TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተሰየሙት የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ዛሬ ትውውቅ አድርገዋል። በትውውቅ ፕሮግራሙ ለእርቀ ሰላም ኮሚሽን ተልዕኮ ስኬት መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገልፀዋል።

ምንጭ:- ም/ጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ፖሊስ‼️

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 43 ክላሽ ሸንኮቭ የጦር መሳሪያና 1 ሺህ 300 ጥይቶች በቁጥ ጥር ስር ማዋሉን #የአማራ_ክልል_ፖሊስ አስታወቀ።

#የጦር_መሳሪያዎቹን ከጋምቤላ ወደ አማራ ክልል ጎንደር ከተማ በኤፍ ኤስ አር የጭነት ተሽከርካሪ በማስገባት ላይ እያለ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፥ የመኪናው አሽከርካሪም በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
ገልጿል።

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የጦር መሳሪያዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ሥራ እያከናወነ መሆኑንም ነው ኮሚሽኑ የገለፀው።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መካነሰላም🔝

ሰሞኑን በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ #የተቃጠሉ መስጊዶችን መልሶ ለመገንባት ያለመ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር በእስቴ መካነሰላም ከተማ ተካሂዷል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ250,000 ብር በላይ ድጋፍ ተደርገ🔝

በባህርዳርና በደብረ ታቦር የሚኖሩ የአስቴ ወረዳ ነዋሪዎች በቅርቡ የተቃጠሉትን ሁለት መስጅዶች ለመስራት የሚያስችል ሩብ ሚሊዮን ብርና #የሲሚንቶ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ተወላጆቹ በራሳቸው ተነሳችነት ብሩን ከመሰብሰብ ባለፈ ቦታው ደረስ በመሄድ የጎዳቱን ሁኔታ በመመልከት የአለኝታነት ድጋፋቸውን እንዳሳዩ የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ አላምረው ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
በዛሬው ዕለት ገልጸዋል፡፡

ተወላጆቹ ለመስጅዶች ግንባታ አስተባባሪ ኮሚቴ ካስረከቡት 250 ሺህ ብር በተጨማሪም ለግንባታው የሚውል 100 ኩንታል ሲሚንቶ አበርክተዋል፡፡

ተወላጆቹ ድርጊቱን አውግዘው ምንም ዓይነት እኩይ ዓላማ ያለው አካል ትንኮሳ #ቢፈፅም የሁለቱ እምነት ተከታዮች አንድነት የበለጠ ይጠናከራል እንጂ ምንም ዓይነት የሚፈጠር ነገር የለም ብለዋል፡፡

ድጋፉን ያሰባሰቡት የሁለቱም እምነት ተከታይ የወረዳዋ ተወላጆች አጥፊዎቹ ታድነው ተገቢው ቅጣት እንዲሰጣቸውም በድጋፍ ርክክቡ ወቅት ጠይቀዋል፡፡

አጥፊዎችን ለመለየት ከተያዙት 6 #ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ምርመራው #ተጠናክሮ መቀጠሉንም አቶ መላኩ ገልጸዋል፡፡ የተቃጠሉት መስጅዶች ግንባታ በፍጥነት እንደሚጀመር ተመልክቷል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በደቡብ ጎንደር አንዳቤት ወረዳ ላይ የተቃጠለውን የጃራ ገዶ መስጅድ የአካባቢው ማህበረሰብ 27 ሺህ ብር በማዋጣት መልሶ የመስራት ሂደቱን እንደጀመረ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ለኢቢሲ አመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደቡብ ጎንደር አንዳቤት ወረዳ ላይ የተቃጠለውን የጃራ ገዶ መስጅድ የአካባቢው ማህበረሰብ 27 ሺህ ብር በማዋጣት መልሶ የመስራት ሂደቱን ተጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚንስትር #ዐቢይ_አሕመድ ለእርቀ ሰላም ኮሚሽን ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ #መርጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ብርሃኒ እየሱስ ሰብሳቢ ሆነው ሲሾሙ የሕግ ባለሙያዋ የትነበርሽ ንጉሴ ደሞ ምክትል ሰብሳቢ ሆነዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ዛሬ በኮሚሽኑ አባላት የትውውቅ መድረክ ላይ ተገኝተው መንግሥት በኮሚሽኑ ሥራ ጣልቃ እንደማይገባ፣ ኮሚሽኑም ሥራውን ከሐይማኖት፣ ብሄርና ሌሎች መድልዖዎች ነጻ በሆነ መልኩ እንዲያከናውን ጠይቀዋል፡፡

via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ #በሠላም እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ላደረገው ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋና አቀረበ፡፡

32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና ተያያዥ ስብሰባዎች ከጥር 30 እስከ የካቲት 4 ቀን 2011 ዓም ድረስ በአዲስ አበባ መካሄዳቸው ይታወቃል፡፡

ጉባኤው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የአዲስ አበባ ነዋሪ በእንግዳ ተቀባይነትና ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ቀና ትብብር ማድረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢዜአ በላከው መግለጫ ገልጿል፡፡

እንግዶቹ ለልዩ ልዩ ጉዳዮች በአጀብ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በፍፁም ትዕግስት ለእንግዶች ቅድሚያ በመስጠት፤ መንገድ ተዘግቶ ለተሽከርካሪ ክፍት እስከሚሆን ድረስ አሽከርካሪዎች በትዕግስት በመጠበቅ፤ ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ጉባኤው በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ በማበርከቱ አመስግኗል።

የጸጥታ አካላትም ቀንና ሌሊት ኃላፊነታቸውን በትጋት በመወጣታቸው ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል፡፡

ህብረተሰቡ የከተማዋ ፀጥታ አስተማማኝ እንዲሆን የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪ አስተላልፏል፡፡

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ተደረገባቸው‼️

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዋና ሳጂን #እቴነሽ_አረፋይኔን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ።

ዋና ሳጂን እቴነሽ አረፋይኔ የእስረኞችን ጥፍር የመንቀልና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አድርሰዋል በሚል 11 ክሶች ተመስርተውባቸዋል።

የቀድሞ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ አባል የነበሩት ዋና ሳጅን እቴነሽ አረፋይኔ በሽብር ወንጀል ተፈርጀው ታስረው በነበሩ የኦነግና የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት ላይ ሽንት በመሽናት፣ ጥፍር በመንቀልና በሌሎችም ዘግናኝ በተባሉ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ተከሳሿ በተለምዶ ማዕከላዊ ይባል በነበረው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ ቡድን መርማሪ ሆነው ሲሰሩ ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን በሽብር ተግባር ወንጀል ተፈርጀው በታሰሩ ዜጎች ላይ ፈጽመዋል የተባለውን የወንጀል ድርጊት አቃቤ ሕግ ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ የነበረው ክስ ያስረዳል።

ዛሬ የዋና ሳጂን እቴነሽ የዋስትና ጥያቄ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት የተከሳሿን የዋስትና ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል።

ተከሳሿ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር፣ ካልሆነም አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩና ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ፤ እንዲሁም ጡት የምትጠባ ሕፃን ልጃቸውን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ትእዛዘ እንዲሰጥ ጠይቀው ነበር።

ተከሳሿ በመገናኛ ብዙሃን በቀረበብኝ ፕሮግራም ሳቢያ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለመውረድ ለደሕንነቴ ስለምሰጋ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንደቆይ ይፈቀድልኝ ሲሉ ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱም ተከሳሿ ከቀረበባቸው ክስ ውስጥ በተለይም 1ኛ እና 2ኛ ክስ አለአግባብ ስልጣንን በመጠቀም የሙስና ወንጀል በመሆኑና ይህም እስከ 10 ዓመት እንደሚያስፈርድ በመጥቀስ የዋስትና ጥያቄው ተቀባይነት አለማግኝቱን ገልጿል።

በተጨማሪም አንድ ተጠርጣሪ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ሊቆይ የሚችለው በጊዜ ቀጠሮ ምርመራ ላይ ክስ እስኪመሰረት በመሆኑ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲወሰዱና ጉዳይቸውን በዛው ሆነው እንዲከታተሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ነገር ግን በደህንነታቸው ላይ ምንም አይነት ስጋት እንዳይኖራቸው፣ ማረሚያ ቤቱም ሕገ-መንግስታዊ መብታቸውን እንዲያስከብር በማለት ነው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ የሰጠው።

በተጨማሪም ዋና ሳጂን እቴነሽ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መክረው ልጃቸው አብራቸው እንድትሆን ከፈለጉም ማረሚያ ቤቱ እንዲቀበላቸው አዟል።

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ የዋና ሳጂን እቴነሽ አረፋይኔን የክስ መቃወሚያ ለመቀበል ለየካቲት 13 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 4 ሚሊየን ብር የሚገመት 80 ኪሎ ግራም የብር ጌጣጌጥ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ። በዛሬው ዕለት በአዋሽ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ግምታዊ ዋጋቸው 3 ሚሊየን 953 ሺህ 200 የሚሆኑ 80 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ የብር ጌጣጌጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል። በተጨማሪም ግምታዊ ዋጋቸው 661 ሺህ የሆኑ የተለያዩ አልባሳት እና መለዋዎጫዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለፀው። በተመሳሳይ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ ግምታዊ ዋጋቸው 166 ሺህ 700 ብር የሆነ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በጥቅሉ በዛሬው ዕለት ብቻ 4 ሚሊየን 580 ሺህ 900 ብር የሚገመት የኮንትሮ ባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር መዋሉ ነው የተገለፀው።

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia