪዎች መካከል በተቀሰቀሰ #ግጭት ቢያንስ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን የዐይን ዕማኞች ተናገሩ። በግጭቱ የቆሰሉ ወደ ወራቤ ሆስፒታል ተወስደዋል። የጀርመን ራድዮ ያነጋገራቸው ሶስት የዐይን እማኞች እንደተናገሩት ሁለት ሰዎች የተገደሉት የጸጥታ አስከባሪዎች በተኮሱት ጥይት ነው። ግጭቱ ዛሬ ጠዋት አራት ሰዓት ገደማ መቀስቀሱን የተናገሩ የዐይን እማኝ "የሞተ ሁለት ነው። ግን በርካታ ቆስሏል። የቆሰለውን ይኸን ያህል አልለውም። በርካታ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
አንድ ሌላ የዐይን ዕማኝ የሟቾቹ ቁጥር ሁለት መሆኑን #አረጋግጠው የግጭቱ መነሾ ለኢንቨስትመንት የታጠረ ቦታ ሊሰጠን ይገባል የሚል ጥያቄ በወጣቶች በመቅረቡ እንደሆነ አስረድተዋል። የዐይን እማኙ የአካባቢው ወጣቶች ታጥሮ የተቀመጠን ቦታ ለማፅዳት ሲሞክሩ "ግብግብ ተፈጥሮ አንድ ሁለት ሰው ሞቷል" ብለዋል። "ከዚህ በፊት ለኢንቨስትመንት የተሰጠ መሬት ነበር። የተሰጠው ባለሐብት ሶስት አመት ሙሉ አጥሮት ነው ቁጭ ያለው። ምንም የሰራው ነገር የለም" የሚሉት የዐይን እማኝ የአካባቢው ወጣቶች በተደጋጋሚ ቦታው ሊሰጠን ይገባል የሚል ጥያቄ ከወረዳ እስከ ክልል አቅርበው ነበር ብለዋል።
"ጠዋት ሁለት ሰዎች ሞተዋል። ቤቶችም ተቃጥለዋል" ያሉ ሶስተኛ የዐይን እማኝ በበኩላቸው በግጭቱ የቆሰሉ ሰዎች ወደ #ወራቤ_ሆስፒታል መወሰዳቸውን ተናግረዋል። ከቆሰሉ መካከል የጸጥታ አስከባሪዎች ይገኙበታል ተብሏል። የዐይን ዕማኞቹ የጸጥታ ኃይሎች ወደ ከተማዋ ከገቡ በኋላ የመረጋጋት አዝማሚያ ይታያል ብለዋል።ወጣቱ ተጭኖ ተጭኖ እየሔደ ነው። ግጭት የተቀሰቀሰባት የገርቤ በር ወረዳ በስልጤ ዞን ከወራቤ ከተማ በ13 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ትገኛለች።

‹‹በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከ80 ሺህ በላይ ዜጎች #ተፈናቅለዋል፡፡›› የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት
.
.
የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዛሬ በሠጠው መግለጫ ተፈናቃዮችን ለመርዳት ክልሉ 35 ሚሊየን ብር በመመደብ ድጋፍ ሲደረግ ቢቆይም አሁን ላይ ያለውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቋቋም ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ እንደሆነ ገልጻል፡፡
ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮች ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው #ተፈናቅለዋል፡፡ በአማራ ክልልም ከክልሉ ውስጥና በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ ከ80 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የክልሉ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡
የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ.ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ እንዳሉት ከክልሉ ውጭ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልሎች እንዲሁም በክልሉ ውስጥ ደግሞ በተለይም በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር አካባቢዎች ዜጎች በስፋት ተፈናቅለዋል፡፡
የመፈናቀል አደጋው ከተከሰተበት በተለይም ከሕዳር ወር ጀምሮ የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥት በጋራ ተፈናቃዮችን በጊዜያዊና በዘላቂነት ለማቋቋም 35 ሚሊየን ብር በመመደብ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ያስታወሱት አቶ አሰማኸኝ ‹‹አሁን ላይ ያለውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቋቋም ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ ሆኗል›› ብለዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ ለሰፋ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ሥነ ልቦናዊ ችግሮች በመጋለጣቸው ዘላቂ ድጋፍ እና እንክብካቤ እንደሚያስፈልጋቸው ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡ ይህንንም ለማድረግ የክልሉ መንግሥት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሚመራ ግብረ ኃይል አቋቁሞ ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፤ ‹‹ድጋፉ በተደራጀ እና በአንድ አግባብ እንዲሆን ይፈለጋል›› ሲሉም አሳበዋል፡፡
የሚደረገው ድጋፍ በገንዘብ፣ በዓይነት እና በዕውቀት ሊሆን እንደሚችል ያስረዱት አቶ አሰማኸኝ ከዚህ ቀደም ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በማመስገን በተከፈተው የሒሳብ ቁጥር ሕዝቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
#የገንዘብ_ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ አካላት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአደጋ መከላከል ፕሮግራሞችና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000258250811 እንዲሁም በዓይነት ድጋፍ ለማድረግ ለሚፈልጉ አካላት በስልክ ቁጥሮች 0582180196፣ 0582181096፣ 0582181151፣ 0918701136፣ 0918340128 ወይም 0953600333 በመደወል መረጃ ማግኘት እንደሚቻል አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ አብመድ