TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል~ሀዋሳ🔝

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የአደሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ እንዲያስችለው በ220 ሚሊዮን ብር ባለ ስምንት ፎቅ የማስፋፊያ ህንፃ ግንባታ እያከናወነ መሆኑን ገለፀ፡፡

የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ እንደገለፁት በ2009 ዓ.ም የተጀመረው የህንፃው ግንባታ ሲጠናቀቅ እስካሁን በነባሩ ሆስፒታል የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጨምሮ ለሆስፒታሉ በቅርብ ርቀት ለሚገኙ የክልሉና የኦሮሚያ አጎራባች ዞኖች የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ያስችለዋል፤ የሆስፒታሉ ግንባታ ከቦታ መረጣና ከግንባታ ዕቃዎች ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ በታሰበበት ጊዜ #ባይጠናቀቅም ባሁኑ ወቅት ከ25 በመቶ በላይ ሥራው መከናወኑን አቶ ሙንጣሻ ገልፀዋል፡፡

ሆስፒታሉ በነባሩ የአገልግሎት መስጫው 130 አልጋዎች ያሉት ሲሆን የማስፋፊያ ስራው ሲጠናቀቅ የአልጋ ቁጥሩን 300 በማድረስ እንዲሁም የባለሙያዎችና የመሣሪያ ግብአቶችን በተሻለ ሁኔታ በማሟላት ለተሻለ አገልግሎት እንደሚበቃ ዋና ስራ አስኪያጁ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ የጤና ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia