TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Assosa

ከሰሞኑን በአሶሳ ከተማ ውስጥ በግለሰቦች ቤት በተደረገ ፍተሻ የተከማቸ 50 በርሜል ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የአሶሳ ከተማ ፖሊስ ለኢዜአ በሰጠው ቃል ፤ በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸው 50 በርሜል ነዳጅ (ቤንዚን እና ናፍጣ) ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር በህብረተሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድቷል።

በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በከተማው #ቤንዚን እና #ናፍጣ በጥቁር ገበያ በሊትር እስከ 200 ብር እየተሸጠ መሆኑን ፖሊስ የጠቆመ ሲሆን የዚህ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ምንጭ በህጋዊ መንገድ ከነዳጅ ማደያዎች ተቀድቶ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ጥቂት ግለሰቦች እጅ መግባት መሆኑን አስረድቷል።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ #Update

ወደ ትግራይ ክልል #ነዳጅ መግባት መጀመሩን የክልሉ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው ፤ ወደ መቐለ 10 ቦቴ ነዳጅ መግባቱን ያመለከተ ሲሆን ወደ ኩዊኃ እና ዓጉላም ነዳጅ መግባት መጀመሩን ጠቁሟል።

ከፌዴራል መንግስት ጋር ጥሩ ትብብር እየተደረገ ነው ያለው ቢሮ " እናተ ጋር ካለው ችግር አንፃር ቅድሚያ እንሰጣለን " ተብለናል ሲል ገልጿል።

ጦርነት ለመፈጠሩ በፊት በወር 12 ሚሊዮን ሊትር ናፍጣ ይገባ እንደነበር የገለፀው ቢሮው አሁን እየገባ ያለው ነዳጅ ከሚፈለገው አንፃር እጅግ በጣም ትንሽ ነው ብሏል።

መቐለ ውስጥ ካሉት 15 ማደያዎች ነዳጅ የገባው በ4ቱ ላይ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

ነዳጅ ለማግኘት እነማን ቅድሚያ አላቸው ?

አሁን እየገባ ያለው ነዳጅ በተወሰነ መልኩ ስለሆነ ፦

- አምቡላንስ
- እሳት አደጋ
- ውሃ አቅራቢ ቦቴዎች
- የመንግስት ተሽከርካሪዎች
- የእርዳታ አከፋፋይ አካላት
- ባንክ፣ ቴሌ፣ መብራት ኃይል
- በትራንስፖርት ቢሮ ታሪፍ የወጣላቸው ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ቅድሚያ እንደሚያገኙ ተመላክቷል።

የፋይናንስ እጥረት በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እንዳይገባ እንቅፋት መሆኑን ያሳወቀው ቢሮው ችግሩን ለማፍታት ከባንክ ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ቤንዚን እና ናፍጣ ስንት እየተሸጠ ነው ?

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከፌዴራል መንግስት ለክልሉ እንደተላከ ለመረዳት ተችሏል።

በመቐለ #ቤንዚን በሊትር 60 ብር ከ57 ሳንቲም እየተሸጠ ሲሆን #ናፍጣ 66 ብር ከ58 ሳንቲም እየተሸጠ መሆኑን ከክልሉ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Photo Credit : Tigrai Television

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቤንዚን ? በአዲስ አበባ ቤንዚን ረጅም ሰዓት ሰልፍ ሳይሰለፉ ማግኘት ዘበት ከሆነ ሰነባብቷል። ባለፉት ሳምንታት በትንሽ በትንሹ የጀመረው የቤንዚን ሰልፍ ከሰሞኑን እጅግ ብሶበታል። በአንዳንድ ማደያዎች " ቤንዚን የለም " እየተባለ ሲለጠፍ ቤንዚን ያለባቸው ማደያዎች እጅግ በጣም ረጅም ሰልፍ ነው ያለው። በዚህም ምክንያት የመኪና አሽከርካሪዎች ቀናቸውን በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ይገኛሉ።…
#ቤንዚን

° " ቤንዚን ማግኘት ፈተና ሆኖብልናል " - አሽከርካሪዎች

° " የቤንዚን አቅርቦት ችግር የለም " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን

አሁን ላይ በአዲስ አበባ ቤንዚን ማግኘት አስቸጋሪ እንደሆነባቸው አሽከርካሪዎች እየገለጹ ናቸው።

የተለያዩ ማደያዎች ላይ " ቤንዚን የለም " የሚል የተለጠፈ ሲሆን ቤንዚን አለባቸው የሚባሉና የሚቀዳባቸው ማደያዎች ላይ እጅግ በጣም ረጅም ሰልፎች ነው ያሉት።

አሽከርካሪዎች ቤንዚን ለመቅዳት ሰዓታትን ለመሰለፍ እየተገደዱ ነው። በዚህም ቀናቸውን በሰልፍ እያሳለፉ በመሆኑ ስራቸው እየተበደለ ነው።

ምንም እንኳን ከሰሞኑን ችግሩ ብሶ ቢታይም ባለፉት ሣምንታት አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሰልፎች ይታዩ ነበር።

ለመሆን ምንድነው የተፈጠረው ?

በዚህ ጉዳይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን መ/ቤትን ማብራሪያ ጠይቋል።

የተፈጠረው ነገር ምንድን ነው ? ስንል ጥያቄ ያቀረብንላቸው የባለስልጣኑ አንድ አካል በሰጡን አጭር ማብራሪያ፣ " የቤንዚን እጥረቱ የለም " ብለዋል፡፡

በከተማዋ ያለውን ችግር በተመለከተ ፤ " የእኛ ልጆች ኢስፔክሽን ሲወጡ ያዩት ነገር አሁን የቴሌ ብር አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ነው፡፡ ምክንያቱም በካሽ ግብይት መፈጸም አይቻልም ፤ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ስለሆነ አብዛኛው ሰው ያንን ሲስተም ሳይጠቀም ቆይቶ በካሽ ትራንሰፈር እያደረገ ነበር፡፡ በዚያ ምክንያት አንዱ ከማደያ ላይ ነዳጅ ቀድቶ ለመውጣት ረጅም ሰዓት ይወስዳል " ብለዋል፡፡

" እናም ረጃጅም ሰልፍ የሚፈጠረው በዛ ነው እንጅ በእጥረት አይደለም " ብለው ለተጨማሪ መረጃ ወደ ሌላ የሚመለከተውን የተቋሙ አካልን የመሩን ሲሆን ሌላኛው አካል ማብራሪያ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ቢሰጡም በቀጠሮ ሰዓት በተደጋጋሚ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

በሌላ በኩል ፥ ባለስልጣን መ/ቤቱ ለካፒታል ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፥ በአዲስ አበባ ከተማ በአማካይ እስከ 1.4 ሚሊየን ሊትር ቤንዚን እያቀረበ መሆኑን አመልክቷል።

" በአዲስ አበባ ከሰሞኑ በነዳጅ ማደያዎች ላይ የተስተዋለው ያልተለመደ ሰልፎች ባለፈው ሣምንት በነበሩት ሁለት ቀናት ከበዓላት ጋር በተያያዘ የአቅርቦት መቀነስ በመኖሩ ነዉ " ብሏል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ፥ " በከተማዋ በቀን በአማካይ እስከ 1.4 ሚሊየን ሊትር ቤንዚን የሚቀርብ ቢሆንም የማደያዎቹ አገልግሎት አሰጣጥ ዝግታ መኖሩ እና የቤኒዚን ምርት ላይ ከፍተኛ የጥቁር ገበያ ፍላጎት መኖር ሠልፎችን ምክኒያት በማድረግ የአቅርቦት ዕጥረት ያለ በማስመሰል አጋጣሚውን ለትይዩ ገበያዉ ለመጠቀም መሞከር ይታያል " ሲል አስረድቷል።

" ከነዳጅ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ያለው ሁኔታ በአፋጣኝ እንዲስተካከል የተደረገበት እርምጃ እንዲወሰድ ተደርጓል " ያለዉ መ/ቤቱ " በዚህም በመዲናዋ ከመደበኛ ኮታ ተጨማሪ ቤንዚን እንዲቀርብ ሆኗል " ሲል አስታዉቋል።

" የየቤኒዚን ተጠቃሚ አሽከርካሪዎች አቅርቦት በበቂ ሁኔታ መኖሩን ተረድተው በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ ማደያዎችን በመጠቀም መገልገል ይችላሉ " ሲል አሳስቧል።

#AddisAbaba #Benzine

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የዜጎችድምጽ ችግሩ ቢነገር ቢነገር መፍትሄ ያልተገኘለት በክልሎች ያለው የቤንዚን ጉዳይ ! በክልል ከተሞች ነዳጅ በተለይም ቤንዚን ማግኘት ፈተና እንደሆነ ቀጥሏል። በርካታ በትራንስፖርት ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ባለው ችግር ምክንያት ሰርቶ መግባት ቤተሰብ ማስተዳደር ከባድ ሆኖባቸዋል። ከክልል ከተሞች አንዷ የሲዳማ መዲናዋ ሀዋሳ ናት። በዚህች ከተማ ነዳጅ እንደልብ ማግኘት ከቆመ ዓመታት አልፈዋል።…
#ቤንዚን🚨

🔴 " በክልሉ የቤንዚን ችግር የፀጥታ ጉዳይ ወደ መሆን ደርሷል " -  የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ

🔵 " በማደያዎች አከባቢ የሚነሱ ሕገ ወጥ ተግባራት ሕብረተሰቡ በመንግስት ላይ እንዲነሳሳ እያደረገ ነዉ " - የሲዳማ ክልል ንግድ ቢሮ


በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተለይም በመዲናዋ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣዉን ቤንዚን ማግኘት ፈተናን ተከትሎ የተስተዋሉ ችግሮችን በተደጋጋሚ መዘጋባችን ይታወሳል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በትላንትናዉ ዕለት በሰጡት መመሪያ፥ በክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የሚመራ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል።

ግብረ-ኃይሉ በዛሬው ዕለት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሰፊ ዉይይት በማድረግ የዉሳኔ ሃሳቦችን ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማወቅ ችሏል።

በዚህም መሰረት በተለያዩ ክልሎች የነዳጅ ምርት እጥረት ቢኖርም በሲዳማ ክልል በተለይም በሀዋሳ ከተማ ያለዉ የህገ-ወጥ ንግድ ህብረተሰቡን ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ሲዳርግ መቆየቱ ተጠቅሷል።

በማደያዎች፤ በንግድና ገበያ ልማት ባለሙያዎች ፤ ከፀጥታ አካላት በኩል ያሉ ክፍተቶች በመድረኩ ተነስቷል።

ማደያዎች በሌሊት ለቸርቻሪዎች ከመሸጥ እስከ ነዳጅ ቦቴዎችን መሰወር ድረስ ፤ የንግድና ገበያ ልማት ባለሙያዎች ደግሞ ከሕገ-ወጥ ነጋዴዎች ጋር አብሮ መስራትን ጨምሮ ከማደያ ቀጂዎች ጋር በመመሳጠር ቤንዚን ማሸሽ ድረስ ተሳታፊ ነበሩ ተብሏል።

እንዲሁም የፀጥታ አካላት የሌሎችን ተሽከርካሪዎች የራሳቸዉ በማስመሰል ለህገወጥ ግብይቱ ምክንያት መሆን ጨምሮ ተገቢውን እርምጃ አልወሰዱም የሚል ግምገማም በመድረኩ ቀርቧል።

ግብረ-ኃይሉ ለእነዚህ እና ሌሎችም መሰል ችግሮች የመፍትሔ ኃሳቦች ናቸዉ ያላቸዉን አስቀምጧል።

አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊና የግብረ-ኃይሉ ሰብሳቢ ምን አሉ ?

በክልሉ የቤንዚን ችግር የፀጥታ ጉዳይ ወደ መሆን ደርሷል ያሉ ሲሆን፥ በዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ የተጀመረዉ እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ገልጸዋል።

" መንግስት በከፍተኛ ድጎማ የሚያስገባውን ቤንዚን ማንም ከዚህ በኋላ ለግል መበልፀጊያ  ማድረግ አይችልም ፤ ከዛሬ ጀምሮ የቤንዚ አቅርቦትና ስርጭት ሂደቱን ግብረሃይሉ ይመራዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ከዚህ ቀደም ተሽከሪካሪ ተለይቶ ይደለደል የነበረዉ አሰራር ከነገ ጀምሮ አይኖርም ነው ያሉት።

ማደያ ለሌለባቸዉ አከባቢዎች ሲደረግ የነበረዉ አሰራር በሕግና ደንቡ መሠረት ብቻ ይከናወናልም ሲሉ አንስተዋል።

ማንኛዉም የፀጥታ መዋቅር አባላት ያሏቸዉ የቤንዚን ተሽከሪካሪዎች በየተቋሞቻቸዉ ተለይተዉ በሕጋዊ መንገድ በኩፖን ብቻ እንደሚስተናገዱ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ተናግረዋል።

አክለውም " ከነገ ቀን ጀምሮ በቤንዚን ሽያጭ ላይ በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች በተለይ ደግሞ ሀዋሳ ከተማ ላይ ይታይ የነበረዉን ሕገ-ወጥ ስርዓት አደብ እናስገዛለን " ብለዋል።

በተጨማሪም ፦

➡️ የፀጥታ መዋቅር አባላት ከየማደያዉ ጣልቃ ገቢነት እንደሚወጡ፤

➡️ ከነገ ጀምሮ ካሜራ ያልገጠሙ ማደያዎች አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል።

የክልሉ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት መኩሪያ ምን አሉ ?

" በማደያዎች አከባቢ የሚነሱ ህገወጥ ተግባራት ሕብረተሰቡ በመንግስት ላይ እንዲነሳሳ እያደረገ ነዉ " ሲሉ ተናግረዋል።

ኃላፊዋ፥ " እንደ ሀገር የአቅርቦት እጥረት ቢኖርም በሀዋሳ ከተማ በብዛት የሚስተዋለው ግን ሰዉ ሰራሽ ችግር ነዉ ፤ ይህም ችግር ዘርፈ ብዙ መሆኑን በጥናት አረጋግጠናል " ብለዋል።

" መንግስትንና ሕዝብን ለማጣላት የሚሰሩ ማደያዎችን ከድርጊታቸው ካልተቆጠቡ እርምጃው ይቀጥላል፤ ከኤልክትሮንክስ ግብይት ዉጪ ሽያጮችን የሚያካሂዱ ማደያዎችም በሕግ አግባብ ከመጠየቅ ባለፈ የነዳጅ ምርቶችን መግኘት አይችሉም " ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

አሁን ላይ ጣት ከመጠቋቆምና አንዱ በሌላዉ ከማማካኘት ይልቅ ሕዝብ በተማረረበት በዚህ የቤንዚን ጉዳይ አስቸኳይ እርምጃ መዉሰድ እንደሚያስፈልግም ወ/ሮ ሠላማዊት መንገሻ በመድረኩ አንስተዋል።

⚠️ከፍተኛ የቤንዚን ችግር ሲዳማ ክልል ውስጥ ብቻ ያለ ሳይሆን ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉት ሁሉም ክልሎች ላይ ተመሳሳይ ነው። ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች ስራ ሰርተው መግባት መኖር ፤ ቤተሰብ ማስተዳደር ፍጹም አልቻሉም። ህዝቡ እጅግ ተማሯል። ማደያዎች ላይ " የለም " ይባላል ግን በጥቁር ገበያ እስከ 200 ብር ድረስ በግልጽ በአደባባይ ይቸበቸባል። አንዳንድ ከዋና ዋና ከተማ በወጡ ማደያዎች በትውውቅ በሊትር እስከ 200 ብርና ከዛ በላይ ይቸበቸባል። ቤንዚን ለሊት ላይ በድብቅ ከየማደያው እየተጫነ ከከተማ በህገወጥ መንገድ ይወጣል። ይህ ህገወጥ ተግባር መንግሥት እርከን ውስጥ ካሉ አካላት አንስቶ የማደያ ሰዎች፣ የጸጥታ ሰዎች ከላይ እስከ ታች ድረስ ረጅም ሰንሰለት ነው ያለው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የክልሎች የቤንዚን ስርጭትን ጉዳይ አሁንም መከታተሉን ይቀጥላል።

#TIKVAHETHIOPIA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM