#update እንቦጭ አረምን ለመቆጣጠር የተሰበሰበው 54 ሚሊዮን ብር እስካሁን ሥራ ላይ #አለመዋሉን ሸገር ዘግቧል፡፡ ከአምና ጀምሮ የአማራ ክልል ሃላፊዎች የሚመሩት የጣና ትረስት ፈንድ ተቋቁሞ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቡ ይታወሳል፡፡ ቦርዱ እስካሁን በተለያዩ ቸግሮች ሳቢያ ብሩን ፈሰስ ማድረግ አልቻለም ነበር፡፡ በቅርቡ ግን 23 ሚሊዮን ብር ያህል ለመልቀቅ ወስኗል፡፡ ገንዘቡ አረሙን በጉልበታቸው ለሚያሰወግዱ የአካባቢው አርሶ አደሮች ክፍያ፣ ለጀልባ ግዥና ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ለጀመረው አረም የሚበላ ጥንዚዛ ማራባት ሥራ ይውላል፡፡ አሁን እንቦጭ የወረረው የሐይቁ ስፋት 2 ሺህ 300 ሄክታር ያህል ይገመታል፡፡
Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia