TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከ30 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ሊተላለፉ ነው‼️
.
.
በቀጣይ ስድስት ወራት ከ30 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች #ለማስተላለፍ ዝግጅት ላይ መሆኑን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚንስቴር አስታወቀ።

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አቶ #ጃንጥራር_አባይ በምክር ቤቱ ቀርበው የሚኒስተሩን የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።

ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው፥ በቀጣይ 6 ወራት ግንባታቸው የተጀመሩ የመኖሪያ ቤት ልማት ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውን አስታውቀዋል።

እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያም 44 ሺህ ቤቶችን ለማስተላለፍ ቢታቀድም በበጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ከ30 ሺህ በላይ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች እንብደሚተላለፉ ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

በዚህም17 ሺህ የሚሆኑት  የ40/60 የቤት ልማት ፕሮጀክት ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ የ20/80 መሆናቸውን ሚኒስትሩ አቶ ጃንጥራር አባይ ገልፀዋል።

በዚህ ዓመት የሚተላለፉት መኖሪያ ቤቶች አሁን ላይ ግንባታቸው በአብዛኛው ወደ ማለቁ ሲሆን፥ የአሳንሰርና የማጠናቀቂያ እቃዎች መግጠም እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ መሰረተ ልማት ስራቸው እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ቀደም ሲል ሙሉ የቤቱን ዋጋ የከፈሉ ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ  የሚሰጣቸው መሆኑ በመመርያ የተለየ ቢሆንም ከተከሰተው የዋጋ ጭማሪ አንፃር የቤቱን ሙሉ ዋጋ የከፈለ ተመዝጋቢ አለ ማለት አይቻልም ብለዋል።

በዚህም መሰረት በተለይም በ40/60 የቤቶች መርሃ ግብር ተመዝግበው በመቆጠብ ላይ የሚገኙ ፈላጊዎች 40 በመቶ መቆጠብ ከቻሉ በእጣው መካተት እንደሚችሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም 1 ሺህ 700 የኪራይ ቤቶች ግንባታ በአራት ኪሎ ባሻ ወልዴ እና በለቡ እየተካሄደ መሆኑንም ነው ያስታወቁት።

ከዚህ ባለፈ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የከወናቸውን ተጨማሪ ስራዎች ለምክር ቤቱ ያቀረቡት ሚኒስትሩ ፥ ባለፉት ስድስት ወራት ተቋሙን እንደ አዲስ የማደራጀት፣ የአመራር ስልጠና እንዲሁም በስራ እድል ፈጠራ እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ስልጠና መሰጠቱን አስታውቀዋል።

ከዚህ ውጪም በ6 ወሩ በከተሞች የስራ እድል ፈጠራ በአጠቃላይ ለ589 ሺህ 215 ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል ያሉ ሲሆን፥ ይህም ከተያዘው እቅድ 62 ነጥብ 8 መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስርን ለመፍጠር በተሰራው ስራም በ6 ወራቱ የ8 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር የገቢያ ትስስር መፍጠር ተችሏል ያሉት ሚኒስትሩ፥ ኢንተርፕራዞቹ 4 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር እንዲቆጥቡ መደረጉንም ገልፀዋል።

ለ103 ሺህ ጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሶችም ብድር እንዲመቻች መደረጉንም ነው ሚኒስትሩ ለፓርላማ አባላት ያብራሩት።

የሊዝ አዋጅን በተመለከተም በአዋጁ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የሊዝ አዋጁን የማሻሻል ስራ እየተሰራ መሆኑንም ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት።

በአሁኑ ወቅትም የሊዝ አዋጁ ክለሳ ተጠናቆ ለሚለከተው አካል መላኩን እና በቅርቡም ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።

ሰነድ አልባ የከተማ መሬቶችን በተመለከተም በ6 ወራቱ ለ60 ሺህ ሰነድ አልባ መሬቶች ሰነድ ለመስጠት ታቅዶ ለ20 ሺህ 153 መሬቶች የህጋዊ ይዞታ ማረጋገጫ መሰጠቱን አስታውቀዋል።

የከተሞች ፎረምን በተመለከተም ከየካቲት 9 እስከ 14 2011 ዓ.ም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እንደሚዘጋጅ የገለጹት ሚኒስትሩ  ከ800 በላይ ከተሞች እንዲሳተፉ ይደረጋል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ህገ ወጥ ይዞታዎችን ስርዓት እንዲይዙ የማድረግ ስራ መሰራቱንም አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia