TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል~ሀዋሳ🔝

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የአደሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ እንዲያስችለው በ220 ሚሊዮን ብር ባለ ስምንት ፎቅ የማስፋፊያ ህንፃ ግንባታ እያከናወነ መሆኑን ገለፀ፡፡

የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ እንደገለፁት በ2009 ዓ.ም የተጀመረው የህንፃው ግንባታ ሲጠናቀቅ እስካሁን በነባሩ ሆስፒታል የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጨምሮ ለሆስፒታሉ በቅርብ ርቀት ለሚገኙ የክልሉና የኦሮሚያ አጎራባች ዞኖች የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ያስችለዋል፤ የሆስፒታሉ ግንባታ ከቦታ መረጣና ከግንባታ ዕቃዎች ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ በታሰበበት ጊዜ #ባይጠናቀቅም ባሁኑ ወቅት ከ25 በመቶ በላይ ሥራው መከናወኑን አቶ ሙንጣሻ ገልፀዋል፡፡

ሆስፒታሉ በነባሩ የአገልግሎት መስጫው 130 አልጋዎች ያሉት ሲሆን የማስፋፊያ ስራው ሲጠናቀቅ የአልጋ ቁጥሩን 300 በማድረስ እንዲሁም የባለሙያዎችና የመሣሪያ ግብአቶችን በተሻለ ሁኔታ በማሟላት ለተሻለ አገልግሎት እንደሚበቃ ዋና ስራ አስኪያጁ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ የጤና ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር #ዐብይ_አህመድ የአፍሪካ ህብረት ሽልማትን ወስደዋል!!
ዶክተር አብይ አህመድ ተሸለሙ!
.
.
ዶክተር #ዐብይ_አህመድ የአፍሪካ ህብረት ሽልማትን ወስደዋል፡፡ ሽልማቱ በስርዓተ ጾታ እኩልነት ዙሪያ ጥሩ ተግባራትን ለፈጸሙ ግለሰቦች የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍናቸው ወራት ውስጥ በአመራር ስፍራዎች ላይ #የሴቶችን_ተሳትፎ አሳድገዋል፡፡ ለአብነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ግማሽ አባላት ሴቶች እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ ሴት ፕሬዝደንት፣ መከላከያ ሚንስትር፣ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት መሾማቸው ተነስቷል፡፡

#ሴቶች በሙስና ወንጀሎች የመሳተፍ እድላቸው አነስተኛ መሆኑን እና በስራቸው ውጤታማ መሆናቸውን በተደጋጋሚ እንደተናገሩ ተገልጿል፡፡ በስርዓተ ጾታ አቀንቃኞች ዘንድ ዶክተር ዐብይ እንደሚወደሱም ተመላክቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ያገኙት ሽልማት በአፍሪካ ህብረት እና በመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በጋራ የሚዘጋጅ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፦ አፍሪካ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#VisitEthiopia #VisitMekelle

Visit a traditional costumes shop in downtown #Mekelle if you want to get a feel for the traditional dress and #EthiopianCoffee pot (#Jebena), and perhaps take one home.

📷 Elizabeth J. W. Spencer 
#Ethiopia #LandofOrigins

©MysticalEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር አካባቢ ያለውን የጸጥታ ችግር #ለማባባስ ታስቦ ሲዘዋወር የነበረ ህገ ወጥ መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአማራ ክልል ፖሊስ አስታወቋል። በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 1 ሺህ 300 ጥይቶችና 43 ክላሽ ሸንኮቭ የጦር መሳሪያዎችን ነው በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፖሊስ ያስታወቀው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በክልሉ #ወንጀል ሰርተው የተደበቁ አሉ፡፡ ይሄንን ያስተባበረ ያቀናበረ ተልዕኮ የሰጠ እጁን ያስገባ አካል ካለ ተጣርቶ #ለህግ ይቀርባል፡፡" የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲ በድሪ ለአዲስ ዘመን የተናገሩት!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለኳስ አፍቃሪያን🔝

ከደቂቃዎች በኃላ #በአውሮፓ_ቻምፒዮስ_ሊግ ጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ከፓሪስ ሴንት ጀርሜን ይፋለማሉ። በሁለቱም ቡድኖች በኩል ያለውን አሰላለፍ ከላይ ባለው ምስል መመልከት ትችላላችሁ።

•በስራ ላይ ለምትገኙ እና ጨዋታውን የማየት እድል ለሌላችሁ #TIKVAHETHIOPIA የውጤት ለውጥ ሲኖር ያሳውቃችኃል!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይገምቱ...#SPORT

#በአውሮፓ_ቻምፒዮንስ_ሊግ ጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ዛሬ ምሽት 5:00 ማንችስተር ዩናይትድ ከፓሪስ ሴንት ጀርሜን ይገናኛሉ።

ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጨዋታው በማን #የበላይነት የሚጠናቀቅ ይመስላችኃል???

ማንችስተር ዩናይትድ🔴
ፓሪስ ሴንት ጀርሜን🔵

#ቲክቫህኢትዮጵያ #TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ በPSG 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። በሌላ ጨዋታ ደግሞ ሮማ በሜዳው ፖርቶን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
7ኛው ዙር የአሼ ታለንት አንቲ ድራግ የጎዳና ላይ ትርኢት፤ ሩጫ እና የቁንጅና ውድድር!

More 0926449748 , 0911033992
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update በኢትዮጵያ ያለው የፌደራሊዝም ስርዓት በዋናነት ብሄር እና ቋንቋ ላይ መመስረቱ አሁን ላይ ለተፈጠሩት ችግሮች ምክንያት መሆኑ ተገለፀ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትግራይ ዲያስፖራ ፌስቲቫል!

2ኛው ዓለምቀፍ የትግራይ ዲያስፓራ ፌስተቫል ለመካሄድ የሚያስችል ዝግጅት
#መጠናቀቁን የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታውቋል፡፡

ፌስቲቫሉ በተለያዩ የዓለም ሃገራት የሚገኙ የትግራይ ዲያስፓራ ማህበረሰብ በክልሉ ብሎም በሃገራቱ እየተከናወኑ ባሉት የሰላም የዴሞክራሲና የልማት ስራዎች ተሳታፊ ለማድረግ ያለው ነው ተብሏል፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የከተማ ልማትና ንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር #አብርሃም_ተከስተ ዝግጅቱን አስመልክቶ በሠጡት መግለጫ ፌስቲቫሉ የትግራይ ዲያስፓራ ስለሃገራቸውና ስለ ክልላቸው ተጨባጭ ሁኔታ ተገንዝበው ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ደህንነት በተደራጀ መልኩ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማድረግ ነው፡፡

ፌስቲቫሉ ዲያስፓራውን በክልሉ በሚካሄደው የንግድ የኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ ልማት እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ ለማድረግ ነው ያሉት ዶክተር አብርሃም የፐብሊክ ዲኘሎማሲውን በማጠናከር በኢትዮ ኤርትራ የተጀመረውን የሰላም ግንኙነት ተጠናክሮ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ነው፡፡

ዋናው ፌስቲባል ከሃምሌ 24 -ሃምሌ 3ዐ/ 2ዐ11 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ሲሆን የህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ /ህወሓት/ የተመሰረተበትን ቀን ምክንያት በማድረግ ከየካቲት 11/2ዐ11 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እንደሚካሄደ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሩሲያ ኢንተርኔትን ለማቋረጥ እያሰበች ነው‼️

ሩሲያ እራሷን #በኢንተርኔት አማካይነት ከሚፈጸም ጥቃት ለመከላከል በምታደርገው ዝግጅት ለአጭር ጊዜ እራሷን ከዓለም አቀፉ የኢንትርኔት ትስስር #የማቋረጥ አማራጭን እያጤነች ነው።

ይህም ማለት የኢንትርኔት ግነኙነት በሃገር ውስጥ ብቻ የተገደበ ይሆናል። በዚህም ሩሲያዊያን የሚልኩት እና የሚቀበሉት መረጃ እርስ በርሳው እንጂ ከተቀረው ዓለም ጋር አይሆንም።

ለሙከራው የተቆረጠ ቀን ባይኖርም በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚከናወን ይጠበቃል።

የተቀሩት የዓለም ሃገራት ሩሲያን ከዓለም አቀፉ የኢንተርኔት አገልግሎት ቢያገሏት በእራሷ መቋቋም የሚያስችላት ረቂቅ አሰራር እየተገበረች ነው።

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ከዚህ ቀደም ሩሲያ #የሳይበር_ጥቃቶችን ታደርሳለች በማለት ማዕቀብ እንደሚጣልባት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ሩሲያ እንዴት ከተቀረው ዓለም የኢንተርኔት ትስስር እራሷን በማግለል በሃገሪቱ ውስጥ ብቻ የኢንተርኔት አገልግሎትን ማኖር ትችላለች? የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው።

የዘርፉ በለሙያዎች ሲያስረዱ፤ "ኢንተርኔት የሚሰራበትን መንገድ መረዳት ይገባናል" ይላሉ። "በሺህዎች የሚቆጠሩ መረጃዎች የሚተላለፉባቸው ዲጂታል ኔትዎርኮች አሉ። እንዚህ ኔትወርኮች 'ራውተር' በሚባሉ መዳረሻዎች ይገናኛሉ። ሩሲያ ያቀደችው በራውተሮች በኩል ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ እና የሚወጡ ዳታዎችን መቆጣጠር ነው።"

ይህን አካሄድ በመጠቀም ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ መረጃዎችን በመቆጣጠር ረገድ ቻይና ውጤታማ ስለመሆኗ ይነገራል።

ሆን ተብሎም ባይሆን ሃገራት በተለያዩ አጋጣሚዎች ከተቀረው ዓለም ጋር የሚኖራቸው የኢንተርኔት አገልግሎት ከዚህ ቀደም ተቋርጧል። ባህር ውስጥ ያለ የኢንተርኔት ገመድ በመቋረጡ ከዚህ ቀደም አፍሪካዊቷ ሃገር ሞሪታኒያ ለሁለት ቀናት ከተቀረው ዓለም ተነጥላ ነበር።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መርማሪ ፖሊሶቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️

በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የተጠረጠረ ግለሰብ እንዲያመልጥ ያደረጉ መርማሪ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡

በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 1 ሺህ 300 ጥይቶችና 43 ክላሽ ሸንኮቭ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቆ ነበር፡፡

ከጋምቤላ አካባቢ ወደ ጎንደር በኤፍ ኤስ አር መኪና ሲዘዋወሩ የነበሩ 43 ክላሽ ሸንኮቭ እና 1 ሺህ 300 የክላሽ ጥይቶች ከነአሽከርካሪው መያዛቸውንም አይዘነጋም፡፡

በወንጀል ተጠርጣሪ አሽከርካሪው በፖሊስ ተይዞ ምርመራ ሲደረግበት ‹ዋናውን የጦር መሳሪያ አሰራጭ› ጠቁሞ ጎንደር ከተማ ላይ አስይዞታል፡፡ ጉዳዪን ለመከታተል ወደ ጎንደር የሄዱት ሁለት መርማሪ ፖሊሶች ዋናውን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አሰራጭ በቁጥጥር ሥር በማዋል ላይ እያሉም አሽከርካሪው (መጀመሪያ ላይ የተያዘው ተጠርጣሪ) አምልጧል፡፡

ተጠርጣሪ እንዲያመልጥ ማድረግ ደግሞ ወንጀል በመሆኑ ሁለቱም መርማሪ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር #አትንኩት_ከበደ ተናግረዋል፡፡

ሁለት መርማሪ ፖሊሶችና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አከፋፋይ በሚል ተጠርጥሮ ጎንደር ላይ የተያዘው ግለሰብ አሁን ላይ በባሕር ዳር ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሆነው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑንም ኮማንደር አትንኩት ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia